Gojjam Media

Gojjam Media

Share

ሃገራዊ እና አለምአቀፋዊ ወቅታዊና ጠቃሚ መረጃዎችን ፡ የጎጃምንና የሌሎችን ባህልና ወግ ፡ ታሪካዊ ቦታዎችን የምናቀርብበት ገፅ ነው 🙏

08/21/2026

👍

Photos from Gojjam Media's post 08/21/2026

አፋር ክልል እያመረተ ነው

08/18/2026

ታቦር በዓል አደረሳችሁ 🙏

08/16/2026

"እኔ የሚያሳዝነኝ -----?

08/16/2026

የእለት እንጀራችንን ባርክልን 🙏

08/15/2026

ከቪየትናም የመጣው ያማረ ምስል !
🇪🇹❤️🇪🇷

በቪየትናም በሚካሄደው ሚስ ወርልድ (Miss World 2026) ውድድር ላይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ተወካዮች ያሳዩት አብሮነት እና ፍቅር የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

አሁንም በሂደት ላይ ያለው ይህ ታላቅ የዓለም አቀፍ ውድድር መስከረም 05/2026 (September 05, 2026) የመጨረሻ አሸናፊውን የሚያስታውቅ ይሆናል።

ሀገሮቻቸውን ወክለው በዓለም አቀፍ መድረክ ለተገኙት ለሁለቱም ቆንጆዎቻችን ታላቅ ስኬትንና መልካም እድልን እንመኛለን!

Via ጉርሻ page

08/15/2026

የእናትነት ህይወት 😘

Photos from Gojjam Media's post 08/15/2026

የምስራች ለኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰብ

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የካፍ (CAF) መስፈርቶችን አሟላ ።

ለበርካታ ዓመታት የኢንተርናሽናል ውድድሮች እገዳ ተጥሎበት የቆየው የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ በተደረገለት ሰፊና ዘመናዊ የሁለተኛ ምዕራፍ የማሻሻያና የግንባታ ሥራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) መስፈርቶችን በማሟላት ለዓለም አቀፍ ውድድሮች ዝግጁ መሆኑን የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ መልካሙ ጸጋዬ ገለፁ።

ይህ ትልቅ የስፖርት ስኬት የሀገራችን ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና ክለቦቻችን በሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት የመጫወት ዕድላቸውን በጥንካሬ የሚመልስ ከመሆኑም በላይ፣ ኢትዮጵያ ወደፊት አበይት የአህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የምታደርገውን ጉዞ እንደሚያፋጥነው ቢሮ ኃላፊው አረጋግጠዋል።

ይህ የስፖርት ቱሪዝሙን ከፍ እንደሚያደርገው አያጠራጥርም።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን❗

Via Visit Amhara

08/14/2026

"ስልካችን ካርድ ሲያልቅ እና ስንደውል ''ያለዎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ነው እባክዎን ሂሳቦን ይምሉ "
።
የምትለው ሴት ይህቺ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እንደሆነች ስንቶታችሁ ታውቃላችሁ ? ስሟም ህሊና ተፈራ ትባላለች።

Photos from Gojjam Media's post 08/14/2026

በአማራ ክልል እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ ትምህርት ቤት የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።
እውቀት፣ እምነትና ሙያ በአንድ ጣሪያ ስር፦ በዙይ ሃሙሲት ከተማ እየተገነባ ያለው ግዙፉ የልማት ፕሮጀክት

ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከሚሰራቸው የልማት ስራዎች አንዱ የሆነው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ዙይ ሃሙሲት ከተማ የሚገነቡ ትምህርት ቤት (ዓለማዊ እና መንፈሳዊ) እና ክሊኒክ እናስቃኛችሁ።

ከገዳሙ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በዙይ ሃሙሲት ከተማ ገዳሙ መንፈሳዊና ዓለማዊ እውቀትን፣ ሙያዊ ክህሎትን እንዲሁም ማህበራዊ አገልግሎትን ያስተሳሰረ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክት በከፍተኛ እንቅስቃሴ እየሰራ ይገኛል።

​በ30 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት እንቃኘው።

​📍ዘመናዊና የአብነት ትምህርት ቤቶች
​የፕሮጀክቱ ዋነኛ አላማ «በሁለት ቢላዋ የተሳለ» ማለትም በዓለማዊ እውቀቱ የበቃ፣ በመንፈሳዊ ባህሉና ግብረ-ገብነቱ የበለፀገ ትውልድ ማፍራት መሆኑ ተገልጿል።

​በአካባቢው ያለውን ከፍተኛ የትምህርት ጥራት ክፍተት የሚሞላና በአዲስ አበባ ከሚገኙ ዝነኛ ትምህርት ቤቶች የሚያሳዩትን የዲሲፕሊንና የእውቀት ጥራት የሚደግም ይሆናል የተባለለት በአንድ ክፍል ከ20 እስከ 25 ተማሪዎች ብቻ በመመደብ የመምህርና የተማሪን ጥብቅ ግንኙነት እንደሚያረጋግጥ የተነገረለት ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምር ዓለማዊ ትምህርት ቤት እየተገነባ ይገኛል።

ትምህርት ቤቱ​ የኮምፒውተር፣ የኬሚስትሪ ላቦራቶሪዎችና ዘመናዊ ቤተ-መጻሕፍት የተካተቱበት ሲሆን፣ የተማሪዎችን ልዩ ልዩ ተሰጥኦ ለማልማት የሚያስችል የስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳ ተዘጋጅቶለታል።

ሌላኛው እየተገነባ ያለው ​ጂ+3 የአብነት ትምህርት ቤት ሲሆን ተማሪዎች የአብነት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ጎን ለጎን ዓለማዊ ትምህርትን መማር ግዴታ አድርጎ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል።

ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ የሆኑ ጉባኤ ቤቶች፣ የተማሪዎችና የአባቶች ማደሪያ፣ መመገቢያ አዳራሽና የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ተዘጋጅቷል።

​«የአብንት ተማሪዎች ነፃ ምግብ፣ አልባሳትና ማደሪያ የሚያገኙ ሲሆን፤ በትምህርት ገበታቸው ወቅትም ለግል ፍላጎቶቻቸው ማሟያ የሚሆን የኪስ ገንዘብ የሚያገኙበት የምርትና የልማት ስራዎች ተመቻችተውላቸዋል።»

​ሌላኛው ለዘላቂ ገቢ፣ የክህሎት ማዳበሪያና የማምረቻ መጋዘኖች ግንባታዎች ሲሆኑ ​የአብነት ተማሪዎችም ሆኑ ሌሎች ሰልጣኞች ከትምህርት በኋላ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ እራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ የሚያስችሉ ተግባራዊ የሙያ ማሰልጠኛዎችና ማምረቻዎች በሳይቱ እየተገነቡ ይገኛሉ።

​የምግብ ማቀነባበሪያ፦ የኑግ፣ የሱፍ፣ የአቮካዶ ዘይቶችን ማቀነባበር፤ የጤፍ፣ የበቆሎና የስንዴ ምርቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ማቅረብ።
​የንፅህና ውጤቶች ማምረቻ፦ ደረቅና ፈሳሽ ሳሙናዎችን በማምረት ለጎንደር፣ ባህር ዳርና አካባቢው ከተሞች ማቅረብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል።

📍የ​ጤና ተቋም
ሁለተኛው ፕሮጀክት የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት (መካከለኛ ደረጃ ክሊኒክ) ግንባታ ሲሆን ​የአካባቢው ህብረተሰብ ወደ ባህር ዳር ወይም ጎንደር ሳይሄድ እዚያው የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ ታስቦ መካከለኛ ደረጃ ክሊኒክ እየተገነባ ይገኛል። ክሊኒኩ እንደ ኤክስሬይ፣ ኢሲጂ፣ ኢኢጂ እና አልትራሳውንድ ያሉ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች የተሟሉለት ይሆናል ተብሏል።

​የፕሮጀክቱ ማኔጀር አቶ ዳኜ የኋሌ እንደገለጹት፣ ፕሮጀክቱ ታህሳስ 1፣ 2018 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ፈጣን እድገት በማሳየት ላይ ይገኛል፣​የዓለማዊ ትምህርት ቤት ብሎኮች ስራዎች አልቀው ግንባታቸው 85% ደርሷል። 6 ብሎኮችና 24 ክፍሎች ያሉት ሲሆን የማጠናቀቂያ (Finishing) ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

​የአብነት ትምህርት ቤት የጂ+3 ህንፃ የመጨረሻው ፎቅ የኮንክሪት ድልድል ስራ እየተሰራ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የራሱ የውሃ ሪዘርቫየርና የሮቶ ማከማቻዎች የተገነቡ ሲሆን፣ የብረትና የእንጨት ስራዎች በራሱ የውስጥ አቅም እየተከናወኑ ይገኛሉ።

​የማጠናቀቂያ ጊዜ የቁሳቁስና የመንገድ እንቅፋቶች በተሻለ ሁኔታ ከተቀረፉ ፕሮጀክቱ ግንቦት 2019 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ሲሆን፣ ረዘመ ከተባለ ደግሞ አጠቃላይ ማጠናቀቂያው እስከ ጥር 2020 ዓ.ም እንደሚሆን ተገልጿል።

በቀጣይ ክፍል ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም በዙይ ሃሙሲት ከተማ እየሰራ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ የምናስቃኛችሁ ይሆናል።

📌 በገዳሙ የተሰሩ ስራዎችን ለማንበብ ሊንክ
https://www.facebook.com/share/p/1LN517GaiB/

Want your business to be the top-listed Media Company in Toronto?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Toronto, ON

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gojjam Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Toronto.