WMCC

WMCC

Share

AddisWalta - AW
አዲስ ዋልታ
Walta Media and Communication Corporate Who We Are
Walta Media and Communication Corporate S.C.

(WMCC) is a broadcast media company based in Addis Ababa, the political capital of Africa. The company which owns TV and Radio Stations aspires to become a pan African media company currently disseminating information in local and international languages. Walta has built its reputation through covering all aspect of Ethiopia and beyond in its professional news, documentary and programs reporting.

09/06/2026

የፖሊሲ ጉዳይ ቅኝት - ሰኔ 2፣ 2018 ዓ.ም

09/06/2026

የዓለም ዋንጫ ማሸነፍ የቻሉ ሀገራት…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፈረንጆቹ 1930 ጀምሮ መደረግ በጀመረው በዓለም ዋንጫ ውድድር ስምንት ሀገራት ብቻ ዋንጫውን ማሳካት ችለዋል፡፡

በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብራዚል አምስት ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን÷ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫውን ያሳካችው በፈረንጆቹ 1958 ነበር፡፡

ከዚያ በመቀጠል በፈረንጆቹ 1962 ሻምፒዮን በመሆን በተከታታይ ዋንጫውን አሳክታለች፡፡

እንዲሁም በ1970፣ 1994 እና 2002 ሻምፒዮን በመሆን በመድረኩ አምስት ጊዜ ዋንጫውን በማሳካት ቀዳሚዋ ሀገር ናት፡፡

ከብራዚል በመቀጠል የዓለም ዋንጫን ብዙ ጊዜ ማሳካት የቻሉት ጀርመን እና ጣሊያን ናቸው፡፡

ሁለቱም ብሔራዊ ቡድኖች በተመሳሳይ አራት ጊዜ ሻምፒዮን ሆነዋል፡፡

ጣሊያን በፈረንጆቹ 1934 ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን ስትሆን÷ በድጋሚ በ1938 ዋንጫውን በማሳካት በተከታታይ ሻምፒዮን ለመሆን በቅታለች፡፡

እንዲሁም በፈረንጆቹ 1982 ለሦስተኛ ጊዜ ያሸነፈች ሲሆን÷ ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ያሳካችው በፈረንጆቹ 2006 ነበር፡፡

የአራት ጊዜ የመድረኩ አሸናፊዋ ሀገር ጣሊያን የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ጨምሮ ለተከታታይ ሦስተኛ ጊዜ ከውድድሩ ውጪ የሆነች ሲሆን÷ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 2014 ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ ማጣሪያውን ማለፍ ባለመቻሏ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ከመድረኩ ውጪ ሆናለች፡፡

ሌላኛዋ አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያሸነፈችው ሀገር ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን የሆነችው በ1954 ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ በፈረንጆቹ 1974፣ 1990 እና 2014 ላይ በመድረኩ ሻምፒዮን መሆኗ ይታወሳል፡፡

የደቡብ አሜሪካዋ ሀገር አርጀንቲና ደግሞ ሦስት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማሳካት ችላለች፡፡

አርጀንቲና ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማሳካት የቻለችው በፈረንጆቹ 1978 እንደነበር ይታወሳል፡፡

በፈረንጆቹ 1986 ለሁለተኛ ጊዜ ሻምፒዮን ከሆነች በኋላ ከ36 ዓመታት ጥበቃ በኋላ በ2022 ለ3ኛ ጊዜ ማሸነፏ ይታወሳል፡፡

ፈረንሳይ እና ዩራጋይ ደግሞ በተመሳሳይ ሁለት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማሳካት የቻሉ ብሔራዊ ቡድኖች ናቸው፡፡

ዩራጋይ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ውድድር ያሸነፈች ሲሆን÷ ወቅቱም በፈረንጆቹ 1930 ነበር፡፡

የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ውድድር ያሸነፈችው ዩራጋይ በወቅቱ ውድድሩን ያዘጋጀችው ራሷ እንደነበረች ይታወሳል፡፡

ዩራጋይ ከዚያ በኋላ በፈረንጆቹ 1950 በድጋሚ ዋንጫውን ማንሳቷ አይዘነጋም፡፡

ፈረንሳይ በፈረንጆቹ 1998 እና 2018 ሻምፒዮን በመሆን በመድረኩ ሁለት ጊዜ ከዋንጫው ጋር ተገናኝታለች፡፡

እንግሊዝ እና ስፔን ደግሞ በተመሳሳይ አንድ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ማሳካት ችለዋል፡፡

እንግሊዝ በፈረንጆቹ 1966 ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ያሳካች ሲሆን÷ በወቅቱም የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር ራሷ ነበረች፡፡

ከዚያ በኋላ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በመድረኩ ሻምፒዮን መሆን አልቻለም፡፡

ስፔን በፈረንጆቹ 2010 ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪኳ ሻምፒዮን መሆኗ ይታወሳል፡፡

የፊታችን ሐሙስ በሚጀምረው የ2026 ዓለም ዋንጫ አዲስ ሀገር ሻምፒዮን ይሆናል ወይስ ከዚህ ቀደም ካነሱ ሀገራት መካከል አንዱ ሻምፒዮን ይሆናል የሚለው ይጠበቃል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

08/06/2026

ሀገራዊ ምክክር እና ሀገር በቀል የእርቅ ዕሴቶች...

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት፣ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር እንዲሁም ታሪካዊና መዋቅራዊ ቅሬታዎችን በውይይት ለመፍታት ታላቅ የብሔራዊ ምክክር ሂደት እያካሄደች ትገኛለች።

የዚህ ጉዞ ስኬት የሚወሰነው ከውጭ በሚቀዱ የፖለቲካ ቀመሮች ሳይሆን ማህበረሰቡ ለዘመናት ጠብቆ ባቆያቸውና ከማንነቱ ጋር በተሳሰሩ የሰላምና የዕርቅ ዕሴቶች ላይ መመስረት ሲችል ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሔረሰቦች የሚኖሩባት የባህልና የማንነት ሕብረቀለም እንደመሆኗ መጠን እያንዳንዱ ማህበረሰብ ግጭቶችን የሚፈታበት፣ ፍትህን የሚያሰፍንበት እና የተናጋ ማህበራዊ ትስስርን የሚያድስበት የራሱ የሆነ ሀገር በቀል የዕርቅ ሥርዓት አለው።

ከእነዚህ ውድና ሕያው ማህበራዊ ዕሴቶች መካከል በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የደራሼ ብሔረሰብ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት “ደሃ” ተጠቃሽ ነው።

በደራሼ ማህበረሰብ ዘንድ “ደሃ” ወይም ሽምግልና ማለት እንዲሁ ግጭት ሲከሰት ብቻ የሚደረግ የጊዜያዊ ስምምነት ሂደት አይደለም። ይልቁንም ፍትህ የሚረጋገጥበት፣ የበደለ የሚጠየቅበት፣ የተበደለ የሚካስበትና ጠቅላላው ማህበራዊ ኑሮ ሕጋዊና ሞራላዊ እውቅና የሚያገኝበት ጠንካራ ዕሴት ነው።

ይህንን ሥርዓትን የሚመሩትና የሚያስፈጽሙት መሪዎች “ካዳያ” በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ መሪዎች የሚመረጡት በማህበረሰቡ ሕገ-ህሊና ውስጥ ባሉ ጥብቅ መስፈርቶች ሲሆን÷ የካዳያዎች የሥልጣን ዘመን ሁለት ዓመት ብቻ ነው።

ይህ የሚያሳየው በባህላዊ ሥርዓት ውስጥ የሥልጣን ሽግግርና ለሌሎች ዕድል የመስጠት የዴሞክራሲ መርህ ቀድሞውኑ የነበረ መሆኑ ነው።

የደራሼ የዕርቅና የፍርድ ተግባር የሚከናወነው የማህበረሰቡ መረጃ የሚለዋወጥበት፣ ወጣቶችና አዛውንቶች የሚገናኙበት ዋነኛ ማዕከል በሆነው “ሞራ” በሚባል ጥላ በሚሰጡ ታላላቅ ዛፎች ሥር ድንጋዮች እንደ እርከን ከፍ ተደርገው በተዘጋጁ የሸንጎ ስፍራዎች ላይ ነው።

በደራሼ ባህል ሞራ ላይ ተከስሶ መቆም ትልቅ ማህበራዊ ውርደት ተደርጎ ይቆጠራል። ይህ ማህበራዊ ሞራል ሰዎች ወንጀልና ጥፋት ከመስራታቸው በፊት ራሳቸውን እንዲገቱ ያደርጋቸዋል።

የደሃ የዳኝነት ሂደት ፍፁም ሰላማዊና ሥርዓታዊ ሲሆን÷ ተበዳዩ አቤቱታውን ካቀረበ በኋላ ተከሳሹ በምስክሮች ፊት እንዲቀርብ ይጠራል። ተከሳሹ የቀረበውን ጥሪ አሻፈረኝ ካለ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር ማህበረሰባዊ ማዕቀብ ይጣልበታል።

በዳዩ በጥፋቱ ካመነ ደግሞ ሌላው አስደናቂ እሴት ይታያል፤ የካሳውን ክፍያ ጥፋተኛው ግለሰብ ብቻውን ሳይሆን የጎሳው አባል በሙሉ አዋጥቶ እንዲከፈል ይደረጋል።

ይህ እኔነትን ወደ እኛነት የሚቀይርና የአንዱ ጥፋት የሁሉንም ትኩረት እንዲስብ የሚያደርግ የጋራ ኃላፊነት መገለጫ ሲሆን÷ ዕርቁ የሚደመደመው ፍፁም ማህበራዊ ትስስርን በሚያድስ ታላቅ በዓል ነው።

ለዕርቁ ማሳረጊያ የሚሆን “ጨቃ” የተባለው ባህላዊ መጠጥና ምግብ የሚዘጋጀው የጎሳ አባላት እህል አዋጥተው በጋራ በመሥራት ነው።

በዕርቁ ቀን ከተበዳይና ከበዳይ ወገን የመጣው ምግብና መጠጥ አንድ ላይ ተደባልቆ በአንድ ማዕድ ይበላል። ፅዋቸውን ካነሱበት ሰዓት ጀምሮ ቁርሾው ሙሉ በሙሉ ተረስቶ ቀኑን በደስታ ያሳልፋሉ።

የደራሼ “ደሃ” ሥርዓት አሁን ኢትዮጵያ ለጀመረችው ብሔራዊ የምክክር ሂደት እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ስልቶችንና ፍልስፍናዎችን ማበርከት ይችላል።

የዘመናዊው የፍትህ ሥርዓት ጥፋተኛውን መቅጣት ላይ ብቻ ሲያተኩር÷ የደሃ ሥርዓት ግን ትኩረቱ የተበላሸውን ግንኙነት ማደስ ላይ ነው።

ሀገራዊ ምክክሩም እንደ ደራሼ ዕርቅ ሥርዓት ይቅርታንና ማህበራዊ ፈውስን ማምጣት ላይ ሊያተኩር ይገባል።

ዘመናዊነት ማለት የራስን መልካም እሴት መጣል ሳይሆን ባለው ሀገር በቀል እውቀት ላይ ሳይንሳዊ ጥናት በማድረግ እሴት መጨመር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም ሆነ መላው ሕዝብ እነዚህን ሕያው የሆኑ የባሕል ዕሴቶችን ለሀገራዊ መግባባት ሊጠቀምባቸው ይገባል።

የደራሼ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት የሚያስተምረን ታላቅ እውነት ቢኖር ችግሮቻችንን እኛው ራሳችን በራሳችን መድረክ በጥበብና በፍቅር መፍታት እንችላለን የሚለውን ዘላለማዊ ሀቅ ነው።

Photos from WMCC's post 08/06/2026

በኮሪደር ልማት የተዋበችው ወልድያ ከተማ በምስል፡-

Photos from WMCC's post 08/06/2026

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ሕብረት የእኩልነት፣ ዝግጁነትና ክራይስስ ማኔጅመንት ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ሕብረት የእኩልነት፣ ዝግጁነት እና ክራይስስ ማኔጅመንት ኮሚሽነር ሀጃ ላህቢብ ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት÷ አውሮፓ ሕብረት ከዓለም አቀፍ የጤና እክሎች ጋር በተያያዘ በተለይም በቅርቡ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመከላከል ለተደረገው ጥረት ላሳየው አጋርነትና ድጋፍ አመስግነዋል።

ሕብረቱ ለአፍሪካ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል የሰጠው ድጋፍ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ዓለም አቀፍ ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል ወሳኝ ርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በአፍሪካ ቀንድ ስላለው ሰላምና ደህንነት ሁኔታ ማብራሪያ መስጠታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ኮሚሽነር ሀጃ ላህቢብ በበኩላቸው÷ የአውሮፓ ሕብረት ከአፍሪካ ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከርና በጋራ የጤና እና የሰብዓዊ ቀውሶች ዙሪያ በቅንጅት ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ? 08/06/2026

ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ? #ፋና #ኢትዮጵያ

Photos from WMCC's post 08/06/2026

ወደ አዲስ የትብብር ምዕራፍ ያደገው የቻይና - ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና እና ሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ግንኙነት ወደ አዲስ የእድገትና የትብብር ምዕራፍ ተሸጋግሯል አሉ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ከሰባት ዓመታት በኋላ ዛሬ ወደ ሰሜን ኮሪያ ያቀኑ ሲሆን÷ በፒዮንግያንግም በሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የእንኳን ደህና መጡ ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሺ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የሁለቱ ሀገራትን ስልታዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የሀገራቱን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር የሀገራቱን ሕዝቦች የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ፣ ለቀጣናውና ለዓለም ሰላም፣ ለልማት እና ብልጽግና አዎንታዊ አስተዋጽዖ ያደርጋል ብለዋል።

ሁለቱ ሀገራት የጋራ ፖለቲካዊ መተማመን መሰረትን ማጠናከር እና የተግባራዊ ትብብር ደረጃን ማሳደግ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ የሶሻሊስት ሀገራት መሆናቸውን ያስታወሱት ሺ ጂንፒንግ÷ በመካከላቸው ያለውን ወዳጅነት በጋራ አመለካከታቸው እና እምነታቸው እንዲሁም በጋራ ግባቸው ላይ የተመሰረተ እና በጥልቅ ታሪካዊ ትስስር የተደገፈ፤ ጠንካራ የፖለቲካ መሰረት ያለው መሆኑን አንስተዋል።

ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ወዳጅነት፣ የጋራ የወደፊት ዓላማ እና መደጋገፍ የሀገራቱ ግንኙነት መገለጫዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና እና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት ላይ አራት ሐሳቦችን አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በከፍተኛ ደረጃ ያሉ የመሪዎች ጉብኝት፣ ውይይት እና መሰል ልውውጦችን መቀጠል እንዲሁም የፖለቲካ መተማመኛ መሰረታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በቀዳሚነት አሳስበዋል።

በሁለተኛ ደረጃ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ተግባራዊ ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በቻይና እና ሰሜን ኮሪያ መካከል ያለውን ትብብር እንደ ጉልበት በመጠቀም በሕዝብ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር ሌላው የሀገራቱ የግንኙነት ማጠንጠኛ እንደሆነ አስረድተዋል።

በመጨረሻም ፍትሐዊነትን የሁለቱ ሀገራት የስትራቴጂካዊ ግንኙነት መርህ አድርጎ ማቆየት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በብርሃኑ አበራ

Photos from WMCC's post 08/06/2026

በኦሮሚያ ክልል 29 ሚሊየን ኩንታል ፍራፍሬ ምርት ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለፍራፍሬ ልማት ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በ2018 በጀት ዓመት 29 ሚሊየን ኩንታል የፍራፍሬ ምርት ተመርቷል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ።

በቢሮው የፍራፍሬ ልማት ዳይሬክተር ቻላቸው አዱኛ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷በክልሉ የፍራፍሬ ምርት ውጤታማነትን ለማጠናከር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

ክልሉ ለፍራፍሬ ልማት ምቹ የአየር ንብረት፣ በቂ የዝናብ መጠንና ተስማሚ የአፈር ዓይነት ያለው በመሆኑ ለዘርፉ ምርታማነት ከፍተኛ አቅም እንዳለው አውስተዋል፡፡

በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የምግብ ሥርዓትን ከማሻሻል ረገድ ሚናው የላቀ በመሆኑ በተከወኑ በርካታ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል፡፡

እንደ አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ አፕል እና ሎሚ ያሉ ዋና ዋና የፍራፍሬ ዓይነቶች የዞኖቹን መልክዓ ምድርና የአየር ንብረት መሰረት በማድረግ እየለሙ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የተሻሻሉ የፍራፍሬ ምርጥ ዘሮችን በመጠቀምና የማስፈጸም አቅምን በማሻሻል ልማቱ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።

በዚህም በ2013 ዓ.ም ከ90 ሺህ ሄክታር ያልበለጠውን የፍራፍሬ ልማት በአሁኑ ወቅት በ240 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ እየለማ መሆኑን ተናግረዋል።

ክልሉ ለፍራፍሬ ልማት ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በበጀት ዓመቱ 29 ሚሊየን ኩንታል ፍራፍሬ መመረቱን ጠቁመዋል።

ከዚህ ውስጥም ከ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሚሆነው የአቮካዶ ምርት መሆኑን ነው አቶ ቻላቸው የተናገሩት፡፡

ባለፈው ዓመት 2 ሺህ 400 ኩንታል የአቮካዶ ምርት ወደ ውጭ መላኩን አንስተው፥ ዘንድሮም በተሻለ ሁኔታ ለመላክ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

በአቤል ነዋይ

Photos from WMCC's post 08/06/2026

የኢኮኖሚ መነቃቃትንና የሀገር ውስጥ አቅምን እየገነባ የሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክቶች ከተማዋን ውብ እና ከብክለት ነፃ ከማድረግ ባለፈ ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎችን እያስገኙ ይገኛሉ፡፡

በከተማዋ ከእንጦጦ ተራራ ተነስቶ እስከ አቃቂ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ድረስ የሚዘልቅ የ56 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ግዙፍ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍሎ እየተተገበረ ነው፡፡

ለአብነትም ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ እንዲሁም ከእንጦጦ እስከ ቀበና ባለው መስመር የሚከናወነው መጠነ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን፤ ከወንዞቹ ዳርና ዳር እስከ 50 ሜትር እንደሚዘልቅ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ፕሮጀክቱ የአረንጓዴ ኮሪደሮችን፣ የሕዝብ መሰብሰቢያና የመዝናኛ ስፍራዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ እንዲሁም የንግድ እና የከተማ ግብርና ማዕከላትን አቀናጅቶ የያዘ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም መሰል ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች በዋናነት በውጭ ሀገር ባለሙያዎችና አማካሪዎች የሚሰሩ የነበሩ ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ የእነዚህ አዳዲስ ፕሮጀክቶች የንድፍ (ዲዛይን) እና የትግበራ ስራዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሀገር ውስጥ መሐንዲሶች የተቀረጹና የተተገበሩ በመሆናቸው፤ የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በከተማ ልማት ያላቸውን የመፈጸም አቅምና ብቃት በተግባር አሳይቷል፡፡

በኮንስትራክሽን፣ በኢንጂነሪንግ እና በአርክቴክቸር፣ በመልክዓ-ምድር ውበት ግንባታ፣ በሎጂስቲክስና ተያያዥ የሙያ መስኮች ለበርካታ ዜጎች አዲስ የስራ ዕድል በመፍጠር የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ዘርፍን በከፍተኛ ደረጃ ማነቃቃት ችሏል፡፡

ከአረንጓዴ ኮሪደሮችና ከመዝናኛ ስፍራዎች ጎን ለጎን የከተማ ግብርና እና የንግድ ቦታዎች ተቀናጅተው መገንባታቸው ለነዋሪዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እያስገኙ ነው፡፡

ቀደም ሲል በቆሻሻ መጣያነትና ለጎርፍ አደጋ ስጋት የነበሩት የወንዝ ዳርቻዎች አሁን ላይ ለሽርሽር ምቹ ፣ ለሸማቾችና ለነጋዴዎች በቀላሉ መገበያየት የሚያስችሉ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀና ማራኪ የገበያና የመዝናኛ ማዕከላት መሆናቸውንም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

08/06/2026

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች እነማን ናቸው?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገራችን ኢትዮጵያ ከሚገኙ እና በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የአጀንዳ ሃሳቦችን ማሰባሰቡ የሚታወቅ ነው፡፡

በዚህ የምክክር ሂደት በክልል/ ከተማ አስተዳደር ደረጃ፣ በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በዲያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ የተሰበሰቡ አጀንዳዎች በኮሚሽኑ ተደራጅተው ለመጨረሻው የአጀንዳ ቀረፃ እየተዘጋጁ ነው፡፡

👉ለመሆኑ በእነዚህ አጀንዳዎች ላይ የሚመካከረው ማን ነው?

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ ተሳትፎን የሚያደርጉ አካላት ኮሚሽኑ አጀንዳ ካሰባሰበባቸው ባለድርሻ አካላት የተመረጡ/ የተወከሉ ሲሆን ይህም በባለድርሻ አካላቱ እውቅና ሲከናወን ቆይቷል፡፡

በዚህ መሰረት በክልሎች/ ከተማ አስተዳደሮች፣ እና በዲያስፖራው ማህበረሰብ ዘንድ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ ወቅት በሀገራዊ ምክክር ጉባዔው ላይ እነሱን ወክለው የሚመካከሩ ወኪሎቻቸውን እንዲመርጡ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል በኩሚሽኑ አሰራር ስርዓት መሰረት በክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች እና በፌዴራል ተቋማት በሚገኙና ወኪሎቻቸውን በአጀንዳ ማሰባሰብ ወቅት እንዲመርጡ ያልተደረጉ ባለድርሻ አካላት ወኪሎቻቸውን በደብዳቤ ወክለው ለኮሚሽኑ እንዲያሳውቁ ኮሚሽኑ ለባለድርሻ አካላቱ ጥሪ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት በአጠቃላይ 4,000 የሚጠጉ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበት የሀገራዊ ምክክር ሂደት

👉የየወረዳው የሕብረተሰብ ክፍል ወኪሎችን

👉የክልል/ከተማ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ወኪሎችን

👉የፌዴራል ባለድርሻ አካላት ወኪሎችን እና

👉የዲያስፖራ ማህበረሰብ ወኪሎችን ያሳትፋል፡፡

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Addis Ababa