Hab Studio
Bakel Studio is Ethiopian based cultural and updated information provider
23/09/2026
በረራ ተቋረጠ!
ህወሓት የአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠሩ ታውቋል።
በዚህ ምክንያት ወደ መቀሌ፣ አክሱም እና ሽሬ የሚደረጉ የአየር በረራዎች ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል።
በተጨማሪም፣ በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ በጸጥታ ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለው ወደላታወቀ ስፍራ ተወስደዋል።
ከትናንት ጀምሮ ወደ መቀሌ በረራ አለመኖሩን ከፍላይት ራዳር ለማረጋገጥ ተችሏል።
23/09/2026
😭
የኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ባለ ውለታው አርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ አስቸኳይ የሕክምና እርዳታ ጥሪ ቀረበ
በሀገራችን የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ውስጥ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በፊልም፣ በቴአትር እና በተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ ባሳየው ድንቅ የትወና ክህሎቱ የብዙዎችን ቀልብ የገዛው አርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በአሁኑ ወቅት ባጋጠመው የጤና እክል ምክንያት የሁላችንንም ደጋፊ እጅ ይሻል።
በተለይም «አላዳንኩሽም» በተሰኘው ተወዳጅ ፊልሙ እንዲሁም በመድረክ ላይ ባለው ልዩ የድምፅ እና የትወና ብቃት የሚታወቀው አርቲስት ዮሐንስ፣ በሥራ ላይ እያለ በደረሰበት ከባድ አደጋ የዳሌ አጥንቱ ተሰብሮ ላለፉት 6 ዓመታት በሰውነቱ ውስጥ በተተከለ የብረት ድጋፍ ከሕመምና ስቃይ ጋር ሲታገል ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅት አጥንቱን ደግፎ የቆየው ብረት በደም ዝውውሩ ላይ ከፍተኛ ችግር በመፍጠሩ፣ በአስቸኳይ ወጥቶ በሌላ ድጋፍ ሰጪ አካል እንዲተካ የህክምና ባለሙያዎች አሳስበዋል። ለዚህ አስቸኳይ የሕክምና ሂደትም ከ600,000 (ስድስት መቶ ሺህ) ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ታውቋል።
ይህን ተወዳጅ አርቲስታችንን ወደ ነበረበት ሙሉ ጤንነት እና ወደሚወደው የጥበብ መድረክ ለመመለስ አቅማችን የፈቀደውን ያህል በመደገፍ ወገናዊ አለኝታችንን እናሳይ።
• የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000003991238
• የሒሳብ ስም፦ Yohannes Afework Kassa (ዮሐንስ አፈወርቅ ካሳ)
ይህን መረጃ Share በማድረግ ለሌሎች በጎ አድራጊዎች እንዲደርስ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላሉ።
ለአርቲስት ዮሐንስ አፈወርቅ ፈጣሪ ፈጣን ምህረቱን እንዲልከለት እንመኛለን።
22/09/2026
...እወደዋለሁ....እሳሳለታለሁ...ልክ እንደ እናት እቅፌ ውስጥ አስገብቼ ፀጉሩን እየደባበስኩ..
"ዛሬ ቀንህ እንዴት ነበር አባቴ?"
"ባክሽ ብዙ ደስ አይልም ወይ ላንለወጥ ነገር እየደከምን ነው ሌላ አማራጮችን መፈለግ አለብን...መጀመሪያ ቃል እንደገባሁልሽ ቃሌን ማክበር አልቻልኩም...አንደላቅቄ ማኖር አልቻልኩም...ከጓደኞችሽ አሳነስኩሽ...አታይም ፀጉርሽን" ይለኛል የተበጣጠሰ ፀጉሬን ቀና ብሎ በእጁ እየነካካ....
"እኔኮ አፈቅርሀለው ነገ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ አውቃለሁ ባይመጣም አፈቅርሀለው ኪስህን አይቼ አይደለም የወደድኩህ ...አንተ ብቻ በርታልኝ አንተ ብቻ ጠንክርልኝ ቢኖርህ እንዴት እንደምታኖረኝ አውቃለሁ"
"ብቻ ነገ ቀን ይውጣልን የኔ እናት" ብሎ ግንባሬን ስሞኝ ከስሬ ይሸጎጣል...ይለፋል ይሰራል እኔም እሰራለሁ ግን ትዳር እንዳሰብነው አልሆነልንም ነበር ከባድ ጊዜ ነበር ....ከጊዜያት በኋላ ሁሉም ነገር መስመር ያዘልን ...ሱቅ ከፈትን...ሀብት አፈራን...ብዙ ነገሮችን ቀየርን....
"ከጓደኞቼ ጋ ራት ፕሮግራም አለብኝ ካመሸሁ አታስቢ አትጠብቂኝ"
"እሺ ራሳችሁን ጠብቁ"
..ከጊዜያት በኋላ ያመጣው ባህሪ ግራ ያጋባል...ያኔ በባዶ ኪስ የነበረን ፍቅር አሁን ገንዘብ ቀይሮታል...ቤቱ ከሚያድርበት ውጪ የሚያድርበት ጊዜ ይበልጣል...እንደበፊቱ መታቀፍን አይፈልግም ...ከእኔጋ ጊዜ ማሳለፍ አይፈልግም...እንደውም ከእኔጋ መታየትንም አይፈልግም...ብዙ ጊዜ ችግሩ ከእኔ ነው ብዬ ራሴን ለመለወጥ ታገልኩ...ኋላ ላይ የገባኝ ችግሩ የኔ እንዳልሆነ ነው ያኔ ዝምታን መረጥኩ....
"መፋታት አለብን በእርግጥ የተፈራረምነው ነገር የለም እንለያይ.."
አለኝ....ለካ አልተፈራረምንም...ያኔ እንፈራረም ስለው" ከወረቀትኮ ልብ ይበልጣል" ነበር ያለኝ የትም አይሄድም ብዬ ስላሰብኩ ከዛ በኋላ ደግሜ አልጠየቅኩትም.....
"ያሁሉ ጊዜስ? ያ ሁሉ ፍቅራችንስ? የኔስ እድሜ? በቃ? በቀላሉ እንለያይ አልከኝ? "
"አዎ በቃ እኔም ላንቺ ያለኝ ስሜት ቀንሷል...አንቺም በጊዜ ወደሚወድሽ ሂጂ" ..ለካ ነይልኝ ባሉ ማግስት ሂጂም ይባላል...ለእሱ ብዬ ነበር ከቤተሰቦቼ የተለየሁት...አይሆንሽም ሲሉኝ ይወደኛል ይሆነኛል ብዬ ነበር በባዶ ቤቱ የገባሁት....
"አስብበት ግድ የለህም"
"አስቤበታለሁ ውሳኔዬን ነው የነገርኩሽ...ቤተሰቦችሽ ጋ ምትሄጂበትን ቀን ሰአት አሳውቂኝ መኪና እልክልሻለሁ..." ጥሎኝ ወጣ....
ግራ ገባኝ...ከሱጋ ያሳለፍኩት ጊዜ
በሰከንዶች ውስጥ እንደ ትውስታ ታዩኝ...በባዶ ቤት የነበረን ፍቅር ታየኝ...ልቤ ተሰበረ ድምፁ ለእራሴ እስኪሰማኝ ድረስ ከሽ...ከሽ...ይለፍልኝ እንጂ አንቺን እንዴት እንደማኖርሽ አቃለው ብሎኝ አልነበር? ገንዘብ ሲመጣ ፀባይም አብሮ ይቀየራል? ፍቅርም ይጠፋል? ምኔ አስጠልቶት ነው? እንደ እናት ስፍስፍ አልኩበት? የትም እያደረ ሲመጣ ስለማልጠረጥረው ነው? ወይስ ጨቅጫቃ ሚስት መሆን ነበረብኝ? እኔ የችግሩ መወጣጫ ነበርኩ? ብዙ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች..... አብረን የተነሳነው አንድ ፎቶ እንኳን አልነበረንም....ፍቅር አውሮኝ ነበር....እኔ ከዛ ቤት በወጣሁ ማግስት...የምታምር የምታሳሳ ቆንጅዬ ኮረዳ አስገባ...ቅር አላለኝም ...ውበቴ ደብዝዞበት ነው ካለበት ደረጃ ጋ አልመጥነውም ነበር....ቅር አላለኝም....ማፍቀር የራስ ማድረግ ብቻ አይደለም የሚያፈቅሩትን ሰው ምርጫም ማክበር ፍቅር ነው
22/09/2026
የእንባ [ደም] ቆብ!
የእራት ግብዣው ጨርሰን እንደወጣን መኪና ውስጥ ስልክ አወራለሁ፡፡ አንድ አባት መንገዱ ጠርዝ ላይ ቆመው በቅንድባቸው አወሩኝ። ስልኩን አቋርጬ ለመስማት መስተዎቱን ዝቅ አደረኩ። በሩን ክፍት አደረጉና መልሰው በኀይል ዘጉት፡፡ ኹኔታው በጣም ስላስደነገጠኝ ስልኩን ዘግቼ ከመኪና ወረድኩ፡፡
“ምንድነው አባ?” አልኩኝ እየተንቀጠቀጥኩ፡፡
“እኛ እዚኽ ብርድ ላይ ቆምን አንተ ሴት ጋር ትጀናጀናለህ? . . . ዘወር በል ወደዚያ!” አሉኝ፡፡
“ጌታ ሆይ!. . . . መስቀል ይዘው ነው እንዲኽ የሚሉት?” አልኩ ደንግጬ፡፡
“ያንተ ጌታ ቂጣም ሴት ትመስላለች፡፡ . . . ደግሞ እንደ ደኅና ሰው ጌታ ሆይ ትላለህ? . . . ሸርሙ*!” አሉኝ፡፡
የሰከሩ ስለመሰለኝ፤ ራሳቸውን እንዲገዙና የቤተክርስቲያን ስም እንዳያጠፉ ቀስ አድርጌ ልነግራቸው ጠጋ አልኩ። አጠገባቸው የነበሩ ሌላ አባት፤ በዕድሜም በማዕረግም ከፍ ያሉ የሚመስሉት፤
“ምን ልትኾን ነው?” አሉና ገፋ አፈረጉኝ፡፡
ቦግ አለብኝ! ከአፋቸው የወጣው ቆሻሻ ቃል አሰከረኝ፡፡ እጄን ሰብስቤ ጠብ ውስጥ ገባሁ፡፡ ከኹለቱም ጋር የለየለት ድብድብ አደረኩ፡፡ የድግሱ መልክ፣ የቀን ውሏችን እስኪበላሽ፤ ቤቱም አካባቢውም ቀውጢ ኾነ፡፡
ከኹሉም በልብ ውስጥ የጨለመው እምነት ከባድ ነበር፡፡ ከዚች ቀን ጀምሮ አባት ማክበር አቆምኩ፡፡ ጾም፣ ጸሎት፣ ቤተክርስቲያን ከመኼድ ተከለከልኩ፡፡ መስቀል መሳለም አንገሸገሸኝ፡፡ አማኞቹ ሳይቀር አስጠሉኝ፡፡ እግዚአብሔር ማነው? ንዴቴ በኹሉ ላይ ኾነ፡፡ አባዎችን ለማዋረድ ብችል ለመጉዳት የተዘጋጀሁ ኾንኩኝ፡፡
***
ከትንሿ የወይራ ዛፍ ሥር ከነፍስ አባቴ ጋር በአንድ ጉዳይ ጨዋታ ይዣለሁ፡፡ እሳቸው ግንዱን ደገፍ ብሎ ካለ ድንጋይ ላይ፣ እኔ መሬቱ ላይ እግራቸው ሥር ቁጭ ብያለሁ፡፡ ይኽንን ለትሕትና ያደረኩትም ቢኾንም ከፍታውን ሊመኩበት ሲፈልጉ ሳይ ትንሽ ጎረበጠኝ፡፡ የአቀማመጣችን ከፍና ዝቅ ኀላፊነት የሚሰጠቸው እንጂ ኩራት የሚደርብላቸው አልመሰለኝም ነበር፡፡
ነጠላዬን ወደ ግንባሬ ሳብ አደረኩና ጫማዬን አውልቄ በባዶ እግሬ ኾንኩ፡፡ ጥፍር ቀለም የተቀቡ ጣቶቼ ፍጥጥ ብለው ሳያቸው በቀሚሴም በነጠላዬም ልሸሽጋቸው ሞከርኩ፡፡ ቀድመው ይኽንን ያዩ ስለመሰለኝ መሬቱን በድንጋይ ጫር ጫር እያደረኩ፤
“አባ እኔ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም፡፡ በሚችሉት፣ ይኾናል ባሉት ኹሉ ይርዱኝ” አልኳቸው፡፡
“ማዳኑን ባንጠራጠርም የጸሎት መልስ ግን እንደ መድኀኒት አይደልም፡፡ ቄስ እንደ ሐኪም በድፍረት መናገር አይችልም፡፡ ኹሉም ነገር እምነትና የእግዚአብሔር ፍቃድ ላይ የሚደገፍ ነው፡፡ የእኛ ድርሻ እንደ ያዕቆብ እሱን ይዞ አንቢኝ ማለት ብቻ ነው፡፡ ሳያቋርጡ መጸለይ! እንጂማ የልጅ ነገር ከባድ ነው፡፡ እኔ ራሱ በብዙ ተፈትኜበታለሁ፡፡ አንዳንድ ለአንቺ የምነግርሽ እኔ የማልኖራቸውና ልኾን የምመኛቸው ናቸው” አሉኝ ቅዝዝ ብለው፡፡
ከእሳቸው ጋር ይኽንን እያወራሁ አንድ ወጣት ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ሰውነቱ ልሟል። መንፈሱ ግን ጠንካራ ይመስላል፡፡ ከጸበል እንደተመለጠ ሰው ዐይኑ ድፍርስ ሰውነቱም ቅጭጭ ያለ ነው፡፡ አስተያየቱ ቁጣ የቀላቀለ ንዴት አለበት፡፡ ድንጋይ የሚያነሣብን መስሎኝ ፍርሀት ፍርሀት አለኝ፡፡ ሐሳቤ እንደተሰረቀ ሲያዩ አባ ትኩረታቸውን ወደ እሱ አደረጉ፡፡ ልጁ ወደ መቅደሱ ቀረብ እንዳለ በጉልበቱ ውድቅ አለ፡፡ ሰውነቱ ከወለሉ ጋር የፈጠረው ድምፅ ሰቅጣጭ ነበር፡፡ በእንብርክክ ወደ በሩ ጠጋ አለና መቃኑን ይዞ ይንሰቀሰቅ ጀመር፡፡
“ይቅርታ የእኔ ልጅ? . . . “ አባ ትንሽ ገፋ አደረጉኝ፡፡
“ይኼ ልጅ ራሱን የሚጎዳ ይመስላል” እግሬን ሰብሰብ ሳደርግላቸው ብድግ አሉ፡፡
እሳቸው ወደ ልጁ እየኼዱ፤ የእኔን ሐሳብ የሸሹት መስሎኝ ቅር አለኝ፡፡
***
በካሕናቱ በር በኩል ብዙ ጊዜ ለእጣን ማቀጣጠያ የሚኾን ከሰል አይጠፋም፡፡ ልጁ እዚኽ አመድ ላይ እየተንከባለለ ግንባሩን ከወለሉ ጋር እያፋተገ ደረስኩ፡፡
“ራስን መጉዳት እኮ ልክ አይደልም፡፡ ተነሥ!” አልኩት፡፡ ቀና ብሎ በቁጣ ተመለከተኝና መልሶ ወለሉ ላይ ተኛ፡፡
“መጀመሪያ ተነሥና በጋራ እንጸልይ?” አልኩት ትንሽ ጎንበስ ብዬ፡፡
ድንገት አፈፍ አድርጎ ኹለት እግሬን ያዝ አደረገኝ፡፡ ልወድቅ ብዬ እንደምንም ተንገዳግጄ ተረፍኩ፡፡ ቀሚሴ እንዳይጠልፈኝ ለመሰብሰብ ስሞክር፤ ከዕርድ እንዳመለጠ በሬ ጫማዬ ሥር በኀይል እየተነፈሰ ምንም አላላውስ አለኝ፡፡ በርከክ አልኩና ትከሻውን ይዤ ቀና ላደርገው ሞከርኩ፡፡ ጭንቅላቱን የበለጠ ወደ መሬት እየቀበረ ቀና ለማለት እንቢኝ አለኝ፡፡ ከእንባ ውጭ የሚናገረው ቃል አልነበረውም፡፡ ፀጉሩን እየደባበስኩ ዝም አልኩ፡፡
ትንሽ ቆይቶ ሰውነቱ መላላት፣ የያዘኝ እጁም መርገብ ሲጀምር፤
“ምንድነው የኾንከው የእኔ ልጅ?” አልኩት እጄን ትከሻው ላይ ጣል አድርጌ፡፡
“ይቅርታ ያድርጉልኝ አባ!” አለና መልሶ ወለሉ ላይ በግንባሩ ድፍት አለ፡፡
“ተው እባክህ ራስህን አትጉዳ . . . ለእግዚአብሔር እንባና ቃል ይበቃዋል” አልኩት፡፡
ከሣጉ ጋር እየታገለ እግሬን እንደያዘ ከተኛበት ነተሥቶ ቁጭ አለ፡፡ መስቀል ላሳልመው ወደ ግንባሩ ጠጋ ስል ተስገብግቦ መስቀሉን ቀጥሎ እጄን፣ ጉልበቴን፣ ካፖርቴን ጭምር በጥድፊያ ሳማቸው፡፡ ኹኔታው በጣም አስደነገጠኝ፡፡
“ከአራት ዓመት በኋላ ዛሬ ቤተክርስቲያን መጣሁ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ተሳለምኩ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ . . .” አለ፡፡
እጁን እንደያዝኩት ደረጃው ላይ ቁጭ አልን፡፡
“ይኽንን ያህል ጊዜ እንዴት ብቅ ሳትል ቀረህ? . . . አምጸህ ነው?” አልኩት፡፡
ንግግሩን እንባ ቀደመው፡፡ ለተወሰነ ጊዜ አቀርቅሮ ዝም አለ።
“ምን እንደሚባል አላውቅም. . . ” አላና በአንድ ግብዣ ቦታ የተፈጠረውን አንድ አጋጣሚ አወጋኝ፡፡
“ያ አባት የብዙ ሰዎችን ልብ አቁስለው፣ የቤተክርስቲያንንም ስም አጉድፈው ሊኾን ይችላል፡፡ እንደ አንተ ያሉ ልጆች እንዲጠፉ ምክንያት በመኾናቸው ጥያቄ አለባቸው፡፡ አንተ ግን የራስህን መስቀል ስለመሸከም እንዴት አላሰብክም?” አልኩት፡፡
“መቶ በመቶ ጥፋቱ የእሳቸው እንደኾነ ርግጠኛ ስለነበርኩ ምንም ዐይነት ኀላፊነት አልወሰድኩም፡፡ ጭራሽ ለጥያቄ የሚበቃ ጉዳይ አልመሰለኝም፡፡ ይገርመዎታል፤ እጣን እየናፈቀኝ አንዳንድ ጊዜ የጀበና ቡና የሚሸጥበት ቤት እየኼድኩ ቁጭ እላለሁ” አለኝ፡፡
በብረት ዘንግ ራሱን እንደተመታ ሰው ክው አልኩኝ፡፡ ድንገት እንባዬ መጣ፡፡ ቆቤን አውልቄ መኻላችን ቁጭ አደረኩት፡፡ ራሰ በራ እንደኾነ ሲያ ድንገጥ አለ፡፡ እንደ እኩያ ዐንገቱን ይዤ ትከሻው ላይ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ ይኽ የእሱ ንስሓ አይደለም፡፡ ለእኔ የተላከ መልእክት ነው፡፡ በክህነታችን እየፈጸምን ያላነው ክሕደት ቁልጭ ብሎ ታየኝ፡፡ የመንጋን እምነት ከመብላት በላይ ለእረኛ ምን ኀጢአት ይኖራል? ለግልገሎች መጥፋት ሰበብ ከመኾን በላይ ምንም የሚያሳዝን ነገር አለ? ያሳትኳቸውን ጠቦቶች እያሰብኩ ድርቅ ብዬ ቀረሁ፡፡
“የኔ ልጅ እንኳ አንተ ተመለስክ፡፡ እንኳን አንተ የመዳኑን መንገድ ተከተልክልኝ፡፡ አምላኬ አንተን ስለላከልኝ አመሰግነዋለኹ! ይኼው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፤ ከዚኽ በኋላ የተባልነው ኹላችን፤ ኀላፊነታችንን እንድንወጣ ይቺን ብቻ ለማስተማር ቃል እገባለሁ!” ቀድሞ እሱ ሲንከባለልበት ወደነበረው ዐመድ ዝቅ አልኩኝ፡፡
በርከክ ባልኩበት፤ ቀጭን ነፋስ በላዬ ላይ ሽው አለብኝ። ቀና ስል ጥምጣሜን አየኋት። በእንባ የራሰች ስለመሰለኝ መልሼ ላደርጋት እስክፈራ ተጨነኩ፡፡
Via: yohannes belay
ቪድዮ እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር ። " - ሮዛ
ባሳለፍነው ሳምንት፣ ከዓርብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ አንድ የሃይማኖት አባት የሚታዩበት ፀያፍ ነውረኛ ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቆ ብዙዎችን አስደንግጧል ፤ ጉድ አሰኝቷል።
ቪዲዮው እውነተኛ ነው ? እውነተኛ አይደለም፣ በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ (AI) የተቀናበረ ሐሰት ነው ? የሚሉ ክርክሮችም ተነስተዋል።በኋላ ላይ ግን " እኔ ተበዳይ ነኝ " ያለች ግለሰብ ወደ ሚዲያ ወጥታ ከላይ የምታዩትን ቪዲዮው እውነተኛ መሆኑን አፍረጥርጣ መስክራለች።
" ተበዳይ ነኝ " ያለችው ስሟ ሮዛ እንደሚባል፣ የአክሱም ነዋሪ እንደሆነችና በከተማው በሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በአስተናጋጅነት እንደምታገለግል ተናግራለች።
ሮዛ " ሱርያል " ለተባለ የዩቲዩብ ሚዲያ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በድምፅ በሰጠችው ማብራሪያ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የ " ትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ አረጋዊ " በሥራ ቦታዋ መጥተው ባገኙት የመስተንግዶ እርካታ መነሻ እንደተዋወቋት ገልጻለች።
ከዚያም የሮዛና የጳጳሱ መቀራረብ ተጠናክሮ በመቀጠሉ፣ በኋላ ላይ ራሷን እስከ መጥላት ወደ አደረሰ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተበዳይ ነኝ ባይዋ በጸጸት ተናግራለች።
ሮዛ እንደምትለው፣ ጳጳሱ በተደጋጋሚ ጊዜ " ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት " ይህንን መግቻ እንዲሆን ለጳጳሳት መኖሪያ ወደ ተፈቀደ ቤታቸው በመሄድ ጾታዊ ግንኙነት እየፈጸሙ ቪዲዮ በድብቅ መቅረጿን ተናግራለች።
ከላይ ላይ ያለውን የቀረጸችውን የቪዲዮ ማስረጃ ወደ ጳጳሱ ልካ ግንኙነታቸው እንዲቆም ብትማጸንም እንዳልተሳካ ተናገራለች።በድብቅ የቀረጸችውን ቪዲዮ እንድታጠፋ ከጳጳሱ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ እንደቀረበላትም ገልጻለች።
ሆኖም ብር ከመቀበል በላይ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህ መሰል ጸያፍ ተግባር ከሚፈጽሙ የሃይማኖት አባቶች እንድትላቀቅ ባሳየችው አቋም፣ እስከ የመግደል ሙከራ ዛቻ እንደተደረሰባት አብራርታለች።
በዚህ ሁኔታ የቀረጸችው ቪዲዮ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ ሊለቀቅ ችሏል። ይግም ፍርሃትና ስጋት እንደፈጠረባትም አልደበቀችም።ሮዛ፣ “ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ መጽሐፍ ሕግ በጽኑ በሚገዙ የሃይማኖት አባቶች መመራት አለባት” ስትል በአጽንኦት አሳስባለች።
በተጨማሪም በአክሱምና ከአክሱም ውጪ እሷን ጨምሮ የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው 4 ሴቶችን እንደምታውቅና እንደምታጋልጥ አረጋግጣለች።
ከዚህ ቀደም ጳጳሱ ለጵጵስና በታጩበት ጊዜ " ወልደዋል " ተብሎ በቪዲዮ የተደገፈ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭቶባቸው የነበረ ሲሆን የሰጡት መልስ አልነበረም።
በአሁኑ የቪድዮ ጉዳይም ፣ እንዲሁም ሮዛ ላወረበችው የጾታዊ ጥቃት ክስ እስካሁን በይፋ የሰጡት መልስ የለም።" በደል ደርሶብኛል " ባይዋ ሮዛ በአሁኑ ሰዓት በቂ የሕግ አገልግሎት እየተሰጣት በአክሱም ከተማ እንደምትገኝ ገልጻለች።
መቀመጫቸው አክሱም የሆኑት አቡነ አረጋዊ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉ አይታወቅም። ከዚህ በፊት በባህርዳር አባይ ማዶ ገብርኤል አስተዳዳሪ እና ቆምስ ከአንዲት መነኩሴ ልጅ በመውለድ እና በመካዱ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምሮቶ በDNA በመረጋገጡ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ታግዶ ግለሰቡ ለልጁ በየወሩ 3ሺብር የማሳደጊያ እንዲከፍል ፍርድቤቱ መወሰኑ አይዘነጋም ።
21/09/2026
#ሌሎችን ከጥቃት ለማዳን እራሷን አሳልፋ ሰጠች !
የሮዛ ስህተት ምንድነው ? ይሄንን መረጃ ይዛችሁ ፍረዱ
ሮዛ በሆቴል መስተንግዶ ስራ ህይወቷን የምትገፋ ወጣት ነች። ከእለታት አንድ ቀን በስራ ምክንያት የትግራይ ሲኖዶስ ፀሐፊ እንደሆነ ከሚነገርለት የጵጵስና ልብስ የለበሰ አባት ጋር ተዋወቀች።
ሮዛም አባት ተዋወቅሁ ብላ ደስ አላት። እንዲፀልዩላት ተናግራ በደስታ ወደ ስራዋ ተመለሰች። ግንኙነታቸዉ በዚህ መልኩ ቀጠለ
ከጊዜያት በሗላ አባት ብላ የቀረበቻቼዉ ሰዉ ከፍ ባለ ገንዘብ ከአስተናጅነት አዉጥተዉ ሕይወቷን እንደሚቀይሩላት ቃል ገቡላት። በሒደትም አባብለዉ ሴትነቷን ተጠቀሙባት።
ነገር ግን ቃል የገቡላትን አለመፈፀም ብቻ ሳይሆን መረጃ እንዳታወጣ ማንገራገር ጀመሩ። ሁኔታዉን ለቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎችና ለሕግ አስከባሪዎች ብትናገርም ማስረጃ በሌላት ጉዳይ ላይ ቅሬታ በማቅረቧ በስም ማጥፋት እንደሚከሷት ተነገራት።
ጫናወወ እያደገ በመምጣቱ ሮዛ አንድ ነገር ለማድረግ ወሰነች። ራሷን አጋልጣም ቢሆን በሌሎች ሴቶች እና በቤተክርስቲያን ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን ለማጋለጥ ቪዲዮ መያዝ እንዳለባት ወሰነች።
ለዚህም ሁኔታዎችን ሁሉ አመቻችታ ራሷን ጭምር አጋልጣ ቪዲዮዉን ያዘች። ቪዲዮዉንም ማስረጃ ስለሌለሽ በስም ማጥፋት እንከስሿለን ላሏት የቤተክርስቲያን እና የህግ ሰዎች ጭምር ሰጥታ ነበር። ከቪዲዮዉ በሗላ ድርድር፣ እንግርግሪያ፣ ድርድር፣ እንግርግሪያ፣ ድርድር፣ እንግርግሪያ ...ቀጠለ
ቪዲዮዉ አየር ላይ ዋለ....
"ህይወት አስ"ገድ"ዶኝ" ሴ"ተ"ኛ አዳሪነት ሰርቻለሁ፣ አባት ብየ በቀረብሗቸዉ ሰዉ የደረሰብኝን ነገር ሌሎች እንዲማሩበት ራሴን በማዋረዴ አልፀፀትም" ያለችዉ ራሷ ነች
የሆነዉ ይኸዉ ነዉ፣ ይሄንን መረጃ ይዛችሁ ፍረዱ!!
21/09/2026
የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ትምህርት ቤት (አዲስ አበባ ፒያሳ ጊዮርጊስ) አገልጋይ የሆነው ወንድማችን አመኑ ይልማ በዲስክ በነርቭ ሕመም ለብዙ ዓመታት ታሞ የተወሰነ ሕክምና ቢያገኝም ነገር ግን አሁን ሕመሙ እጅጉን ጠንክሮበት በራሱ ለመጸዳዳት አለመቻል ፣ ራስን ስቶ የመውደቅ ደረጃ ላይ ..... ደርሷል በዚህም ላይ የቤት ኪራይ ወጪ ያለበት እና ባለትዳር የልጅ አባት በመሆኑ እጅጉን ተቸግሯል ስለዚህ የተሻለ ሕክምና ማግኘት እንዲችል በጎ ልብ ያላችሁ እግዚአብሔር የፈቀደላችሁ የተቻላችሁን ያህል የርኅራኄ እጃችሁን እባካችሁ ዘርጉለት እርሱን በስልክ ለማውራት ከፈለጋችሁ 0910115204 በዚህ ደውሉለት
በቴሌ ብር ለመርዳት 0910115204 / 0960192121
በንግድ ባንክ 1000277663167
በአቢሲንያ 247151842
በአሀዱ ባንክ 0018050810101
በንብ ባንክ 9260 (7000003735608 )
Via : Daniel bona
21/09/2026
!
ብቻውን ልጅ ያሳድጋል :ሚስቱን ዩንቨርስቲ ያስተማራል :የቀን ስራ ጅብሰም ቀለም እና የመሳሰሉትን ሊስትሮን ጨምሮ ይሰራል :ቤት ውስጥ እንጀራ መጋገርን ጨምሮ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚሰራው ራሱ ነው : ይሄን ሁሉ የሚያደርገው ብቻውን ያለማንም አጋዥ ነው ....ከዚህ ሁሉ አድካሚ የቀን ተቀን ሕይወት ቦክሱን አብሮ ይሰራል!
በ 11 ወር ውስጥ 11 ግጥሚያ አድርጎ 11ዱንም አሸንፏል አብዛኞቹ ግጥሚያዎች ከመጀመሪያው ዙር አያሳልፋቸውም በ knockout ይዘርራቸዋል!... ባጠቃላይ ከ 24 ጨዋታ በላይ አሸንፏል ይሄ ሰው መልካሙ ዉቤ ይባላል በቅፅል ስሙ ጎንደሬው ኖካውተር!
ታዲያ ይሄ ልጅ ትላንትና ምሽት በ Ethio fight night የ boxing ውድድር በ 54 K.G ዘርፍ ከ ይድነቃቸው ብርሃኑ ጋር ግጥሚያ አድርጎ በጠባብ ውጤት ተሸንፏል።
🔺መልካሙ ውድድሩን ቢያሸንፍ ኑሮውንም በተወሰነ መልኩ ያሸንፍ ነበር ነገር ግን አልተሳካም እናም ድርጅት ያላችሁ ንግድ ተቋም ያላችሁ ይህነን ወንድም ማስታወቂያወችን አሰሩት አበርቱት። 🔺
በትላንቱ ውድድሩ ላይ የነበረው ክፍተት መቸኮል እና ለማጥቃት ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ዋጋ አስከፍሎታል።
Via : ዘመን ተሻጋሪው
በድጋሜ ተመልሷል✌️
21/09/2026
#በተዋወቅን በሁለተኛው ቀን "ለምን ቤቴ አትመጪም"የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ።መጀመርያ ደነገጥኩ...ቀጥሎ ውስጤ ላይ አንዳች ደስ የማይል ስሜት ተፈጠረብኝ።ሳላውቀው "ይኼ ሴሰኛ አልኩኝ...."ሴሰኛ ስል ድሮ እናቴ ጎረቤታችን ያሉትን ሽማግሌ የምትጠራበት ቅፅል ስም ትዝ አለኝ።ለምን እንዲህ እንዳለቻቸው ስጠይቃት አስር ቦታ ይዘላሉ ትለኛለች ነገሩን አለባብሳ።አስር ቦታ ማለት ከብዙ ሴት ጋ ይገናኛሉ ማለቷ እንደሆን ገብቶኝ ወንድ ልጅ ከትውውቃችን ማግስ ስሜቱን ሲያሳየኝ ሴሰኛ ማለት ይቀናኛል
መልካሙ ጋ ስንገናኝ የታክሲ ብር አጥቼ ከኤቲኤም ማሽን ጋ ስታገል ነው ድንገት ከኋላዬ መጣና
"እኔ ልሞክረው"አለኝ ድምፁ ቀጭን ሰውነቱ ግዙፍ ውሀ ውሀ የሚል ንፁህ ወንድ ነው።እኔም ደጋግሜ መሞከሬ አሰልችቶኝ ቦታውን ለቅቄለት ቆምኩ።የትምህርት ሰአት ረፍዶብኝ ማደርገው ጠፍቶኝ እየተንቆራጠጥኩ ማሽኑ ለሱ ገንዘቡን ሲሰጠው ችግሩ ከኔ መሆኑ ገብቶኝ ልሄድ ስል...
"ቆንጆ እኔ ላበድርሻ"አለኝ ሁለት መቶ ብር ነጥሎ እየሰጠኝ።እውነት ለመናገር አልተግደረደርኩም ብሩን ተቀብዬው ስልኬን ሰጥቼው ተለያየን....ያን ቀን ማታ ትንሽ አወራን በነጋታው ረጅም ወሬ እና ሳቅ ተጨምሮበት ተግባባንና ሊዘጋው ሲል እቤቱ እንድሄድ ጠየቀኝ....ይሄኔ ውስጤን ቅር እያለው ቢሆንም"አንድ ቀን"አልኩት ያው እምቢ መሆኑ ይገባው ብዬ ነበር...እሱ ግን ጥያቄውን አላቆመም በመግባባታችን ውስጥ መላመድ ቢጨምርም አምኜው መሔድ አልፈለኩም።እሱም ቢሰለቸው ጭራሽ መደወሉን ተወው። እኔም ለአልጋ አስቦኝ እምቢ ስላልኩት ነው ብዬ ተውኩት።ተረሳሳን።ወር ሆነን....አንድ ቀን ድንገት ስልኬ ጮኸች ክላስ ስለነበርኩ አላነሳሁም ግን ደሞ መደወሉ ደስ ብሎኝ ነበር.....እንደወጣሁ ደወልኩለትና
የጠፋ ሰው ኩራትህ ለቀቀህ አልኩት እየተጀነንኩ
ሜሪ እናቴ አርፋለች ብቻ አለኝ።ድንግጥ ብዬ ቀረሁ የምለው አጥቼ እየተንተባተብኩ እሱ ወሬውን ቀጠለ....
ታቂያለሽ ህርሜን ከቤት ብወጣ ነው ያገኘሁሽ እናቴን ጥዬ ስለማልወጣ ሁሉ ነገሬ ቤት ነበር ድንገት በወጣሁበት ቅፅበት አንቺን አገኘሁሽ ስንገናኝ ለእማ መፍትሔ ያበጀሁ መስሎኝ ነበር።ሚስትህን ሳላይ እያለች ስለምታስጨንቀኝ አንዴ እንድትስቅልኝ ፈልጌ ነበር ቤቴ እንድትመጪ የጠየቅኩሽ ግን አልሆነም በጠቅኩሽ ማታውን እናቴ ሞታ አደረች በቃ አለና ፀጥ አለ
ምገባበት አጣሁ ምናለ እሺ ባልኩትና የእናቱን ሳቅ አይቶ በተለያዩ ብዬ አሰብኩ ከፋኝ ወድያው ሳላስበው
አሁን የት ነህ ልምጣ አልኩት ቤቱን ጠቆመኝ ሄድኩኝ ተመላለስኩኝ እዛው ቤቱ ቀረሁ ሁለት ልጆችን ወለድን መልካሙን ባሌ አደረግኩት
studio
Category
Website
Address
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Hab Studio posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.