Promote Silte

Promote Silte

Share

የስልጤ ብሔረሰብን ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋና የቱሪስት መስህቦች እንዲሁም አጠቃላይ ገጽታን ለአለም የምናስተዋውቅበትና ልምድ የምናጋራበት ነው።

Photos from Promote Silte's post 05/07/2026

ለስልጤ የማንነት ታጋይ ለሀሰን ኢብራሂም የገራድነት ማዕረግ የመስጠት ሥነ-ሥርዓት በድምቀት ተካሄደ!

በስልጤ ዞን ​በሚቶ ወረዳ የስልጤ ሕዝብ የማንነትና የልማት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና ላበረከቱት ታዋቂው የማንነት ታጋይ ሀሰን ኢብራሂም የላቀ የባሕላዊ አመራርና የክብር መገለጫ የሆነው የገራድነት ማዕረግ የመስጠት ፕሮግራም ተካሂዷል።

የሚቶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር መሀመድ ​"ታጋይ ሀሰን ኢብራሂም የስልጤ ህዝብ በታሪኩ ውስጥ የራሱን አሻራ አሳርፎ፣ ማንነቱ ተከብሮና መብቱ ተረጋግጦ ዛሬ ለደረሰበት የልማትና የዕድገት ምዕራፍ እንዲበቃ ካደረጉ እውነተኛ የህዝብ ልጆች መካከል አንዱና ግንባር ቀደሙ በመሆናቸው ማዕረግ ለሰሩት ታላቅ ሥራና ለከፈሉት መስዋዕትነት የሚመጥን ተገቢ እውቅና ነው፤"ብለዋል።

​ታጋይ ሀሰን ኢብራሂም የስልጤ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ምላሽ እንዲያገኝ፣ እንዲሁም ሕዝቡ የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን መብቱ ተከብሮ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር በነበረው ረጅም የትግል ጉዞ ውስጥ የማይተካና ታሪካዊ ሚና የነበራቸው መሆኑ ተገልጿል።

የታጋይ ሀሰን ኢብራሂም የገራድነት ማዕረግ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት፣ ወጣቱ ትውልድ ለማኅበረሰቡና ለሀገር ዕድገት በታማኝነት፣ በቅንነትና በቁርጠኝነት ማገልገል እንዳለበት ትልቅ የሕይወትና የሞራል ትምህርት ያስተላለፈ ክስተት መሆኑ ተገልጿል።

ታሪክ የማይረሳው ሥራ የሠሩ ባሕላዊና ማኅበራዊ መሪዎችን ማክበር የነገውን ትውልድ ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳ መሆኑም ተጠቅሷል።

Photos from Promote Silte's post 04/07/2026

በጦራ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የደሩል-ሰላም አካዳሚ ሲያስተምራቸው የነበሩ 115 የኬጂ ሶስት ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

Photos from Promote Silte's post 04/07/2026

በአልቾ ውሪሮ ወረዳ በኩተሬ ከተማ የተቋቋመው ፈረጃት አካዳሚ ለተከታታይ አመታት ሲያስተምራቸው የቆዩ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎችን የተማሪ ቤተሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

‎የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የፈረጃት ማህበር ሰብሳቢ አቶ ኑራዲን ረሻድ ማህበሩ ‎ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት እየሰራ ይገኛል በማለት ዛሬ ለምርቃት የበቃችሁ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች እንኳን ደስ ኣላችሁ ብለዋል።

Photos from Promote Silte's post 04/07/2026

በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የሚገኘው በድሪያ መዋለ ህፃናት ትምህርት ቤት በ2018 የትምህርት ዘመን በኬጂ ሶስት (KG3) ደረጃ ሲያስተምራቸው የቆዩ 46 ተማሪዎችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

Photos from Promote Silte's post 04/07/2026

በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ቂልጦ ከተማ የሚገኘው ረሂቀል መኽቱም አካዳሚ በ2018 የትምህርት ዘመን በKG-3 ደረጃ ሲያስተምራቸው የነበሩ 69 ተማሪዎችን ዛሬ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።

የቀለም ትምህርታቸውን የጀመሩበትን ይህንን የመጀመሪያ ምዕራፍ በስኬት እና ደስታ አጠናቅቀው ለዚህ በመብቃታችሁ ​ለተማሪዎች፣ ለወላጆች እና ለመላው የአካዳሚው ቤተሰብ እንኳን ደስ አላችሁ!

Photos from Promote Silte's post 02/07/2026

ጂኦፓርክ (Geopark) ምንድን ነው? 🌍✨
​📍አንዳንዴ ስለ መሬት አቀማመጥ፣ ስለ ተራሮችና ድንጋዮች ታሪክ ቆም ብለው አስበው ያውቃሉ? ጂኦፓርክ ማለት ይህንን አስደናቂ የተፈጥሮ ታሪክ የሚነግረን ልዩ ቦታ ነው!

​ለመሆኑ ጂኦፓርክ ምን ማለት ነው?
📍ጂኦፓርክ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) እውቅና የሚሰጠው፣ ልዩና አለምአቀፍ የጂኦሎጂካል (የመሬት አቀማመጥ) እሴት ያለው ነተከለለ እና የተጠበቀ አካባቢ ነው።

🔑ነገር ግን ነገሩ ስለ ድንጋዮችና ተራሮች ብቻ አይደለም፤ ጂኦፓርክ የሚከተሉትን ሶስት ወርቃማ ነገሮች አጣምሮ የያዘ ነው፡-

➥ የመሬት ታሪክ (Geology): በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዓመታት መሬት እንዴት እንደተገነባች የሚያሳዩ አስደናቂ ዋሻዎች፣ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ውጤቶች እና ልዩ የዓለት ቅርጾች።

➥ ተፈጥሮና ባህል (Nature & Culture): በአካባቢው የሚገኙ ብቅቅ ሰብአዊ ታሪኮች፣ ባህሎች እና ብዝሃ-ህይወት (ዕፅዋትና እንስሳት) ከጂኦሎጂው ጋር እንዴት ተሳስረው እንደሚኖሩ ያሳያል።

➥ የአካባቢው ማህበረሰብ እድገት (Sustainable Development): የአካባቢው ህዝብ ተፈጥሮን ሳይጎዳ በቱሪዝም (Eco-tourism) እና በተለያዩ ስራዎች እንዲጠቀምበትና እራሱን እንዲችል ያደርጋል።

​✍️በአጭሩ ጂኦፓርክ ማለት "የመሬትን ታሪክ እያነበብን፣ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተን የምንኖርበትና የምንማርበት ክፍት የሰማይ ስር ሙዚየም" ነው።

​⚠️ኢትዮጵያችንም ገና ያልተነኩና ለጂኦፓርክነት የሚመጥኑ በርካታ አስደናቂ የተፈጥሮ ድንቆች ባለቤት ናት!✨



Via👉 Abdulmejid Nuredin

Photos from Promote Silte's post 01/07/2026

ከስጦታዎች ሁሉ በላጩ ስጦታ፤ የደም ልገሳ!

​የማይተካውን ህይወት ለመታደግ የሚተካውን ደም መለገስ ትልቅ የህሊና እርካታ ከሚያስገኙ ቅዱስ ተግባራት መካከል ዋነኛው ነው።

28/06/2026
Photos from Promote Silte's post 27/06/2026

ኬራቴ ከተማ በምሽት!!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መቀመጫ ለሆኑ ከተሞች ማዕከል የሆነችው ኬራቴ ከተማ የምሽት ድባቧ እንዲህ ያምራል።

በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ኬራቴ ከተማን ከሀላባ - ወራቤ፣ ከሆሳዕና ወራቤ፣ ከአዲስ አበባ- ሆሳዕና እና ሀላባ/ወላይታ ሶዶ ለማቋረጥ መርገጥ የግድ ነው።

ከተማዋን ከፍ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ጀምሮ በመጨረስ መርህ የተሰራው የኬራቴ የመንገድ ዳር ማብራት ደግሞ ሌላ ገፅታዋን ገልጦላታል።

Photos from Promote Silte's post 27/06/2026

በህግ ትምህርት ዘርፍ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ነዲያል ነስሮ- የስኬት ጉዞ እና የወደፊት ተስፋ

በወራቤ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ከተመረቁት ተማሪዎች መካከል በህግ ትምህርት (School of Law) ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነችው ነዲያል ነስሮ፣ ለስኬቷ ምስጢር የሆነውን ጥረትና የወደፊት ራእይዋን አጋርታናለች።

ነዲያል በትምህርቷ 3.89 የሆነ ከፍተኛ ውጤት (GPA) በማስመዝገብ ነው ይህንን ክብር ለመቀዳጀት የበቃችው።

ስኬቷ ከሁሉም በላይ በፈጣሪ እርዳታ የተገኘ መሆኑን በመጥቀስ "አልሀምዱሊላህ" በማለት ምስጋናዋን አቅርባለች።

በተጨማሪም ለደረሰችበት ደረጃ የቤተሰቦቿ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ገልጻ በተለይም ለእናቷና ለመላው ቤተሰቦቿ ያላትን ጥልቅ አክብሮትና ምስጋና ገልጻለች።

"ትለፋለህ፣ ትጥራለህ፣ ታጠናለህ፤ ግን ምንም ቢሆን ከላይ ካልተሰጠህ ከየትም አይመጣም" ስትል የስኬት ቀመር በትጋትና በፈጣሪ ረዳትነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን አስረድታለች።

ስለ ወደፊት እቅዷ የተጠየቀችው ወጣቷ ህግ ባለሙያ፣ ትምህርቷን እዚህ እንደማታበቃ ገልጻለች።

ከዲግሪ ወደ ማስተርስ እንዲሁም እስከ ዶክትሬት (PhD) ድረስ የመጓዝ ትልቅ ህልም እንዳላት ተናግራለች።

ዋና ዓላማዋም በትምህርት ያገኘችውን እውቀት ተጠቅማ "በሀገራችን ያለውን የህግ ክፍተቶች ለመሙላትና ለማስተካከል" እንደሆነ በልበ ሙሉነት ገልጻለች።

በመጨረሻም ለተመራቂ ጓደኞቿ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፈችው ነዲያል በቤት ሆነው ለሚከታተሏትና በጸሎት ለሚያስቧት ቤተሰቦቿ በድጋሚ ምስጋናዋን አቅርባለች።

የነዲያል ነስሮ ስኬት ለሌሎች ሴት ተማሪዎችና ለወጣቶች በትጋት ከሰሩ የማይደረስበት ግብ እንደሌለ ትልቅ ማሳያ ሆኖ አልፏል።

Want your business to be the top-listed Event Planning Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Woraby
Addis Ababa