Tikus Neger

Tikus Neger

Share

Tikus N***r features the latest celebrity news, untold life stories, musician biographies, relations

09/21/2026

ዜጋን የሚያማርር የተቋማት የገንዘብ ስብሰባ በእውነት ለሀገር ውድቀት ትልቁ ሚና ይጫወታል። ዛሬ በጉልበት ይወሰዳል ነገ ህዝብ የበቃው ቀን ህ! በተለይ በስራው ላይ እንዲህ ቅጥ ያሳጣችሁ

09/19/2026

ይሄ ጉዳይ በፊት ይደረግ ነበረ አሁን እንደገና በአዲስ መልክ መጥቷልና ተጠንቀቁ።

09/14/2026

ተጠንቀቁ! ዲጂታል ሌብነት ብዙዎች ተታለውበታል።

09/11/2026

ውድ ቤተሰቦቼ! መጪው አመት ያሰብነውን የምናሳከበት፣ ጤናና ሰላሙን ከፍቅር ጋር የምንላበስበት እንዲሁም አገራችን ላይ ሰላሟ በዝቶ የምናይበት ዘመን ያድርግልን! መልካም አዲስ አመት!

www.youtube.com 09/10/2026

ውድ ቤተሰቦቼ መልካም አዲስ አመት እየተመኘሁላችሁ እቺን ሙዚቃ ጋብዣቹሀለው። ሃሳባችሁን ግለጹባት።

www.youtube.com

09/10/2026

አይ ሱስ ይሄን ምን ትሉታላችሁ!

09/09/2026

በአል ደርሷል እባካችሁ እራሳችሁን ከሌቦች ከአጭበርባሪዎች ጠብቁ አመጣጣቸው አይታወቅም። #ለጥንቃቄ #ተጠንቀቁ

09/08/2026

እውነት ይሄ ነገር ስንቶቻችሁ ገጥሟቹኋል? በእውነት ህዝብ የሚበዛበት የመንግስት አካባቢ እንደዚህ አይነት አይን ያፈጠጠ ነገር ተገቢ ነው?

09/05/2026

በባህር ዳር ከተማ ሰዎችን በማገት የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላትና የመንግስት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በባህር ዳር ከተማ በሰዎች ላይ እገታ በመፈፀም፣ ገንዘብ በመጠየቅና በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላትና ለወንጀሉ መፈፀሚያነት የዋለ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪውቹ ታጋቾቹን አፍነው በመውሰድ ለ11 ቀናት አግተው ያቆዩዋቸው ሲሆን፤ በወቅቱ ታጋቾቹን ለመልቀቅ 3 ሚሊዮን 370 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው በመጠየቅና ገንዘቡ ከተከፈላቸው በኋላ እንዲለቀቁ ማድረጋቸውን የምርመራ መረጃው ያመላክታል።
የመምሪያው የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ አዛዥ ኮማንደር መኳንንት አድማስ እንደገለጹት ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 (ኤፍራታ) አካባቢ ነዋሪና ነጋዴ የሆኑ ሶስት ግለሰቦች በራሳቸው ተሽከርካሪ ወደ ስራ ቦታቸው በመሄድ ላይ እያሉ በወቅቱ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት እገታ ተፈፅሞባቸዋል ብለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ታጋቾቹን በመንግስት ተሽከርካሪ አፍነው በመውሰድ ለ11 ቀናት አግተው ማቆየታቸውን ያስረዱት ኮማንደር መኳንንት የወንጀሉ አደራጆች እና ተሳታፊዎች በቅንጅት የሰሩ መሆኑን አክለው አስታውቀዋል።
በተደረገው ጥብቅ ክትትልም 1ኛ. ወንጀሉን በዋናነት ያስተባበረው አብርሃም ጫኔ የተባለ በቀበሌ 06 የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ባለቤት፤
2ኛ. ተሽከርካሪን ለወንጀል ያዋለ መለሰ ጌትነት የተባለ አሽከርካሪ ግለሰብ፤
3ኛ. ታጋቾቹን ደብቆ ያቆየውና ወንጀሉን የሸፈነው በቀበሌ 14 እንዘግድብ አካባቢ የሚገኝ ህንፃ አስተዳዳሪ (170 ሺህ ብር ክፍያ በመቀበል ወንጀሉን ያደባበሰ)፤
4ኛ. አበበ ጌቴ፣ ከአዲስ አበባ የተሳተፈ ተባባሪን ጨምሮ እስከ 870 ሺህ ብር በባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ ረገድ የተሳተፉ አባላት፤ በአጠቃላይ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ኮማንደር መኳንንት ያስታወቁት።
በተጨማሪም ለወንጀሉ ማስፈፀሚያነት የዋሉ አንድ ማካሮቭ እና አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች ከነተሽከርካሪው መያዛቸውን ገልጸዋል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ተቋማት ለስራ የተመደቡላቸውን ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባ ያሳሰበ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ቀሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚያስችል ጥብቅ የምርመራ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።

09/03/2026

የሰባት ዓመቷን ህፃን ፊዮና ሰለሞንን ከአዲስ አበባ አግታ ወደ ጎንደር ከተማ በመውሰድ ከፍተኛ የገንዘብ ካሳ የጠየቀችው የቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ውላለች።
ተጠርጣሪዋ ወጣት መቅደስ ሞገስ በአዲስ አበባ ውስጥ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት የሰራችውን አሰቃቂ አጋጣሚ በመጠቀም ህፃኗን ይዛ በመሰወር ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ ተጓዘች። የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ እንደገለጹት፣ ተጠርጣሪዋ ህፃኗን ይዛ ማራኪ ክፍለ ከተማ ከሚገኘው የዩኒቨርሲቲው አጠገብ ባለው ጫካ ውስጥ ተሸሽጋ ሳለ በፖሊስ አባላት በደረሰበት ጥብቅ ክትትል እና ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ልትያዝ ችላለች።
መቅደስ ወንጀሉን የፈጸመችው ለጊዜው ካልተያዘው ግርማ ወንድአሁን ከተባለው የአክስቷ ልጅ ጋር በመተባበር እንደሆነ ታውቋል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለህፃኗ ቤተሰቦች ስልክ በመደወል 3 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን፣ አስቀድመውም ከ370 ሺህ ብር በላይ ተቀብለው እንደነበር ኮማንደሩ አጋልጠዋል።
ህፃን ፊዮና በሰላም ወደ ቤተሰቦቿ እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን፣ ፖሊስ አሁንም የተሰወረውን ግርማ ወንድአሁንን እና ሌሎች ከጉዳዩ ጋር እጃቸው ያለበትን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል አጠናክሮ የቀጠለውን ብርቱ አደን ቀጥሏል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Toronto?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Toronto, ON