Awusa.com
A resource and advocacy center for the art, history, culture, ethnography and current affairs of Afa
06/06/2026
!!
"የቀይ ባህር ትውልድ" የ 140 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የሆነው የባህር በራችን ለማስመለስ በዛሬው የሆርሶ ምርቃት በእናት ሀገራችን ባንዴራ ቃል ገብተዋል ።
የፅናት ኮርስ እጩ መኮንኖች የምረቃ ስነ ስርዓት ዓርማቸውና ዓላማቸው " የቀይ ባህር ትውልድ " አድርገው የተግባር ጉዛቸውን ጀምረዋል።
ድል አንድ ለእናቱ
ሺ ለጠላቱ
ጀግናው የኢትዮጵያ 🇪🇹 መከላከያ ሰራዊታችን💪
06/06/2026
ኤርትራ የንጹህ መጠጥ ውሃ እጥረት ገጠማት።
የውሃ ማጓጓዣ ታንከሮች ስራ ማቆማቸው ለዋሃ እጥረት መከሰት ምክንያት ሆኗል።
የአሜሪካ እና የኢራን ጦርነት ባስከተለው የሀይል እጥረት ኤርትራ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገልጿል።
በዚሁ የሀይል እጥረት ሳቢያ ነዳጅ የሚጠቀሙ የውሃ ታንከሮች ስራ አቁመዋል ተብሏል።
የመጠጥ፣ የንፅህና እና ሌሎች አገልግሎት የሚውል በቂ የውሃ አቅርቦት አለመኖሩ ተመልክቷል። የውሃ እጥረት በከተማ እና በገጠር ዋነኛ ችግር ሆኗል ተብሏል።
06/06/2026
“የትግራይ ህዝብ ልጆቼን ለጦርነት አልሰጥም ማለት አለበት ‼️”ጀነራል ሳሞራ
05/06/2026
ሂዝቦላህ ቡድን የትጥቅ ትግሉን ለማቆም ቃል አለመግባቱ ተገለፀ
የሊባኖሱ የሂዝቦላህ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሼክ ናኢምቃሲም ቡድኑ የትጥቅ ትግሉን ለማቆም ለማንም ቃል እንዳልገባ አስታወቁ።
ሼክ ናኢምቃሲም በሰጡት መግለጫ የድርድር ዋና ዓላማ የተቃውሞ ኃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት ከሆነ ይህ ድርጊት የሊባኖስን ጥንካሬ የሚያዳክም እና ህልውናዋን የሚፈታተን አደጋ መሆኑን አስረድተዋል።
ዋና ጸሐፊው አክለውም ይህ አካሄድ ሊባኖስን ወደ አለመረጋጋት የሚከት ለእስራኤል ጥቅም ሲባልም በሊባኖሳውያን መካከል የእርስ በርስ ግጭትን የሚቀሰቅስ የጥፋት አዋጅ ነው ሲሉ ከሰዋል።
እስራኤል በጦርነት ማሳካት ያልቻለችውን ግብ በፖለቲካዊ ድርድር ለማሳካት እየጣረች እንደሆነ የጠቆሙት ሼክ ናኢምቃሲም የመሬታችን ይዞታ እስካለ ድረስ የተቃውሞ ትግላችን ይቀጥላል ብለዋል።
በመግለጫቸውም ሊባኖስ መሬቷን መልሳ እንድታገኝ ላደረገችው ድጋፍ ኢራንን አመስግነዋል።
አያይዘውም የሊባኖስ ህዝብ እየተገደለ እና አገራት እየተደበደቡ እስካለ ድረስ እስራኤላውያን ሰፉሪዎች በጭራሽ ደህንነት አይሰማቸውም በማለት ማስጠንቀቂያ ሰንዝረዋል።
የሂዝቦላህ ዋና ጸሐፊ ንግግር ቡድኑ በጸና አቋሙ እንደሚቀጥል የሚያሳይ መሆኑን ታዛቢዎች እየገለጹ ይገኛሉ።
#ሂዝቦላህ #ሊባኖስ #እስራኤል #መካከለኛውምስራቅ #የፖለቲካትንታኔ #የጦርነትስልት #አለምአቀፍዜና
04/06/2026
የመከላከያ ሰራዊትን የሚገዳደር ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል የለም!
ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ምርጫን ለማደናቀፍ ወደ ግሽ ዓባይ ከተማ የገሰገሰው ጠላት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሷል።
ራሱን 44ኛ ክፍለ ጦር ብሎ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን በሰከላ ወረዳ ምርጫን ለማደናቀፍ ወደ ግሽ ዓባይ ከተማ ትንኮሳ ያደረገ ቢሆንም በጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና የአካባቢው የጸጥታ ሃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እና ቁልፍ አመራሮቹን አጥቶ ከፍተኛ ኪሳራ አስተናግዶ ያሰበው ሳይሳካለት ተመልሷል።
እንዲሁም በሌላ ግንባር ምርጫን ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሰዉ በኋላም በጀግናዉ የመከላከያ ሰራዊታችን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ የተመለሰዉ ፅንፈኛዉ የ44ኛ ክ/ጦር ብሎ በሚጠራዉ የሽፍታ ስብስብ ዉስጥ ከፍተኛ አመራር የነበረዉ ጤናው አቻምየለህ የተባለ ኝፍታ እስከ ወዲያኛዉ ተሸኝቷል ።
የመከላከያ ሰራዊታችን አሁንም ግዳጅ በሚወስድባቸዉ ቀጠናዎች ሁሉ የማህበረሰቡን ሰላም ለማዎክ በሚንቀሳቀሱ የፀረ ሰላም እነ የሸኔ አባላት ላይ ብርቱ ክንዱን እያሳረፈ ይገኛል 💪
04/06/2026
-የሶማሊያ ሕገ-መንግሥታዊ በሞቃዲሾ ከባድ የተኩስ ልውውጥ አስከተለ
-ኢጋድ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ጠይቋል
የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ)በሶማልያ የተፈጠረዉን ሕገ-መንግሥታዊ ቀውስ እና ዉጥረት ተከትሎ በመዲናዋ ሞቃዲሾ የተከሰተዉ ሁከት በጥልቅ እንዳሳሰበው አስታወቀ።
ኢጋድ ዛሬ ሐሙስ ባወጣው መግለጫ ማንኛዉንም ዓይነት የኃይል እርምጃዎች በማዉገዝ ሁሉም አካላት ከኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ፣ ውጥረቱን እንዲያረግቡ እና ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ እና ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ በውይይት እንዲፈቱ አሳስቧል።
የኢጋድ ስራ አስፈፃሚ ወርቅነህ ገበየሁ «በዚህ ወሳኝ ወቅት ሰላምን፣ መረጋጋትን፣ ሀገራዊ አንድነትን እና በሶማሊያ የመንግሥት ግንባታ ጥረቶች የተገኙ ድሎችም እጅግ አስፈላጊ ናቸው" ሲሉ ተናግረዋል።
ኢጋድ ይህን አስቸኳይ መግለጫ ዛሬ ይፋ ያደረገዉ ፤ ትናንት ለሊቱን ለዛሬ ሐሙስ አጥብያ የሶማሊያ ዋና መዲና መቃዲሾ በከባድ የተኩስ ድምጽ ስትናወጥ ማደርዋን ተከትሎ ነዉ። የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበዉ በከተማዋ ላይ ከፍተኛ ጭስ ሲንቦለቦል ታይቷል። ከግንቦት ወር አጋማሽ ወዲህ ሶማሊያ አዲስ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ የገባችዉ፤ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ በግንቦት 15 የሚያበቃው የስልጣን ዘመናቸውን ለአንድ ዓመት እንደተራዘመ ካሳወቁ በኋላ ነዉ።
ይህን ተከትሎ በሀገሪቱ ይደረጋል ከተባለዉ የተቃዉሞ ሰልፍ በፊት በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ከፍተኛ ቀዉስ እና ግብግብ መፈጠሩን የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የተቃዋሚዎች እና የክልል መሪዎች የፕሬዚዳንቱን እርምጃ ውድቅ አድርገው ድርጊቱን በመቃወም ዛሬ ሐሙስ ሞቃዲሾ ላይ የተቃዉሞ ሰልፎችን ጠርተዉ ነበር።
ይሁን እና ከተቃውሞው በፊት ትናንት ረቡዕ እለት የተቃዋሚ መሪዎች ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ ፣ግጭቱ ተቀስቅሶ ሌሊቱን መቀጠሉን በአካባቢው የሚገኙት የAFP ጋዜጠኞች ዘግበዋል።
03/06/2026
“የሙስና አባት”
03/06/2026
የጀግናው ውድቀትና የሴራው ማዕበል፦ የሃየሎም አርአያ ግድያ ምስጢር፦
መግቢያ፦ ከዓመታት በኋላ የፈነጠቀ እውነት?
ከአዝማናት መጋረጃ ጀርባ የተሸሸገ፣ የሰዎችን ቀልብ የሚገዛና የሚያስገርም አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ ከ14 ዓመታት በኋላ በድንገት እጄ ገባ። “የሃየሎም አርአያ ግድያ ምስጢር” በሚል በኢትዮሚዲያ የተጠናቀረው ይህ ጽሑፍ፣ እውነት ይሁን የፈጠራ ጥበብ ባይለይም፣ በውስጡ የያዛቸው ስሞችና ክስተቶች ግን እጅግ አነጋጋሪና አሳሳቢ ናቸው። የወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት የወለደውን ይህን እንቆቅልሽ፣ “እውነት ቢሆንስ?” በሚል ትልቅ የጥያቄ ምልክት ለታሪክ ፍርድ ትቼዋለሁ።
በደም የተፃፉ “የፖለቲካ ድራማዎች”
ባለፉት የአገራችን የፖለቲካ ምዕራፎች፣ መጋረጃቸው ሳይገለጥ የቀሩ የባለስልጣናት ድንገተኛ ሞቶች በርካታ ናቸው። የሃየሎም አርአያ በቡና ቤት መገደል፣ የክንፈ ገብረመድህን በጓደኛ እጅ ማረፍ፣ የኢያሱ በርሀ እና የገብረመስቀል ኃይሉ ድንገተኛ ህልፈት... ሁሉም አስቀድሞ የተጠነሰሰ የፖለቲካ ትያትር አካል ይመስላሉ።
ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የኮሎኔል በርሔ ሸቢያ አሳዛኝ ፍጻሜ ነው። በጦር ሜዳ ጀግንነቱ የተመሰከረለት ኮሎኔሉ፣ የመለስ ዜናዊን አካሄድ በይፋ በመቃወሙ ሳቢያ፣ “ለውይይት” ወደ አዲስ አበባ በተጠራበት ምሽት በመኖሪያ ቤቱ ተገደለ። ይፋዊው መግለጫ “ሚስቱ ገድላው ራሷን አጠፋች” ቢልም፣ እውነታው ግን የመጡት የደህንነት “እንግዶች” ሁለቱንም በደም ባህር ውስጥ አስጥመው፣ የሃሰት ትረካውን ሽጉጥ አቅፈው ማስቀጠላቸው ነበር።
የሃየሎም እምቢተኝነት እና የሀኒሽ ደሴቶች ውዝግብ
በሰራዊቱ ዘንድ እንደ ጣኦት የሚመለከቱት የጦር አዛዡ ሃየሎም አርአያ፣ ከመለስ ዜናዊ ጋር የነበረው ቅራኔ የትየለሌ ነበር። በተለይም ኤርትራን በተመለከተ የሚከተለው ፖሊሲ ለአገር እንደማይበጅ በይፋ ይናገር ነበር።
በ1987 ዓ.ም በአራተኛ ክፍለ ጦር በተደረገው ስብሰባ፣ ሳሞራ ዩኑስ የኢትዮጵያ ጦር ከኤርትራ ጎን ተሰልፎ የመንን እንዲወጋ ሲያቅድ፣ ሃየሎም በቁጣ ተነሳ፦ “አንድም ኢትዮጵያዊ ወታደር ለሌላ አገር ጥቅም ሲል ደሙን መገበር የለበትም!” በማለት አዳራሹን በዝምታ አናወጠው። መለስ ዜናዊ ራሱ ስብሰባውን ተረክቦ ሃየሎም አቋሙን እንዲቀይር ቢማፀንም፣ የጀግናው ምላሽ ግን “የሻዕቢያ ደም በገነፈለ ቁጥር አንከተልም” የሚል የማይልስ ቃል ነበር።
ምስጢራዊው ዘመቻ እና የሰካራም ጥይት
የሃየሎምን የማይበገር አቋም የተገነዘቡት የሴራው መሃንዲሶች እሱን ያገለለ ምስጢራዊ ኮሚቴ አቋቋሙ። የኢትዮጵያ ወታደሮች የኤርትራን ዩኒፎርምና መታወቂያ ለብሰው፣ እንደ ጥላ ተደብቀው ወደ አውደ ውጊያው እንዲገሰግሱ ተደረገ። የብዙዎች ህይወት በከንቱ አለፈ፣ የታሪክ መዛግብትም ተደፈኑ።
ይህ እውነት ሾልኮ ሰራዊቱ ጋር መድረሱ ለመለስ ስልጣን አስጊ ነበርና ሃየሎም መወገድ ነበረበት። በሁለተኛው ወር፣ ያ ቆፍጣና መሪ በመዝናኛ ስፍራ “በሰካራም ኤርትራዊ ጥይት” ተመትቶ ወደማይመለስበት ዓለም ሄደ።
የጥላው በረኞች፦ የሴራው ፈጻሚዎች
ከኤርትራ መንግስት በቅርቡ የኮበለሉ የውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት፣ የዚህ ግድያ መረብ የተሸረበው በሚከተሉት ግለሰቦች ነበር፦
ኡመር ገብረወይኒ እና ልጁ፦ ግድያውን ከአዲስ አበባ ሆነው የመሩ የኤርትራ ደህንነቶች።
ክንፈ ገብረመድህን እና ጌታቸው አሰፋ፦ የውሳኔውና የክትትሉ አጋዥ የነበሩ የደህንነት ሹሞች።
አሰፋ ጉሬዛ እና ልዑል የኋላ፦ መረጃዎችን የማድበስበስና ሌሎችን የማስወገድ ኃላፊዎች።
ጀሚል ያሲን፦ በመጨረሻም የሞትን ቃታ የሳበው ተራ መልዕክተኛ።
የመጨረሻ ቃል
የታሪክ እውነት መቃብር ፈንቅሎ መውጣቱ አይቀሬ ነው። ላሁኑ ግን ላለፉት ነፍሳት ምህረትን፣ ለህያዋን ደግሞ የማንገዳደልበትን የእፎይታ ዘመን እየተመኘሁ፣ ይህንን የታሪክ እንቆቅልሽ እዚህ ላይ አበቃለሁ።
ፈጣሪ አገራችንን ይባርክ!
Assaf Hailu
03/06/2026
🚨 አስደንጋጭ መረጃ፡ የትግራይ ወጣቶች ሰቆቃ እና የተደበቀው እውነት! 🚨
በቅርቡ የወጡ አሳዛኝ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በትግራይ ወጣቶች እና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለው ሰቆቃ እጅግ አሳሳቢ እና ልብ የሚሰብር ደረጃ ላይ ደርሷል።
🛑 በግዴታ ወደ ጦርነት፡ ምንም የማያውቁ ወጣቶች እና ህፃናት ለጦርነት ሲባል በግዴታ እየታፈኑ ወደ ግጭት ቀጣናዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።
🛑 ህገ-ወጥ የሰው ዝውውር ለውጭ ምንዛሬ፡ ከዚህም ባሰ እና እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ፣ ወጣቶቹን ለውጭ ምንዛሬ (ዶላር) ሲባል ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን እየሸጧቸው መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህ የህፃናት እና ወጣቶች ሰቆቃ በአፋጣኝ ሊቆም እና ሁሉም ሊያወግዘው የሚገባ ድርጊት ነው!
🗣 ይህንን አሳዛኝ ክስተት እንዴት ይመለከቱታል? ሀሳባችሁን በኮመንት አስቀምጡ!
🔄 መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ድምጽ እንሁን!
02/06/2026
▪በዚህ ምስል ላይ እንደምንመለከተው ፤ በገጠራማው የአፋር ክልል የምርጫ ኮሮጆዎችን በግመል ጭኖ በበረሃማው መንገድ ሲጓዝ የምናየው ትዕይንት፣ ከአንድ ተራ ፎቶግራፍ የዘለለ እጅግ ጥልቅ የሆነ መልዕክት አለው። 🗳️
ይህ ምስል የነቃ ማህበረሰብን፣ ጽናትን እና የሀገር ፍቅርን በአንድ ላይ አጠቃልሎ የያዘ ህያው ማሳያ ነው።🗳️
ስለ አፋር ህዝብ ስናወራ ማስታወስ እና ማድነቅ የሚገባን በርካታ እውነታዎች አሉ...
የአፋርን ህዝብ ድምፁን ከመስጠት እና መፃኢ እጣፈንታውን ከመወሰን አላገደውም።
ዘመናዊውን የምርጫ ስርአት ከነባሩ የኑሮ ዘይቤው (ከግመል ጉዞ) ጋር አዋህዶ መብቱን ሲያስከብር ማየት፣ ማህበረሰቡ ምን ያህል ለዴሞክራሲያዊ መብቱ ቁርጠኛ እና የነቃ መሆኑን ይመሰክራል።
አፋር ከጥንት ጀምሮ የራሱ የሆነ የዳበረ የማህበራዊ አስተዳደር እና የፍትህ ስርአት ያለው ስልጡን ማህበረሰብ ነው። ባህላዊው የፍትህ እና አስተዳደር ስርአት (ማዳዓ) ዛሬም ድረስ ማህበረሰቡን በሰላም፣ በፍትህ እና በእኩልነት የሚያስተዳድር የረቀቀ የጥበብ ማሳያ ነው።🗳️
ምስሉ ላይ ያለው አባት የምርጫ ኮሮጆዎቹን በግመል ጭኖ መሳሪያውን አንግቦ በኩራት ሲጓዝ ማየት፣ የአፋር ህዝብ ለሀገሩም ሆነ ለመብቱ ዘብ የሚቆም ጀግና መሆኑን ያሳያል።
ተፈጥሮ የፈተነችውን አካባቢ በፅናት ተቋቁሞ፣ ከዘመኑ ጋር እኩል እየተራመደ ያለ ድንቅ ህዝብ ነው። 🗳️
ባጠቃላይ ይህ ምስል ትልቅ ትርጉም አለው። የአፋር ህዝብ ትዕግስቱ፣ እንግዳ ተቀባይነቱ፣ ባህሉን አክባሪነቱ እና ለሀገር ያለው ጥልቅ ፍቅር ሁሌም የሚያስደንቅ ነው።
የጥንት እሴቶቹን ሳይለቅ፣ የዘመናዊነትን እና የዴሞክራሲን ጎዳና በራሱ መንገድ እየተጓዘበት መሆኑ ክብር ይገባዋል።
ክብር ለዚህ ታላቅ፣ ስልጡን እና የነቃ ማህበረሰብ!
Like Share Repost 🙏
Via Abdulfetah Mohammed
#አፋር #ኢትዮጵያ #ምርጫ #ዴሞክራሲ #ስልጣኔ
Klicken Sie hier, um Ihren Gesponserten Eintrag zu erhalten.