DeritaTech Solution
DeritaTech Solution is a Technology page providing IT tips, Tricks and How to videos.Follow us.
30/09/2026
ምርጥ 12 የጉግል አማራጭ Search Engines
1. https://Search.aol.com
2. https://search.brave.com
3. https://duckduckgo.com
4. https://Startpage.com
5. https://ecosia.org
6. https://bing.com
7. https://www.qwant.com/
8. https://Mojeek.com
9. https://swisscows.com
10.https://search.yahoo.com
11. https://ask.com
12. https://kagi.com/
20/09/2026
Steganography ምንድን ነው?
Steganography ማለት መልዕክቶችን በሌሎች መልዕክቶች ውስጥ መደበቅ ሲሆን ፤
ስናያቸው ተራ በሚመስሉ ና ሚስጥራዊነት በሌላቸው ፋይሎች ወይም መልዕክቶች ውስጥ ሚሰጥራዊ መረጃዎችን መደበቅ የሚያስችል
የመረጃ ደህንነት ቴክኖሎጂ ነው።
በSteganography Technique ማንኛውንም ዲጂታል መረጃ በሌሎች መረጃዎች ውስጥ መደበቅ ይቻላል ለምሳሌ:የተለያዩ ቴክስቶችን ፣ሊንኮች፣ PDF ፣ ምስሎችን ፣ ቪዲዩ ፣ ኦዲዮ ና ሌሎችም ዲጂታል መረጃዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
በግልጽ እንዲታዩ ያልተፈለጉ መልዕክቶችን በዚህ ቴክኒክ በምስሎች ውስጥ ፣ ፋይሎች ውስጥ ፣ Video ውስጥ እንዲሁም በሌሎች መልዕክቶች ውስጥ በመሸሸግ ወደ ታለመላቸው ቦታ እንዲደርሱ ማድረግ ይቻላል። በዚህ መልኩ የተደበቁ መልዕክቶች ይፋ የሚሆኑት የታለመላቸው ቦታ ሲደርሱ ወይም መዳረሻቸው ላይ ነው።
🖼 Image Steganography ፡ መረጃን በምስል ውስጥ መደበቅ። በጣም የተለመደው ነው።
🎵 Audio Steganography ፡ መረጃን በMP3 ፣ WAV ወዘተ የድምጽ ፋይል ውስጥ መደበቅ።
🎬 Video Steganography ፡ በቪዲዮ ውስጥ መረጃ መደበቅ። ቪዲዮ ብዙ ፍሬሞች ስላሉት ከአንድ ምስል የበለጠ መረጃ ሊይዝ ይችላል።
📄 Document Steganography ፦ በሰነዶች ውስጥ በspacing፣ formatting ወይም በሌሎች ባህሪያት መረጃ መደበቅ።
🌐 Network Steganography ፦ በNetwork Traffic ውስጥ መረጃን መደበቅ።
ለምሳሌ ፡ አንድ የተለመደ የJPG ምስል እንደ መደበኛ ፎቶ ከላይ ቢታይም በውስጡ የተደበቀ ጽሑፍ ወይም ፋይል ሊኖር ይችላል።
Steganographyን የት ልንጠቀምበት እንችላለን?
Steganographyን ለተለያዩ አላማዎች ልንጠቀምበት እንችላለን ለምሳሌ ፡ ለግል መረጃ ጥበቃ ፣ ለDigital Watermarking ፤ ጎጂ በሆነ መልኩ ደግሞ ለሳይበር ወንጀል ወይም ጥቃት ለማድረስ ፤ ለምሳሌ ፡ ሃከሮች ጎጂ መረጃዎችን በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ፋይሎች ውስጥ በመደበቅ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ ።
እንዴት ማዘጋጀት እንችላለን ?
Steganography ምስልም ይሁን ሌሎች የStego አይንቶችን ለማዘጋጀት እንዲሁም የተላከልንን ምስል በዚህ ቴክኖሎጂ የተደበቀ መልዕክት እንዳለው ወይም እንደሌለው ለማወቅ ለዚህ አላማ የተዘጋጁ Software /tool ያስፈልገናል። ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ በቪዲዮ አስደግፈን እናቀርብላችኋለን !
19/09/2026
ለኮምፒውተር ና ኮምፒውተር ሳይንስ አሻራቸውን ያኖሩ ሰዎች!
🎯 1. Charles Babbage
በ1837 Analytical Engine የተሰኘ የዘመናዊ ኮምፒውተሮች ሙሉ ባህሪ የነበረው የመጀመሪያውን የሜካኒካል ኮምፒውተር የፈጠረ ሲሆን ይህ ሰው "Father of the computer" በመባል ይታወቃል።
✅ 2. Ada Lovelace
Babbage የሰራው analytical engine ፕሮግራም የተጻፈው በAda lovelace ሲሆን የመጀመርያዋ ፕሮግራመር (First computer programmer) በመባልም ትታወቃለች ።
📌 3. Alan Turing
ቱሪንግ ማሽን/Turing Machine የተሰኘውን የሂሳብ ሞዴል አስተዋወቀ። ይህ ሞዴል ማንኛውንም አልጎሪዝም እና የኮምፒውተር ስሌት በሎጂክ መስራት እንደሚቻል ያሳየ ነው።
🖥 4. John von Neumann
እስከዛሬ የምንጠቀምበትን መደበኛ የኮምፒውተር Architecture ነድፏል። ይህ አወቃቀር የፕሮግራም መመሪያዎችንም ሆነ መረጃዎችን በአንድ ዓይነት ማህደረ ትውስታ (memory) ውስጥ ማስቀመጥ ያስችላል ።
🔑 5. Claude Shannon
መረጃን ለመለካት ቢት (Bit - Binary Digit) የተሰኘውን መለኪያ አስተዋወቀ። ይህም ማንኛውንም መረጃ (ጽሁፍ፣ ድምፅ፣ ምስል) ወደ 0 እና 1 ቀይሮ ማስተላለፍ እንደሚቻል ና የቡልያን አልጀብራን (Boolean Algebra) ከኤሌክትሪክ ስዊቾች ጋር በማገናኘት የዲጂታል ኮምፒውተር ሰርኪዩቶችን መስራት እንደሚቻልም አሳይቷል ።
🗝 6. Grace Hopper
የመጀመሪያውን Source code compiler የፈጠረ ና COBOL/Common Business-Oriented Language በመባል የሚጠራውን የኮምፒውተር ቋንቋ የፈጠረ።
🎯 7. Dennis Ritchie
Ken Thompson ተሰኘ ጓደኛው ጋር በመሆን Unix Operating System እና C Programing languageን የበለጸገ።
🌎 8. Vint Cerf
ኮምፒውተሮች እና የተለያዩ መሳሪያዎች በኢንተርኔት እና በግል አውታረ መረቦች (private networks) አማካኝነት እርስ በርስ እንዲገናኙ እንዲሁም መረጃ እንዲለዋወጡ የሚያስችል መሰረታዊ የግንኙነት ህጎች (TCP/IP)ን ከRobert Kahn ጋር በመሆን የፈጠረ ። The fathers of the Internet የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል።
🌍 9. Tim Berners-Lee
WWW/world wide webን ለአለም ያስተዋወቀ።
🎯10. Linus Torvalds
ለበርካታ Linux distributions (Linux Operating Systems) መፈጠር መነሻ የሆነውን የLinux Operating System መዓከላዊ ክፍል / Linux Operating System Kernelን የፈጠረ።
11/09/2026
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፤
🌻🌻እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
አዲሱ ዓመት የጤና ፣ የደስታ ፣ የሰላም ና ስኬት ይሆንላችሁ ዘንድ ከልብ እንመኛለን!🌻🌻
10/09/2026
እንቁጣጣሽ ሎተሪን ለቆረጣችሁ ! ዕጣው ወጥቷል ፤ 20 ሚሊየን ብር የሚያስገኘው የአንደኛው ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 2302203 ሆኗል። ሙሉ ማውጫውን ይመልከቱ! መልካም ዕድል!
07/09/2026
አዲስ ኮምፒውተር ከገዛን በኋላ አስፈላጊ ሶፍትዌሮችን ፈልገን መጫን በጣም አድካሚም ና አሰልቺም ነው ፤ መጫን የፈለግናቸው ሶፍትዌሮችም በአንድ ቦታ ላይገኙ ይችላሉ ፤ እያንዳንዱን አፕሊኬሽንም በተናጠል መጫን ይኖርብናል ፤ ለዚህ መፍትሄ ከፈለጉ https://ninite.comን ይጠቀሙበት! Ninite ካሉት በርካታ መሰረታዊ የሚባሉ መተግበሪያዎች መካከል የፈለግነውን መርጠን በአንዴ መጫን ያስችለናል ፤ ይሞክሩት!
06/09/2026
ለሁሉም ሰው እጅግ ጠቃሚ ድረገጾች !
1. realworkfromanywhere.com
በመረጡት የስራ መስክ ያለ ምንም የlocation ገደብ ከየትም ሆነው online በpart time ወይም በfulltime ስራ ሊያገኙበት የሚችሉት ወሳኝ ድረገጽ ነው። https://realworkfromanywhere.com ላይ ገብተው ከዕርስዎ ፍላጎ የተስማማ ስራ ይፈልጉ!
2. myfridgefood.com
ይህ በኪችናችን ወይም በፍሪጃችን ውስጥ ያሉንን ነገሮች ወይም food ingredients ከሚሰጠን ዝርዝር ስንመርጥለት ወዲያው ከመረጥንለት ግበዓቶች ምን አይነት ምግብ ልናዘጋጅ እንደምንችል ና ሙሉ የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ / Recipes ይሰጠናል ፤ ሊሎችም በርካታ ፊቸሮች አሉት ። ከዚህ ጋር መሰል አገልግሎት የምናገኝበት https://supercook.com የተሰኘ ድረገጽም መጠቀም እንችላለን ፤ ይሞክሯቸው!
3.remove.bg
የphotoshop እውቀት ሳያስፈልገን የተለያዩ ምስሎችን ፤ ቪዲዮዎችን የbackground ማጥፋት ወይም መቀየር ከፈለግን በሰከንድ የፈለግነውን ፎቶ ወይም ቪዲዮ የጀርባ ምስል በአዲስ መቀየር ወይም ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ያስችለናል። https://remove.bg ላይ ይሞክሩት!
4. tinywow.com/
ይህ ሁሉን በአንድ ያካተተ ና ሁሉንም በአንድ ቦታ online በቀላሉ ማከናወን የሚያስችል ድረገጽ ነው። pdf ላይ የተለያዩ ነገሮችን ማከናወን ቢፈልጉ ፣ ፎቶ ና ቪዲዮ ማቀናበር / edit ማድረግ ቢፈልጉ ፣ AI ቴክስት ጄነሬት ማድረግ ቢፈልጉ ና ሊሎችም ነገሮችን ኦንላይን ማከናወን ቢፈልጉ በቀላሉ ና በነጻ እንዲሁም አካውንት መፍጠር ሳያስፈልግዎ ያስችልዎታል ፤ https://tinywow.comን ይሞክሩት !
5. radio.garden
በዓለም ዙሪያ ያሉ የሬዲዮ ስርጭቶችን እየመረጥን ለመከታተል ያስችለናል። https://radio.garden/ ሙሉ አድራሻው ነው ይሞክሩት!
02/09/2026
iPhone 18 ይፋ የሚደረገበት ቀን ና አዲሱ የApple ስራ አስፈጻሚ!
📌 የSteve Jobsን ህልፈት ተከትሎ አፕል ኩባንያን ከ2011 ጀምሮ ላለፉት 15 ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩት ና የኩባንያውን የገበያ ዋጋ ከነበረበት 350 ቢሊየን ዶላር ገደማ ወደ 4.7 ትሪሊየን ዶላር በላይ ማሳደግ የቻሉት Tim Cook , ዋና ስራ አስፈጻሚነታቸውን የሃርድዌር ክፍል ሃላፊ ለነበሩት ለ**John Ternus** ከመሰከረም 01,2026 ጀምሮ አስረክበዋል።
📌 በአዲሱ ስራ አስፈጻሚ John Ternus መሪነት የዘንድሮው Apple event "Surprise and Shine" በሚል መሪ ቃል September 9, 2026, በአሜሪካ ካሊፎርኒያ Cupertino ከተማ Apple Park በሚገኘው Steve Jobs አዳራሽ ይካሄዳል ፤ በዚሁ አፕል ኢቨንት ላይ iPhone 18 pro ና iPhone 18 pro ስልኮች ይፋ እንደሚደርጉ ተገልጻል!
📌 iPhone 18 Pro በ6.3-inch እና iPhone 18 Pro Max 6.9-inch የScreen ስፋት የሚኖራቸው ሲሆን ፤ በዘንድሮው የአይፎን 18 ማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ ይፋ የሚደረገው ሌላው አዲስ የአፕል ስልክ iPhone / Foldable iPhone (iPhone Fold) ሲሆን ይህ ስልክ 5.5 ኢንች የእስክሪን ስፋት እንደሚኖረው ሲሆን ሲዘረጋ ወደ 7.8 ኢንች ይሰፋል። አዲሱ ታጣፊው የአይፎን ስልክ iPhone Ultra የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 12GB ራም ና ሁለት ባለ 48 ሜጋ ፒክስል ካሜራ ሊኖረው እንደሚችል ተነግሯል።
📌 ሁለቱም ፕሮ ሞዴሎች ትንሹ የራም Capacity 12GB ሲሆን እስቶሬጅ ደግሞ 256GB መሆኑ ታውቋል።
📌 በዋጋ ደረጃ iPhone 18 Pro ከ1,199 እስከ 1299 ዶላር እና Pro Max model በ1399 ዶላር በሆነ ዋጋ ለገበያ ሊቀርብ እንደሚችል ይጠበቃል።
📌 የዘንድሮውን Apple event ልዩ የሚያደርገው iPhone 18 standard model ከፕሮ ና ፕሮ ማክስ ሞዴሎች ጋር ይፋ አይደረግም ይልቁንም እስከ ማርች 2027 ይቆያል ተብሏል።
Facebook : https://Facebook.com/DeritaTech
Telegram : https://t.me/DeritaTech
X : https://x.com/DeritaTech
YouTube : https://YouTube.com/DeritaTechSolution
Blog : https://DeritaTech.BlogSpot.com/
31/08/2026
ለተማሪዎች 5 ጠቃሚ መተግበርያዎች !
1. Goodnotes
Goodnotes ለተማሪዎች የሚሆን ምርጥ የማስታወሻ መያዣ (best note taking ) መተግበሪያ ሲሆን ለሁሉም ተጠቃሚ ሊሆን የሚችል ብዙ ፊቸር ያለው የnote taking app ነው።
Goodnotesን በመጠቀም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ Digital notes ማዘጋጀት እንችላለን።
Pdf ፋይሎችን አፕሎድ አድርገን annotate ማድረግ ያስችለናል።
ወሳኝ የምንላቸውን መረጃዎች highlight ማድረግ ና ኖቶቻችንን የተለያዩ ዲቫይዞች ላይ Sync ማድረግም ያስችለናል።
2. FocusPomo
ይህ አፕ በጥናት ግዜ ትኩረታችን እንዳይሰረቅ Pomodoro የተሰኘውን ዘዴ በመጠቀም ስናጠና distracted እንዳንሆን ይዳናል።
ይመተግበሪያ ለግዜው ለIOS ወይም ለiPhone ተጠበቃሚዎች ብቻ የሚገኝ ነው።
3. Quizlet
Quizlet ተማሪዎች ለፈተና ስንዘጋጅ አጫጭር ኖቶች ለማውጣት ፣ በሌሎች ተማሪዎች የተዘጋጁ የጥናት ስልት ስብስቦችን ለማግኘት ና ጥናታችንን ውጤታማ ለማድረግ የሚረዳን መተግበሪያ ሲሆን ፤ ለመምህራንም የሚረዳ ፊቸር አለው።
Quizlet ለiOS ና ለWindows የሚሆን አፕ ያለው ሲሆን ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች በweb browsers https://Quizlet.com ላይ ገብተን Signup አድርገን መጠቀም እንችላለን።
4. GroupMe
ይህ መተግበሪያ ለኮሌጅ ወይም ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከክፍል ጓደኞቻቸውን ና ከካምፓስ መሃበረሰብ ጋር መረጃ ለመለዋወጥ የሚረዳ ና በክላስ ውስጥ ስለ ፈተና እንዲሁም ስለ አሳይንመንቶች ለመነጋገር ግሩፕ ቻት ማድረግ ያስችላል ።
5. Microsoft OneNote
OneNote ተማሪዎች ሁሉንም የክፍል ማስታወሻዎቻቸውን ለአጠቃቀም ቀላል በሆነ መልኩ ለማደራጀት ይረዳል ፤ OneNoteን በመጠቀም ተማሪዎች የሚይዟቸውን የክላስ ማስታወሻዎች በሰሚስተር ፣ በSubject ና በተለያዩ ቶፒኮች በመከፋፈል ማደራጀት ከማስቻሉም በላይ online ወደ OneDrive Sync ማድረግ ፣ የዕጅ ጽሁፍ ማስገባት ና ሌሎችም በርካታ ፊቸሮች አሉት ።
Facebook : https://facebook.com/DeritaTech
Telegram : https://t.me/DeritaTech
X : https://x.com/Deritatech
Youtube : https://Youtube.com/DeritaTechSolution
| Blog : https://DeritaTech.blogSpot.com/
30/08/2026
ሲምካርድ ስናወጣ የሰጠነውን ወይም ያስመዘገብነውን የግል መረጃችንን ለምሳሌ ፡ ዕድሜ ወይም የልደት ቀን ፣ የስራ ሁኔታ ፣ አድራሻ እና የመሳሰሉትን ማስተካከል ከፈለግን አሁን የግድ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ መዓከላት መሄድ ሳያስፈልገን ካለንበት ሆነን Online ማስተካከል ወይም መቀየር እንችላለን።
ከስልክ ቁጥራችን ጋር የተያያዘ መረጃ በቀላሉ ካለንበት ሆነን ማስተካከል እንድንችል ኢትዮቴሌኮም ሁለት ቀላል አማራጮችን አዘጋጅቶልናል ፤ የመጀመርያው አርዲ ቻትቦትን መጠቀም ነው ፤ ሁለተኛው 994 ላይ በSMS ማንኛውንም መልዕክት በመላክ ከሚመጡልን አማራጮች የግል መረጃ ለማስተካከል (profile management) የሚለውን በመምረጥ ሂደቱን መቀጠል ነው።
ሙሉ መረጃውን ለማየት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ 👉
https://youtu.be/ftvzD4ExuFY
Facebook : https://Facebook.com/DeritaTech
Telegram : https://t.me/DeritaTech
X : https://x.com/DeritaTech
YouTube : https://Youtube.com/DeritaTechSolution
Blog : https://DeritaTech.BlogSpot.com/
Category
Contact the business
Website
Address
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when DeritaTech Solution posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.