Wollo Current Information

Wollo Current Information

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wollo Current Information, Public swimming pool, Addis Ababa.

22/06/2026

የሴራ ፖለቲካ ተጠቂ የሆኑት የምዕራብ ወሎ ተወላጆች!!

ራሱን ሚኒልክ እዝ በሚል የሚጠራው የምሬ ወዳጆ ስብስብ ከመሀል ሳይንት፣ ከቦረና እና ከወግድ ወረዳዎች ከትግራይ መሳራያ እና ጥይት ታመጣላችሁ በሚል ተቀስቅሰው ወደ ራያ የተላኩት ወጣቶች የሰፈሩበትን ቦታ መረጃ በማቀበል በራያ ቆቦ ወረዳ ባይበዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንዲደመሰሱ ተደርጓል።

ከውስጥ በተሠጠ መረጃ በርካታ ወጣቶች እና የፅንፈኛው ፋኖ አባላት ህይወታቼውን እንዲያጡ ተደርጓል።

ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ድረስ ከወግዲ ወረዳ ከ40 በላይ ከቦረና ወረዳ ከ20 በላይ ከመሃል ሳይንት ከ15 በላይ የተገደሉ ሲሆን በርካታዎቹ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ይህ ሴራ በምሬ ወዳጆ፣ በፈንታሁን መኩዬ፣ በሀብታሙ ደምሴ፣ በብሩክ እና ጎሹ ታረቀኝ በሚባሉ ሴራ ጠንሳሾች በሄኖክ ኪዳኔ አስተባባሪነት ህወሃትን የሚቃወሙ ወጣቶች መርጦ ወደ ራያ እንዲሄዱ በማድረግ መልሰው መረጃ በመስጠት አስጨፍጭፈዋቸዋል።

በጀግናው መከላከያ አየር ሃይል እና ድሮን በርካታ ፋኖዎች ሆነ ብሎ በተቀነባበረ ሴራ በርካታ ፅንፈኞች ተደምስሰዋል።

የወሎ ህዝብ በወያኔ አታላይነት እና ከአብራክህ በወጡ ተላላኪዎች መከራህን አይተህ ያሳደካቸውን ልጆች እስከ መቼ እየገበርክ ትኖራለህ።

29/05/2026

የወሎ ህዝብ መቼም ቢሆን ለጽንፈኛ ቡድን ቦታ የለውም! 🔥

​ወሎ የዘመናት የአብሮነት፣ የፍቅርና የሰላም ተምሳሌት ነው። ማህበራዊ ትስስራችንን የሚያናጉ፣ ሰላማችንን የሚያውኩ እና አካባቢያችንን ወደ ኋላ የሚጎትቱ የትኞቹንም አይነት ጽንፈኛ ቡድኖችና አስተሳሰቦችን የወሎ ህዝብ አይቀበልም፤ ቦታም አይሰጥም!
​ምኞታችንና ትኩረታችን ሁልጊዜም ሰላም፣ ልማትና አንድነት ብቻ ነው! 💚💛❤️
​ #አንድነት #ልማት

28/05/2026

‹‹ምሬ ወዳጆ የሚመራው ኃይል እንደ ቅጠል ረግፏል›› መከላከያ ሰራዊት

በደቡብ ወሎ እና በሰሜን ወሎ የተንቀሳቀሰው የጽንፈኛው ምሬ ወዳጆ ቡድን እንደ ቅጠል እረግፏል።

ጀግናው መከላከያ ሰራዊትና ጥምር ጦር ለብልቦታል። ይሄን ዘራፉ ቡድን።

20/05/2026

ለሰፊው የደቡብ ወሎ ህዝብ፣
በደቡብ ወሎ ፋኖ በሚል ስም ለምትንቀሳቀሱ አመራርና አባላት፣

ጉዳዩ፦ መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ይመለከታል፦

በአማራ ክልል ላለፉት ሶስት አመታት በወያኔ የሴራ ፖለቲካ እና የህልውና ትግል በሚል ጭንብል በደራጁት የራያ ዳይናስቲ ተወላጆች ጥያቄ አለኝ ሽፋን የአማራን ህዝብ በሁለት ጎራ ጠላት እና ወዳጅ በሚል ከፍሎ እርስ በርስ ሲያባላ ቆይቷል።

ህዋታዊ አስተሳሰብን በአማራ ብሄርተኝነትን በማንቀንቀን አማራን ከኢትዮጵያዊነት ከፍታ በማውረደ የተዛባ የጦርነት ሴናሪዮ በመፍጠር ጦርነት ተጎትቶ በአማራ ክልል እንድቀሰቀስ አድርጓል።

የዘመናት የአማራ ጠል እና ደመኝነት በአዕምሮው በመቅረፅ በራሱ አስተሳሰብ የአማራን ህዝብ በማጥመቅ ለከፋ ማህበራዊ ቀውስ ዳርጎት ቆይቷል።

መከላከያ እና የዞኑ የፀጥታ ኃይል የአማራን ህዝብ ግንዛቤ እንዲወስድ እና የጥሞና ጊዜ በመስጠት ረጂም ጊዜ የወሰደ ትግዕስት በማሳየት ጥንቃቄ ሲያደርግ ቆይቷል።

ይህንን ጥንቃቄ በድክመት የተመለከቱት የህወሃት ምንገድ መሪዎች የተሰጣቸውን የውክልና ጦርነት ተቀብለው ተወልደንበታል፣ አድገንበታል ባህል እና ወጉን እናውቀዋለን የቆምንልህ እኛ ነን በሚል የአማራን ህዝብ እግር ተወርች አስረው ዘርፈውታል፣ ገለውታለል፣ ሀብት ንብረቱን አውድመውብታል።
ከወንድም ኢትዮጵያውያን እንድነጠል አበክረው ሰርተውበታል።

ይህን ጨካኝ፣ ፅንፈኛ እና ዘራፊ ቡድን ለማጥፋተሰ ሠራዊታችን ሁሉንም እቅሞቹን በመጠቀም የኦፕሬሽን ስራ የሚሰራ መሆኑን አውቃችሁ በስህተት እና በአስገዳጅ ሁኔታ ይህንን ጠርዝ ረገጥ ሃይል የቸቀላቀላችሁ ወጣቶች ህይወታችሁን እና አካላችሁን ከጉዳት ትታደጉ ዘንድ እናሳስባችኋለን።

ወላጆች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች በዚህ አጥፊ ተግባር የተሰማሩ ወገኖችን በመምከር ከእኩይ ተግባራቸው እንድታቀቡ በአንፃሩ ወጣቶቹን ትርፍ ከማይገኝለት ሞት እና አካል ጉዳተኝነት ትታደጓቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ይህንን የተቀደሰ ሰላማዊ ጥሪ በማይቀበሉት ላይ ለሚወሰደው ጥብቅ እርምጃ ሃላፊነትና ተጠያቂነት የቡድኑ እና የግለሠቦቹ መሆኑን እናሳውቃለን።

የደቡብ ወሎ አስተዳደር እና ጥምር የፀጥታ ኃይል ኮሚቴ።

09/04/2026

ሰበር ዜና ‼️

በድርሳን ብርሀኔ የሚመራው የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂ በደቡብ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ ፀሃይ መውጫ እና በአልብኮ ወረዳ ነጢ በሚባል አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

02/04/2026

ሐሰተኛ መረጃን እንመክት! እውነት ያሸንፋል!

በደቡብ ወሎ ዞን ምንም አይነት ጽንፈኛ ቡድኑን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ አልተካሄደም። ህዝባችን ለሰላሙ፣ ለአንድነቱና ለደህንነቱ ዘብ የቆመ እንጂ ለጥፋት ኃይሎች አጀንዳ የሚመች አይደለም።

በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ የተቀነባበሩ ምስሎችና መረጃዎች የህዝቡን ትክክለኛ አቋም አይወክሉም።

​የሀሰት መረጃ አሰራጮች ሊገነዘቡት የሚገባው ሀቅ ቢኖር፣ የደቡብ ወሎ ህዝብ እውነትን ከሀሰት መለየት የሚችልና በተራ ፕሮፓጋንዳ የማይሸወድ መሆኑን ነው።

ሁላችንም መሰል የሀሰት መረጃዎችን በማጋለጥና እውነተኛውን መረጃ ለዓለም በማሳወቅ የህዝባችንን ገጽታ እንጠብቅ!

​ሐሰተኛ መረጃን እንመክት! እውነት ያሸንፋል!

25/03/2026

"ምርጫ ብሔራዊ ጥቅም የሚከበርበት ነው"

አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር

07/01/2026

ሰበር ዜና!!!

በላይነሽ አመዴ በከላላ እና በመቅደላ ወረዳ ጽንፈኛ ቡድኑን ከሰረቀው ዱቄት ጋር አመድ አድርጋዋለች።

Photos from Wollo Current Information's post 09/12/2025

የአማራ ክልልና የደቡብ የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሐይቅ ከተማና ተሁለደሬ ወረዳ የተውጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በወቅታዊ ሠላምና ልማት ዙሪያ እያወያዩ ነው።

በውይይቱም በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን እና የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስቻለው አላምሬ ናቸው የተገኙት።

08/12/2025

የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በለጋምቦ ወረዳ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ያደረጉት ውይይት፦

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa