Abreham
ምን ጊዜም ሳንጃው ✌️✌️✌️✌️✌️
15/01/2024
ቀጣይ ጨዋታ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ
ሐሙስ 12 ሰዓት
አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም
ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ
፦ሁለቱ ክለቦች ክለቦች ከተገናኙባቸው ያለፋት 6 ጨዋታዎች ፋሲል አራቱን ሲያሸንፍ በአንፃሩ የኛ ጊዮርጊስ ሁለት ጊዜ መርታት ችሏል።
፦በተደረጉት ጨዋታዎች ላይ 9 ግቦች ሲቆጠሩ ጊዮርጊስ 5 ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል። ከተደረጉት ጨዋታዎች አምስቱ 1-0 በሆነ ውጤት ሲያልቁ ጊዮርጊስ 4-0 ፋሲልን መርታተት የቻለበት ውጤት ከፍተኛው ግቦች የተቆጠሩበት ጨዋታ ነው።
፦በእርስ በእርስ ግንኙነታቸው 26 ካርዶች በዳኞች ሲመዘዙ 25ቱ ቢጫ ካርድ 12ቱ ለፋሲል 13 ደግሞ በጊዮርጊስ ተጫዋቾች ላይ ተመዟል። አንዱ ደሞ ቀይ ካርድ ሲሆን ለፉሲል ተጫዋች የተሰጠ ነዉ።
፦ፉሲል በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጋቸው ያለፋት አራት ጨዋታዎች ሁሉንም ማሸነፍ ሲችል ስምንት ጎሎችን አስቆጥሮ አንድ ብቸሠ ተቆጥሮበታል።በአንፃሩ ጊዮርጊስ በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ብቻ ሲሆን በሁለቱ አቻ ወጥቶ በአነዱ ሽንፈትን አስተናግዷል።አራት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሁለት ጎሎችን አስተናግዷል።
፦የሁለቱ ሀያላን ፋክክር በተለይም ከ ቅርብ አመታት ወዲሕ ቀልብን እየሳበ መቷል። እርሶስ ከዘሪሁን ሸንገታው ጊዮርጊስ እና ከውበቱ አባተ ስብስብ ማን ጨዋታውን በበላይነት የሚያጠናቅቅ ይመስሎታል? ግምት በኮመንት
፦በቀጣይ ደሞ የ ሁለቱን ቡድኖች የጨዋታ አቀራረብ ደካማና ጠንካራ ጎናቸውን ይዤ አመለሳለው።እስከዛው
share and follow
Ab Abreham
✌️✌️✌️ምን ጊዜም ሳንጃው ✌️✌️✌️✌️✌️
11/01/2024
የህ ጨዋታ ብቻ አደለም እብደትም ጭምር ነው።
what a game
የግል እይታ
1 ጊዮርጊስ ቤት ማንም ደፈር ብሎ ስለ ጨዋታው ሒደቶች ሲናገር አይስተዋልም። ለምን? እኔጃ.....በግሌ በተለይም ባለፋት አራት ጨዋታዎች ጊዮርጊስ ማግኘት ከነበረበት 12 ነጥብ የዛሬውንም ጨዋታ ጨምሮ ማለት ነወ ማሳካት የቻለው 5ቱን ብቻ ነው....አራት ጎል አስቆጥሮ(አራቱንም ያስቆጠረው አቤል ያለው ነው) 2 ጎል ተቆጥሮበታል ግን ሰባት ወርቃማ ነጥቦችን ጥሏል።
ለዚሕ ዋነኛው ምክንያቱ የብድኑ የማጥቃት አወቃቀር ነው። በተለይም ሞሰስን በቀይ ካጣ በኋላ ዘርዬ ይዟቸው ከሚገባው ሶስቱ አጥቂዎች ሁለቱ ማለትም ተገኑ እና ቢንያም ከአጨዋወት እስታይላቸው አንፃር በማጥቃቱ ረገድ እየሰጡ ያሉት ጥቅም እምብዛም በመሆኑ አቤል እጅጉን እንዲጋለጥ አድርጎታል። በተለይም የተቃራኒ ቡድን ሳጥን ውስጥ ብቻውን መገኘቱ ለተቃራኒ ተከላካዮች እንዲመች ሆኗል። ለዛም ጎሎችን አላስቆጠረም አቤል ካላገባ ደሞ በተገኑ ወየም በቢንያም ጎሎችን ማግኘት ከባድ ነው ያደሞ ቡድኑን ውጤት እንዲያጣ እያደረገው ነው። በተጨማሪም አቤል አጠገቡ ሆኖ የሚያግዝ አጥቂ አለመኖሩ ልጁን ላስፈላጊ እሩጫዎች እና ጫናዎች ሲዳርገው እያየን ነው ይህ ደሞ ከነበረበት ተደጋጋሚ ጉዳት አንፃር ሌላ ጉዳት እንዳይዳርገው እፈራለው።
ዘርዬም ይሕንን አይቶ በተለይም በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ሞሰስን መልሶ ማግኘቱ እና የአማኑኤል ተቀያሪ ላይ በመኖሩ የማጥቃቱን ችግር ቀርፎ እና አቤል ለላይ ያለውን ሸክም ቀንሶ እንደሚመጣ ተስፉ አለኝ።
2 የቅዱስ ጊዮርጊስ ኦፊሺያል ፔጅ ጎሎችን ከመናገር ውጪ ስለ ጨዋታው እንቅስቃሴ፣ስለ ተቀያሪዎች፣የተጫዋቾች ጉዳት፣በጨዋታ እንቅስቃሴ ሰለሚሰጡ ካርዶች ባጠቃላይ ከውጤት ውጪ ሌላውን የሚፅፍ ሰው የለም በቃ። DStv የከዳውን ደጋፊ አብራቹ ትከዱታላቹ በቦታው ያልተገኘ ደጋፊ ስለ ጨዋታው አይመለከተውም በቃ...የሚገርም ነው።
አስተያየት መስጠት ይቻላል share....follow እንደራረግ
የኔ ሳንጃው ....ማሸነፍ ብቻ
ጊዮርጊስ ከ መቻል
የጨዋታው ውጤት 1-1ሆኖአል
ጊዮርጊስ በአቤል ያለው ጎል 1 ነጥብ አግኝቷል።ዛሬም ጎል አስቆጣሪው አቤል ያለው ነው። ባለፋት 3 የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች የዛሬውን ጨመሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ግቦችን ማስቆጠር ሲችል፤አራቱንም ያስቆጠረው አቤል ያለው ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘንድሮ ውጤቱ ባአብዛኛው በአቤል ጎሎች ላይ ጥገኛ ነው ሊባል ይችላል። ይሕ ነገር እስከመቼ ሊቀጥል ይችላል? ሀሳባችሁን በኮመት.........
በእኔ እይታ ቡድኖች የአቤልን እንቅስቃሴ መቆጣጠር በቻሉባው ጨዋታዎች ላይ ጊዮርጊስ ጎል ማስቆጠር ሲቸገር እያየን ነው።ለዚህ ደሞ ከቡና ጋር የነበረው ጨዋታ በቂ ማሳያ ነው። በተለይም ከሞሰስ ቀይ ካርድ በኋላ አቤል በጨዋታዎች ላይ ብቻውን ረጃጅም እና አላስፈላጊ ሩጫዎችን ሲያደርግ እያየን ነው።የዚህ ምክንያቱ ደሞ ከአጠገቡ የሚጫወቱት ቢንያም እና ተገኑ ማጥቃቱ ላይ እምብዛም ወደፊት ተጠግተው እያገዙ አለመሆኑ ይመስለኛል።ይህ ደሞ በተለይም ከልጁ ያለፈ የጉዳት ሪከርዱ ጋር በቀላሉ ለሌላ ጉዳት እንዳያጋልጠው ያሰጋኛል።
የግለ እይታ ነው። ሰለጊዮርጊስ እንወያይ የሀገራችን እግር ኳስ ላይ አዲስ ነገር እንጨምር።