Alex Sheger
Alex Sheger Ethiopian artist
singer & Writer
እግዚአብሔር ፍትህን ሲያሰፍን ሞትን ያክል መልካም ነገር ምድር ላይ ማኖሩ። ሞት ባይኖር ኖሮ ከአንዳድ ሠው መሠል አውሬዎች ጋር እየኖርን ምን ይውጠን ነበር? እንዴትስ እንሆን ነበር?
Alex Sheger
01/08/2026
'ድው
ድም
ድው
ዷ!
ዝም
ጭጭ
እ.ሪ.ታ!
ማንነቱ ያልታወቀው ገጣሚ ጦርነትን ባጭሩ የገለፀበት መንገድ ነው አሉ…………
' ያሬዲና 💚💛❤ ( Zema Yared) ትችላለህ የሸገሩ!
💚💛❤
አሌክስ ሸገር
💚💛❤
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
እኔ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ ነገር ግን በራሴም ሆነ የትኛውም እምነት ውስጥ የመሸጉ አስመሳይ ነጋዴዎች፡ እራስ ወዳድ ሌቦችና በጥላቻ ያበዱ ዘረኛና ቀማኛ አክራሪ ነብሠ በላዎች በፍፁም አይመቹኝም።
በምትኩ እንዲህ እንደ ፓስተር ቸሬና ነፍሳቸውን ይማርናልን እና ልክ እንደ ሃጂ ሙፍቲ ከጥላቻ ይልቅ መልካም መልካሙን የሚሠብኩ የሃይማኖት አባቶችን እና መሪዎችን ሳይ ደስ ይለኛል ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉም ጆሮዬንም እሠጣቸዋለሁ።
ማሳሠቢያ :-
ፓስተር ቸሬን በቅርበት አላውቀውም እውቅናም የለንም፣ ከዚህ በፊት መጥፎ ሠው ይሁን ጥሩ ሠው የቀድሞ ታሪኩንም ምንም አላውቅም እንዲሁ ብቻ ሠሞኑን ማህበራዊ ሚዲያ ላይና ዩቱብ ላይ የተወሠኑ መልካምና የማምንባቸውን እውነት አዘል ትምህርቶች እና የምከተላቸውን የሂወት ፍልስናዬን ሲያስተምር ስላየሁትና ስለተመቸኝ ብቻ ነው እናንተም ብትሠሙት ትወዱታላችሁ ብዬ ያጋራኋችሁ ።
ፓስተር ቸሬ በዚሁ ቀጥል ፈጣሪ ፍፃሜህን ያሳምረው
ቃለ ሂወት ያሰማልን🙏
አሌክስ ሸገር
💚💛❤
ኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
19/07/2026
ከስሜታዊ ደጋፊነት ወጣ ብለን አርጄንቲና እና ሊዮኔል ሜሲ ዛሬ ዋንጫውን እንዲያነሱ ካስፈለገ አሰልጣኝ ስካሎኒ ከነኚህ ሶስት በቂ እረፍት ካገኙ ጥበበኞች መሃል ቢያንስ አንድ ሁለቱን በቋሚነት አሊያም ቀይረው በማስገባት በተከታታይ በሶስት ጨዋታዎች ከአምስት ሠአት ያላነሰ ጨዋታዎች በማድረጉ ምክንያት የተዳከመውን መሃል ክፍላቸው ላይ ፈጠራ ፣ፍጥነትና ጥንካሬን ወይም ጉልበት በመጨመር ሜሲን በሚገባ እንዲያግዙት ማድረግ ይኖርበታል።
አሊያ እንደከዚህ በፊቱ ሠዶ በማሳደድ አይነት ጨዋታ
አሸንፌ ዋንጫ አነሳለው ብሎ ካሰበ ሁሌ ፋሲካ የለምና የሚሆን አይመስለኝም። ምክንያቱም ስፔኖች እንግሊዞች የሠሩትን በተለይም አሠልጣኝ ቶማ ቱሄል የሠራውን ስህተት በፍፁም አይደግሙትም ቀድመው ጎል ካስቆጠሩ ኳሱን ይዘው ጨዋታውን በደንብ መቆጣጠር የሚችሉ ተጫዋቾችና አስፈላጊ ከሆነም ደግመው ጎል ማስቆጠር የሚችሉ ከበቂ በላይ ተጫዋች በብዛት ይዘዋልና በዛ ላይ አሠልጣኛቸው ዴላ ፋንቴ በፖዚሽን ኳስም ሆነ በታክቲክ እውቀቱ ከስካሎኒ የተሻለና ከዚህ በፊትም አስተማሪው የነበረ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
እኔ ሎሳልሶ ወይም ኒኮ ፓዝ ከሁለት አንዳቸው ዛሬ በቋሚነት ቢጀምሩ ደስ ይለኛል ቫለንቲን ባርኮም ተቀይሮ የመግባት እድሉን ቢያገኝ ቅር አይለኝም ብቻ ከሶስቱ አንዳቸው ዛሬ መጫወት አለባቸው ባይ ነኝ።
እናንተስ? ማን በቋሚነት ቢጀምር ወይም ተቀይሮ ቢገባ ትመርጣላችሁ እስቲ አስተያየታችሁን አስፍሩልኝ
ድል ለልጅነቴ አርጀንቲና🇦🇷 እና ንጉስ ሊዮኔል ሜሲ!
አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
18/07/2026
ደረጄ ይበይን ከንቲባው ውድ ወንድሜ አንተ መልካም ሠው አልሞላልኝ ብሎ እንጂ ሁሌም በልቤ አስብሃለሁ።
ዛሬ ደግሞ ስልኬ በዚህ መልኩ አስታወሠክ ፈጣሪ ከመከራው ቤት አስፈትቶህ ከቤተሠቦችህ ጋር በሠላም በጤና እንዲያኖርህ እመኛለሁ።
ውድ ወንድምህ
አሌክስ ሸገር
ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ
"እግዚአብሔር ይመስገን
ሜሲን የኛ ያረገ አምላክ
💕🙏💕
ኮች ስካሎኒ እባክህ እስካሮኒ አትሁንብን መሃላይ አዲስ ሃይል ጨምር ኒኮ ፓዝ አልሜዳ ሊሳልሶን መቼ ልትጠቀማቸው ነው ማካሊስተር፡ኢንዞ፡ሲሞኒ የግድ መቀየር አለባቸው ሊቻም ቀይ እንዳያ ያሰጋኛል