ETHIO MEDIA

ETHIO MEDIA

Share

media and company

04/09/2026
04/09/2026

በአብይ አህመድ የስልጣን ዘመን የአማራ ገበሬ ባይተዋርነት

17/08/2026

በሁሉ ነገራችን ስይጣንን አስንቀናል በርግጥ ሰይጣን ራሱ በእኛ ስራ የሚያፍር ይመስለኛል! ጭካኔን ተላመድነው!

16/08/2026

With Manchester United – I just got recognized as one of their top fans!

16/08/2026

''በአበሽጌ የተፈጸመው ግድያ ቀይሽብርን የሚስተካከል ነው! መሰል ግፍን በቃ ለማለትና እንዳይደገም ለአንድ ቀን እናስባቸው ''

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰጠ መግለጫ

ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ፣ ናቻ ቁሊት ቀበሌ ሦስት ወጣቶች በማንነታቸው ተመርጠውና ከሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ላይ እንዲወርዱ ተደርገው "ፋኖ ናችሁ" በሚል ሰበብ ታሪክ እንደሚያወሳን በቀይ ሽብር ዘመን ሲደረግ ከነበረውም በላይ እጅግ ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ግድያ መፈጸሙን አረጋግጠናል።

ከአካባቢው ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት የጭካኔውን ወደር የለሽነት የሚያረጋግጠው ዘግናኙን ድርጊት ፈጻሚው የፀጥታ አካል ከገደላቸውም በኋላ አስከሬናቸውን የቀብር አፈር እንዳይቀምስ በመከልከሉ በአውሬ እንዲበላ መደረጉንም ሰምተናል።

ከግፍ ሰለባዎቹ አንዱ የሆነው ይታገሱ አሰግደው ከዚህ ቀደም ወንድሙ ከሐዋሳ ተይዞ በተመሳሳይ እንዲረሸን ተደርጓል። ይህም ግድያው ቤተሰብንና ማንነትን ማዕከል ያደረገ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው ይላሉ የአካባቢው ምንጮች።

በተመሳሳይ ከወር በፊት ግዛቸው ግርማ የተባለ ሌላ ወጣት በዚያው በአበሽጌ ወረዳ፣ ዳርጌ ቀበሌ በዘፈቀዳዊ መንገድ ተረሽኗል። ወጣቱ ሥራ ፈጣሪና ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል የከፈተ ብሎም በአካባቢው እጅግ ምሥጉን ነበር።

የዞኑም ሆነ ወረዳው ማኅበረሰብ በፍቅርና በመከባበር በመኖር የሚታወቅና እንደምሣሌም የሚጠቀስ ነው። አንዳንድ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ አካላት እያመጡት ያለው መግለጫም አደገኛና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ የሚደረግ ከመሆኑም በተጨማሪ ዜጎች ምክንያት እየተፈጠረላቸው በዘፍቃድ እንዲጨፈጨፉ የሚያበረታታ መሆኑንም በግልፅ የሚያሣይ ነው።

ሰው በወንጀል ተግባር ተሳትፏል ቢባል እንኳን ለፍርድ ወደ ሕግ ቦታ ቀርቦ ፍርዱን በአደባባይ ያገኛል እንጂ ከሕግ ውጭ ዜጎችን የፊጥኝ አሥሮ በጥይት ደብድቦ መግደል የሚያሳየው ሥርዓቱ በዜጎች ላይ እየፈጸመ ያለውን አጠቃላይ የሰብዓባዊ መብት ጥሰት፣ የደቦ ፍርድና ጭካኔ መሆኑን ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት(የሦስቱ ፓርቲዎች ጥምርት) ያምናል፤ የግፍ ግድያውንም በጽኑ ያወገዛል፡፡

ለሞቱት ነፍስ ይማር እያለ ለአካባቢው ማኅበረሰብና ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ማክሰኞ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሦስቱ ወጣቶች ዘፈቀዳዊ ግድያና በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በሚደረጉ ተመሳሳይ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን በማውገዝ የአንድ ቀን የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ “የንጹሓን የግፍ ግድያ ይብቃ//Stop Massacre of Civilians//” በሚል ቃል እንዲያወግዝና ድምጹንም ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያሰማ ጥሪ እያቀረብን፤

1.ከሕግ ውጭ ምክንያት ፈጥሮ ግድያ የፈጸሙ የፀጥታ ኃይሎችና ግፉ እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሰጡ አካላት ለፍትሕ አደባባይ እስከሚቀርቡ ሕዝቡ ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

2.ግፉን ፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት እየሰጡ ያሉት የማንአለብኝነት መግለጫ እንዲቆም እያሳሰብን ግድያዎች አፋጣኝ፣ ገለልተኛ፣ ግልጽና አስተማማኝ ምርመራ እንዲደረግባቸው እንጠይቃለን።

ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት - ለኢትዮጵያ
ነሐሴ ፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

16/08/2026

''የደከመ ማህበረሰብ ብየ ስሳደብ የአዕምሮ ህመም ነበረብኝ'' አሁን ታክሜ ተሽሎኛል....... ሚኮ ማይክ

በመሴ ሾው ቀርቦ፣ የሚኮ ማይክ (Miko Mike) ድርጊትና የሰጠው ማስተባበያ አሳዛኝ እና ተጨማሪ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብን “የደከመ ማህበረሰብ” ብሎ መስደብ እና የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም ለብሶ መጫወትና ለቪዲዮ ማታለያ ሲያደርግ ቆይቶ ''ይባስ ብሎ፣ ድርጊቱ ያመጣውን ህዝባዊ ቁጣና ተጠያቂነት ለመሸሽ “የአእምሮ ህመምተኛ ነበርኩ” የሚል የሰካራም ማስተባበያ ማቅረብ ህዝቡን የመናቅ ውጤት ነው።

አእምሮ ህመም በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን የሚታገሉት፣ የህክምና እና የእርዳታ እንክብካቤ የሚሻ ከባድ ጉዳይ እንጂ የሰራቸውን ወንጀልና የፈጸማቸውን የስነ-ምግባር ብልሹነት የሚደብቅበት የፖለቲካ ወይም የሶሻል ሚዲያ ጋሻ አይደለም።

የህዝብን ስሜት መጉዳትና ማቃለል በቪዲዮ ማብራሪያ ብቻ የሚታለፍ አይደለም። ማህበረሰቡን እንደፈለጉ እየሰደቡና እየተሳደቡ፣ ነገሩ ሲጠነክር ደግሞ “ታሞ ነው” በሚል ሽፋን ሊያመልጥ ተከስቷል።

ድርጊቱ ማህበረሰብን ብቻ ሳይሆን እውነተኛ የአእምሮ ህመምተኞችንም የሚያሳንስ እና የሚያዋርድ ነው። በሰራው ጥፋት ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በይፋ ህዝቡን ይቅርታ ማለት በጀመርክበት መንገድ ከመሔድ ውጭ፣ የማይበላ ማስተባበያ ማቅረብ ሌላ ጥፋት ነው።

ሀሳብዎን ያካፍሉን?

ሰላም ለኢትዮጲያ
ሰላም ለህዝባችን
ETHIO MEDIA

15/08/2026

#የአብይ የሽመልስ ሴራ ሲጋለጥ

12/08/2026

ሶስት ወጣቶች… ሶስት ህልሞች… ሶስት ቤተሰቦች የተሰበሩበት አሳዛኝ ክስተት

ከቤታቸው የወጡት እነዚህ ሶስት ወጣቶች እንደ ሌሎች ወጣቶች ህይወታቸውን ለመገንባት፣ ቤተሰባቸውን ለመርዳትና የተሻለ ነገን ለማየት ህልም ነበራቸው። ዛሬ ግን እነዚያ ህልሞች በጥ ይት ተቀጩ።

በማህበራዊ ገጾች እየተሰራጨ ባለው መረጃ መሰረት፣ ሶስቱ ወጣቶች በህዝብ አውቶብስ ሲጓዙ ከመኪናው አስወርደው “ፋኖ ናችሁ” በሚል ጥርጣሬ ተገ ድለዋል።

ነገር ግን ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ነገር ፤ የሰው ልጅ ህይወት እንዴት ይህን ያህል ቀላል ሊሆን ቻለ?

እነዚህን ልጆች ለዘጠኝ ወር በማህፀናቸው የተሸከሙ እናቶች ነበሯቸው።
በድካም፣ በላብና በብዙ መስዋዕትነት ያሳደጓቸው አባቶች ነበሯቸው።
እህትና ወንድሞች፣ ጓደኞችና የሚወዷቸው ሰዎች ነበሯቸው።

ዛሬ ግን እነዚህ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ከፎቶ ብቻ እንዲያዩ ተደርገዋል። 💔

አንዲት እናት የልጇን የመጨረሻ ፎቶ ስትመለከት ምን ይሰማታል?
አንድ አባት በዓመታት የድካም ላቡን አፍስሶ ያሳደገውን ልጁን እንዲህ ሆኖ ሲመለከት ምን ይሰማዋል?
የልጃቸውን ድምፅ እንደገና መስማት ለማይችሉ ወላጆች የሚሰማቸውን ሀዘን የሚገልጽ ቃል ከየት ይገኛል? 😭

ሰው በማንነቱ፣ በጥርጣሬ ወይም በፖለቲካዊ ክስ ምክንያት ያለፍርድ ሊገደል አይገባም። የተጠረጠረ ሰው ካለ ህግ አለ፤ ምርመራ አለ፤ ፍርድ ቤት አለ።

ጥያቄያችን ፦ ህግ የት ነው? ፍትህስ የት ነው?

የሰው ህይወት ከማንኛውም ፖለቲካዊ አቋም በላይ ነው።
ግድያ ይቁም። ንፁሃን ከጥርጣሬ ይጠበቁ። ተጠያቂዎችም በህግ ፊት ይቅረቡ።

ለሶስቱ ወጣቶች ነፍስ እረፍትን፤
ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን፤
ለኢትዮጵያ ደግሞ ሰላምና ፍትህን እንመኝ። 🕯️🇪🇹

የእናት እንባ የሚያበቃበት፣ የአባት ልብ የሚረጋበት ቀን ይምጣ።
Via ዳኒ ታምራት

11/08/2026

የአብይ እውነተኛ ማንነት ሲገለፅ🙄

11/08/2026

ለታሪክ ይቀመጥ #ይህ የኢትዮ ፎረም የድምፅ ቅጅ ነው!!

Telephone

Address

AA
Addis Ababa
10000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO MEDIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.