Orthodox Light
ይህ ገጽ፡-
የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያንን እምነት ሥርዓትና ትውፊት
የምንማማርበት
ዐውደ ምሕረት ነው።
ብስራታዊ ❤️❤️
ቅዱስ ሚካኤል ❤️
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!
ቅዱስ ሚካኤል የእግዚአብሔር ታላቅ መልእክተኛ፣ ለምእመናን ደግሞ የቅርብ ረዳትና ጠባቂ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እርሱን የረዳትነት ሚናውን ሲገልጽ እንዲህ ይለናል፦
"በዚያን ዘመን ስለ ወገንህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ... በዚያን ዘመን ከሕዝብህ ወገን በመጽሐፉ ተጽፈው የተገኙት ሁሉ ይድናሉ።" (ት. ዳንኤል 12፡1)
ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር በተሰጠው ሥልጣንና ፍቅር፣ በችግር ጊዜ የሚደርስ፣ የሚታደግና የሚረዳ የሰማያዊ ሠራዊት አለቃ ነው። እኛም በአማላጅነቱና በረዳትነቱ ታምነን፣ እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅድስና በመኖር ከበረከቱ ተካፋዮች እንሁን።
የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን!
#ቅዱስሚካኤል #የሊቀመላእክትበዓል #ኦርቶዶክስ #ረዳት #ተራዳኢ #ለዘላለምይኑር
«እግዚአብሔርን፦ አንተ አምላኬ ነህ፤ አቤቱ፥ የልመናዬን ቃል ስማ" ❤️❤️
ቅድስት ሥላሴ❤️
አምላካችን በአንድነቱና በሦስትነቱ፣ በፍቅሩና በምሕረቱ ሁሌም ከእኛ ጋር ይሁን። የቅድስት ሥላሴ በረከት፣ ሰላም እና ጥበቃ በቤታችን፣ በሥራችን እና በኑሮአችን ሁሉ አይለየን።
አምላካችን በቸርነቱ ይጠብቀን!
"ጌታዬ አንተ አምላክ ጠባቂዬ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ" ❤️❤️
መንገዱ ቢጠብብም፣ ውጣ ውረዱ ቢበዛም፣ የምንፈራው ነገር የለም። በሁሉም መንገዳችን መድሃኒዓለም አለና። ሁሉን በቸርነት የሚያሳልፍ እርሱ ይባረክ! 🙏❤️
27❤️
✝️❤️❤️
ቅዳሴ ስዑር ✝️
Contact the place of worship
Website
Address
Addis Ababa
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Orthodox Light posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.