I show Speed

I show Speed

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from I show Speed, Digital creator, legedad, Addis Ababa.

16/05/2026

" :- የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል" የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ፖሎቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ራመቶ መሐመድ "

#ምርጫችን ብልጽግና
#ምልክታችን የስንዴ ነዶ
#መልዕክታችን ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር መሸገር ነዉ!!

Photos from ጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ገፅ። Gamo Chencha FC fans page's post 14/04/2026
Photos from የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት's post 14/04/2026
Photos from GAMO TV's post 14/04/2026
14/04/2026

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ ለስቅለት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
**********
አርባምንጭ ፣ ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም(አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)፦

ከንቲባ መስፍን መንዛ(ዶ/ር) ባስተላለፉት የ2018 የስቅለት በዓል መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ ፀጋ ያለውን በዓል ሲያከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም በፍቅርና በአብሮነት መንፈስ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል
◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉◉

የተወደዳችሁ የከተማችን ነዋሪዎች፣ እንግዶች እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በሠላምና በጤና አደረሳችሁ! አደረሰን!።

በክርስትና እምነት አስተምህሮ ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ያሳየውን ፍጹም ፍቅርና የይቅርታና የማዳኑን ሚስጥር በማስታወስ የሚከበረው " በዓለ ስቅለት " በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ሥርዓቶች በመላው ዓለም ይከበራል።

ከ2 ሺህ 18 የምህረት ዓመታት በፊት በእስራኤል የሔሮድስ ንግስና ዘመን ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ዐደባባይ ተገርፎ፣ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ መስቀል አሸክመው እየተገፈተረ በምድር ላይም እየተጣለ ተወስዶ በቀራኒዮ አደባባይ በመስቀል ላይ ሲሰቀል ምንም ሐጢያትና በደል ሳይኖርበት ስለሰው ልጅ ፍፁም ፍቅር ብቻ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠባትን "ዕለተ-አርብ" የስቅለት ቀን ቤተክርስቲያን በፆም፤በፀሎት፣ በስግድትና በአርምሞ ትቀደሳለች።

ሕዝበ ክርስቲያን የሆንን እኛ የክርስቶስን አርዓያ በመከተል መስጠትን የህይወታችን አካል አድርገን በፍቅር እንድንኖር ያሳዬን የፅድቅ መምህራችን እርሱ ነውና ምሳሌነቱን በሕይወት ዘመናችን ሙሉ እንተግብረው።

በመሆኑም ይህን ታላቅ ሐይማኖታዊ በዓል ስናከብር በአብሮነት መንፈስ ያለንን ማህበራዊ አንድነታችንን በማጠናከር፣ በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም በመጋራት እንዲሆን ጥሪዬን በአክብሮት አቀርባለሁ ።

በከተማችን የሚገኙ የእድሜ ባለፀጋ ከሆኑ አረጋውያን፣ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ከተጎዱና ከተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ጎን ሆንና በመተጋገዝ በዓሉን በፍቅር ልናከብር ይገባል።

ከሕዝባችን ጋር የጀመርናቸው በርካታ የልማት ሥራዎችና የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ ጥያቄዎችን በጋራ ለመፍታት በትጋት የምንሰራበት ወቅትም በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣም እጠይቃለሁ ።

በዓሉን በሰከነ ሁኔታ እንድናከብር ጥሪ እያቀረብኩ ድንገተኛ አደጋና አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲገጥማችሁ ለሚመለከተው አካልና ለጸጥታ አካላት በጥቆማ በማሳወቅ የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደረጉ ስልም መልዕክቴን እገልፃለው።

በድጋሚ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የስቅለት በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ ።

ፈጣሪ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ !

መስፍን መንዛ (ዶ/ር)

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
ሚያዚያ 2፣2018 ዓ፣ም
አርባምንጭ || ኢትዮጵያ

14/04/2026

አዲስ ታሪክ ተመዝግቧል !
እንኳን ደስ አላችሁ!
ጋሞ ጨንቻ ወደ 2019 ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ
ጋሞ ጨንቻ በፕሪሚየር ሊጉ ጋሞ ዞንን የወከለ ሁለተኛውም ሆኗል።
~ ሚያዚያ 5/2018 ዓ.ም

በአሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ የሚመራው ጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን በዛሬ ዕለት አረጋግጧል።

በዛሬው ዕለት በጅማ ስታዲየም በተካሄደ በሊጉ 18ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ አፕሎቹ ቡራዩ ክፍለ ከተማን በማሸነፍ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል።

የአፕሎቹን ታሪካዊ ጎሎችን ታደለ ቴንቶ፣ ማቴዎስ ኤልያስ እና ብሩክ ጥላሁን አስቆጥረው ጋሞ ጨንቻን ወደ አዲስ ምዕራፍ በማሸጋገር ታሪክ ሰርተዋል።

ጋሞ ጬንቻዎች በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ካደረጓቸው 18 ጨዋታዎች 12 ጨዋታ ማሸነፍ ሲችሉ በ5 ጨዋታዎች አቻ በመውጣ በአንድ ጨዋታ ሽንፈትን አስተግደው በአጠቃላይ 41 ነጥቦችን በመሰብሰብ የውድድር ዓመቱን ቀዳሚ ሆነው አጠናቀዋል።

በ2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ማደግ የቻሉት ጋሞ ጬንቻዎች ከብዙ ልፋት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማደግ አዲስ ታሪክም ጽፈዋል።

እራሱ የመሰረተውን ጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብን በከፍታ ላይ የማየት ሕልም ሰንቆ የነበረው ወጣቱ አሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ ሕልሙ ዕውን ሆኖ አፕሎቹን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማሳደግ ስሙን በደማቅ ቀለም ፅፏል።

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን ያረጋገጡት አፕሎቹ በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ከሚያድገው ቡድን ጋር ለአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ በቅርቡ አዲስ አበባ ከተማ ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።

ጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ በኢትዮጵያ በፕሪሚየር ሊግ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን ከወከሉ አርባምንጭ ከተማ እና ወላይታ ድቻ በመቀጠል 3ኛው ክለብ መሆን ችሏል።
በተጨማሪም በፕሪሚየር ጊጉ የጋሞ ዞን ሁለተኛው አምባሳደር ክለብ ሆኗል።
እንኳን ደስ አላችሁ!

14/04/2026

ብሩህ የስቅለትና የትንሳኤ በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ መከበሩን ፖሊስ አስታወቀ

ሰላምበር ፦ሚያዝያ 06/2018 ዓ/ም ሰላምበር ከተማ አስ/ር ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ፣

የሰላምበር ከተማ አስ/ር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረ/ኢ/ር አለማዮሁ ዱርቁላ ከሁሉም በላይ ከፈጣሪ ዘንድ የሰፈነው ሰላሙን በማስቀደም እንዲሁም በመቀጠል የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ከበዓል ዝግጅት ጀምሮ በዓሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከፖሊስ የተላለፈዉን የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረጋቸዉ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ መሆኑን ተጠቁሟል ።

ኋላፊዉ አያይዘዉም በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የእምነቱ ተከታዮች፣የፖሊስ አመራርና አባላቶች ፣ድጋፍ ያደረጉ አጋር የጸጥታ አካላቶች፣ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ ላቅ ያለ ምስጋና የሰላምበር ከተማ አስ/ር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረ/ኢ/ር አለማዮሁ ዱርቁላ አቅርበዋል ።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል !"

02/04/2026

መጋቢታዊያን ትላንት የነበረውን ክፍፍል፣ ለ27 ዓመታት ሲሰበክ የሰነበተውን የጎጥ መንገድ በመናድ፣ በመደመር ዕሳቤ የህብረትን መቅረዝ መለኮስ ችሏል - አቶ ገዛኸኝ ጋሞ

የመጋቢት ወር ሲታሰብ ፓርቲያችን ብልፅግና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ያመጣውን አዲስ ምዕራፍ እና አዲስ ተስፋ፣ ጉልህ የለውጥ ብርሃን፣ የተጓዝንበትን ፈታኝ ግን ደግሞ አኩሪ የስኬት መንገድ ወደኋላ መለስ ብለን እናስባለን።

መጋቢታዊያን ትላንት የነበረውን ክፍፍል፤ ለ27 ዓመታት ሲሰበክ የሰነበተውን የጎጥ መንገድ በመናድ፣ በመደመር ዕሳቤ የህብረትን መቅረዝ መለኮስ ችሏል። ዛሬም ባለማመንታት በዚህ የአንድነት መርከብ ላይ ብዙዎች ተሳፍረው ፤ ዕድል አግኝተው ተገፍተው ከነበሩበት ፖለቲካ ሜዳ የመሳተፍ ዕድል አግኝተው ለሀገራቸው አዎንታዊ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ናቸው።

​በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ ብልፅግና ፓርቲ ወደ መሪነት ከመጣበት ጊዜ አንስቶ የተጀመሩ ሀገራዊ የልማት ውጥኖችን በማሳካት፣ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን በተጨባጭ በመተግበር እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል አመርቂ ስራዎችን ሰርቷል።

በክልላችንም፣ የህዝባችንን የዘመናት የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ጥያቄዎችን ለመመለስ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን። የሰላም፣ የዴሞክራሲ፣ የህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴቶቻችንን ይበልጥ በማጠናከር የተሻለች ሀገር ለመገንባት ጉዟችንን አጠናክረን ቀጥለናል።

​በዞናችን ጋሞ፤ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የትምህርትና ጤና ተቋማትን እንዲሁም የንፁህ መጠጥ ውሃ እና የመንገድ መሰረተ ልማት አውታሮችን በማስፋፋት፣ የከተማ ልማትን በማፋጠን፣ እንዲሁም የወጣቶችንና የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በርካታ ተጨባጭ ድሎችን አስመዝግበናል።

ህዝባችን፣ በተለይም ወጣቱ ክፍል ከብልፅግና ፓርቲ ጋር በመቆም ላሳየው የማይናወጥ ድጋፍና ላበረከተው የላቀ አስተዋፅዖ በፓርቲው ቅ/ጽ/ቤት ስም ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ።

የጋሞ ህዝብ የሰላምና የአብሮነት ተምሳሌት በመሆን የጀመረውን ይህንን የልማት ጉዞ አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።

​ከፊታችን በ2018 ዓ.ም የሚጠበቀውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በከፍተኛ ድል አጠናቀን የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ ዳር ለማድረስ ከወዲሁ የተደራጀና የተቀናጀ የሁላችንም ርብርብ ወሳኝ ነው።

ፓርቲያችን ብልፅግና ለህዝቡ ቃል የገባውን ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና ፍትሃዊ ስርዓት ግንባታን በተግባር ለማረጋገጥ ይህ ምርጫ ትልቅ ምዕራፍ ነው። በመሆኑም መላው የዞናችን ህዝብ፣ የፓርቲያችን አባላትና አመራሮች ከወዲሁ በንቃት፣ በቁርጠኝነት እና ጠንካራ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በመስራት ለምርጫው ስኬት እንድትዘጋጁ አደራ እላለሁ።

​በአንድነት፣ በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ ቆመን የጋሞን ዞን ብሎም ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የብልፅግና ማማ ለማሸጋገር ሁሉም የብልፅግና አባልና አመራሩ በጋራ በመቆም ኃላፊነቱን እንዲወጣ፤ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

​ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
የብልፅግና ፓርቲ 7ኛው ጠቅላላ የምርጫ ምልክታችን የሆነውን "የስንዴ ነዶን" ይምረጡ!

​አቶ ገዛኸኝ ጋሞ
የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Legedad
Addis Ababa