ZaB
Education, entertainment, and other political and political free information are shared via this page
20/09/2026
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2022 የክብር ዶክትሬት የሰጣቸው የኢትዮጵያዊያን ባለውለታ ! ...
ከጊቤ 1 እስከ ጊቤ3 ግድቦች ላይ የተሳተፉት የ 'we build ' ስራ አስፈፃሚው ፔትሮ ሳሊኒ ምዕራባዊያን ማዕቀብ በጣሉብን ወቅት እንኳን ወደኋላ ሳይሉ በፅናት የህዳሴ ግድባችንን የገነቡ ጀግና ናቸው፡፡ እናመሠግናለን!
ZaB like and follows for more
09/09/2026
የአሜሪካ ዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት (USCIS) በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ቢሮውን ነገ ይከፍታል።
ቢሮው ከነገ ጀምሮ ሥራ የሚጀምር ሲሆን በኢትዮጵያ ከUSCIS ጋር የተያያዙ የኢሚግሬሽን ጉዳዮችን ይመለከታል።
በቢሮው በኩል የውጭ ሀገር ሰነዶች ትክክለኛነት ማረጋገጥ፣ የማጭበርበር ጥርጣሬዎችን መመርመር እና የቤተሰብ ዝምድናን ለማረጋገጥ የDNA ምርመራ ናሙና መሰብሰብ ይከናወናል።
USCIS እንዳለው፣ እስካሁን እነዚህ ሥራዎች በአብዛኛው ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጋር በመተባበር ይከናወኑ ነበር። አዲሱ ቢሮ ግን USCIS እነዚህን ሂደቶች በቀጥታ በኢትዮጵያ እንዲያከናውን ያስችለዋል።
ነገር ግን ይህ ማለት በማህበራዊ ሚዲያ እንደሚነዛው " የአሜሪካ ቪዛ ማግኘት ቀላል ሆኗል " ማለት አይደለም።
አዲሱ የUSCIS ቢሮ በዋናነት የሰነድ ማረጋገጫ፣ የማጭበርበር ምርመራ እና የቤተሰብ ዝምድና ማረጋገጫን ጨምሮ የኢሚግሬሽን ሂደቶችን ለመደገፍ ነው።
ቢሮው የቪዛ መስጫ ቢሮ አይደለም፤ የቪዛ ማመልከቻና ውሳኔ ሂደትም ከዚህ በተለየ የአሜሪካ የቆንስላ ሥርዓት ውስጥ ይቀጥላል።
እንዲሁም የUSCIS አዲሱ ቢሮ አገልግሎቶችን በቀጠሮ ብቻ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ/ም
ZaB like and follow for more
28/08/2026
የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ከሚኒስቴሩ ምደባ ውጭ መቀበል ተከለከለ፡፡
ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈዉ ደብዳቤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን እኔ በምደባ ሳልሰጣችሁ አዛውራችሁ ማስተማር አትችሉም ሲል ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ሚኒስቴሩ በምክንያትነት የገለጸዉ ደግሞ ተማሪዎች ኢትዮጵያን የበለጠ እንዲያውቁ እና ብዝኃነትን እንዲገነዘቡ የሚያስችለዉን ሥርዐት እየሸረሸሩ መኾናቸውን ነው፡፡
ZaB like and follow for more
መነጋገሪያ የሆነው በህንድ አንድ ት/ቤት የተከሰተው ክስተት
በህንድ ሀገር በአንድ የግል ትምህርት ቤት የ6 ዓመት ህፃን በመምህሩ በጥፊ ከተመታ በኋላ ህይወቱ አልፏል።
ክስተቱ በትምህርት ቤቱ የክፍል ውስጥ የደኅንነት ካሜራ ተቀርጾ ወጥቷል።
መምህርቷ ህጻኑን " የቤት ስራ አልሰራህም " በማለት በጥፊ እንደመታችው ተገልጿል።
በደህንነት ካሜራው ላይ እንደታየው ህፃኑ በመምህሩ በጥፊ ከመመታቱ በፊት ፣ በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ሆኖ ሲንቀጠቀጥና መምህሩን ሲለምን ነበር። በኋላ በጥፊ ከተመታ በኋላ ተዝለፍልፎ መምህርቷ ላይ ወድቋል።
በሰዓቱ ርብርብ ተደርጎ ወደ ጤና ተቋም ቢወሰድም ህይወቱ ግን ሊተርፍ አልቻለም።
የህጻኑ ሞት ትክክለኛ ምክንያትና በመምህሩ ድርጊት እና በህፃኑ ሞት መካከል ያለው ቀጥተኛ ግንኙነት በምርመራ እየተጣራ መኑን የህንድ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ክስተቱ በትምህርት ቤቶች ህፃናትን ከአካላዊ ቅጣት መጠበቅና የተማሪዎችን ደኅንነት ማረጋገጥ ላይ ጥያቄ ያስነሳና ዓለም አቀፋዊ መነጋገሪያ የሆነ ነው።
ZaB
🇪🇸 🇪🇺
ሞሮኮ እና ስፔንን በሚያዋስነው የስፔን፣ ሴውታ ድንበር በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ድንበሩን ጥሰው አውሮፓ ገብተዋል።
በተፈጠረው ክስተት 18 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። አብዛኞቹ በባሕር ሲሻገሩ ሰጥመው የሞቱ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በድንበሩ ላይ በተፈጠረ መጨናነቅ ህይወታቸው አልፏል።
የስፔን ባለሥልጣናት እንዳሉት፣ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 49,000 ያህል ስደተኞች ከሞሮኮ ወደ ሴውታ በባሕርና በየብስ ገብተዋል። ይህ ቁጥር 85,000 ሕዝብ ብቻ ካላት ሴውታ ከተማ ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሚደርስ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ከታዩት ትልቁ የአንድ ቀን የስደተኞች ፍሰት እንደሆነ ተገልጿል።
ሴውታ እና ሜሊያ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ የስፔን ግዛቶች ሲሆኑ ወደ እነዚህ ሥፍራዎች መድረስ ማለት ወደ ስፔንና ወደ አውሮፓ ህብረት ግዛት መግባት ማለት ነው።
የስፔን መንግሥት ሕጋዊ ሂደቱን በመከተል ስደተኞቹን በተቻለ ፍጥነት ወደ ሞሮኮ ለመመለስ እየሠራ መሆኑን ገልጿል። እንዲሁም ለድንበሩ ጥበቃ 60 ተጨማሪ ወታደሮችን መላኩ ተሰምቷል።
ቪድዮ ፦ ከማሕበራዊ ሚዲያ
ZaB like and follow for more