Addis MESOB - One Center Digital Government Service
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis MESOB - One Center Digital Government Service, Public & Government Service, Adwa Street, Arada SC, Addis Ababa.
Addis MESOB is a public office for one-stop service center designed to serve the residents of Addis Ababa with multiple public services under one roof making government services faster, more efficient, and citizen-focused.
06/08/2026
አዲስ መሶብ የአዲስ ከተማ ማዕከል ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡
Addis MESOB: ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም.
በአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት የአዲስ ከተማ ማዕከል አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በአንድ ጣራ ስር በማቅረብ ተገልጋዬችን ከአሰልቺ ቢሮክራሲና እንግልት ሙሉ ለሙሉ በማላቀቅ አገልግሎቶችን በቀላሉ እያገኙ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም በመመላለስ አላስፈላጊ እንግልት ይደርስባቸው የነበሩ ተገልጋዬች አዲስ መሶብ ወደ ተግባር ከገባ ጊዜ ጀምሮ ፈጣን አገልግሎት፣ የጊዜና የወጪ ቁጠባን፣ ተደራሽነት እንዲሁም የተገልጋይ እርካታን በማሳደግ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
ተገልጋዬችም የተቋሙን አመራሮች እና ሠራተኞች በማመስገን የአገልግሎት ጥራቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
Addis MESOB
The New Horizon of Service!
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!
Addis MESOB
The New Horizon of Service!
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!
05/08/2026
ከነገዋ ሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ሰልጥነው በአዲስ መሶብ ለተመደቡ ባለሙያዎች አቀባበል ተደረገ::
Addis MESOB: ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም.
ለከተማችን ቤተሰቦች አስተማማኝና ዘመናዊ የህጻናት እንክብካቤ አገልግሎትን ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት ፣ ከነገዋ ሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በሞግዚትነት ሙያ ሰልጥነው በአዲስ መሶብ ለተመደቡ 33 /ሠላሳ ሦስት/ ባለሙያዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል::
በአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ደሳለኝ ተረፈ በአቀባበሉ ወቅት እንዳሉት በአዲስ መሶብ ማዕከል የሚሰጡ የህጻናት እንክብካቤ አገልግሎቶች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና የደህንነት መስፈርቶችን ያሟሉ እንዲሆኑ የጀመርነው ዝግጅት አሁንም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በተጨማሪም ዛሬ አዲስ የተቀላቀላችሁ ሰራተኞች የማዕከሉን የአገልግሎት ጥራት መመሪያዎችን በመከተል እና የስራ አካባቢውን በንቃት በመጠበቅ ተቋማዊ ግባችንን እንደምታሳኩ ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል::
የተቋሙ የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ደመቁ ካሳሁን በበኩላቸው አዲስ መሶብ አገልግሎቶችን በዘመናዊ መንገድ በማቅረብ የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ ረገድ የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን የህጻናት ማቆያ (Day care) አገልግሎታችን ውጤታማ የሚሆነው በሙያዊ ዕውቀትና በስነ-ልቦና በተዘጋጁ ባለሙያዎች ነው፣ ከነገዋ ሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ያገኛችሁትን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ለህጻናቱ ተገቢውን እንክብካቤ በመስጠት ለአባቶችና እናቶች ሙሉ እፎይታ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባችሁ ተገንዝባችሁ በታማኝነትና በፍቅር እንድታገለግሉ በማለት የአደራ መልዕክት አስተላልፈዋል::
በመጨረሻም የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ መስከረም አበበ እንደገለፁት ተቋማችን ሰራተኞቹ በሙሉ አቋማቸው እና በሠላማዊ የአእምሮ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያከናውኑ የህጻናት ማቆያ አገልግሎት ወሳኝ በመሆኑ ከነገዋ ሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ያገኛችሁትን ዕውቀት ወደ ተግባር እንድትቀይሩ እንዲሁም ደግሞ በቀጣይ ለአዳዲስ ባለሙያዎች አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ ይደረጋል ብለዋል::
Addis MESOB
The New Horizon of Service !
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!
04/08/2026
በአዲስ መሶብ በደቂቃዎች የሚያገኙት የሥራ ፈላጊነት መታወቂያ (Labour id)
Addis MESOB: ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም.
ሀገራችን ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ወቅቱን የዋጀ የውጭ ሀገር እና ሀገር ውስጥ ሥራ ስምሪት አዋጅ አጽድቃ የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሥራት ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡
የሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች ዋነኛ እንደ መሆኑ በዘመነ አሠራር መምራት በማስፈለጉ የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (ELMIS) ስርዓትን በመዘርጋት የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ሥራ ፈላጊዎችን በመመዝገብና የሥራ ፈላጊ መታወቂያ (Labour id) በመስጠት እንዲሁም የተለያዩ ስምምነቶችን በመፈራረም ወደ ሥራ የማሰማራት ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የሥራ ፈላጊዎች ያለ ምንም መጉላላት የሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ሥራ ፈላጊነት ምዝገባን እንዲያከናውኑ በማድረግ ረገድ አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት በማዕከላቱ በላቀ መስተንግዶ ለተገልጋዮቹ ለመስጠት በሩን ከፍት አድርጎ እየጠበቀ ይገኛል፡፡
በአዲስ መሶብ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሥራ ፈላጊነት ለመመዝገብና የሥራ ፈላጊነት መታወቂያ (Labour id) ለማግኘት ሲመጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት መታወቂያ መያዝ ይኖርብዎታል፡፡
ከዚህ አገልግሎት በተጨማሪ የአዲስ አበባ ሥራ ክህሎት ቢሮ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች መረጃ ለማግኘት ሁል ጊዜም ባለሙያዎች ሊያገለግሉዎት ዝግጁ ሆነው ይጠብቁዎታል፡፡
Addis MESOB
The New Horizon of Service!
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!
04/08/2026
ውድ ተገልጋዮቻችን
የአዲስ መሶብ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት በከተማችን አዲስ አበባ ከመጪው ሰኞ ሐምሌ 20/2018ዓ.ም ጀምሮ በምስሉ በተዘረዘሩት ክፍለ ከተሞች አገልግሎት መስጠቱን ይቀጥላል።
ውድ ተገልጋዪቻችን በወጣው መርሀግብር መሰረት አገልግሎት በደጃፍዎ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን ስንገልፅልዎ በደስታ ነው።
የአገልግሎት አድራሻዎቻችንን ከምስሉ ላይ ይመልከቱ::
ለበለጠ መረጃ:
ይምጡና ይገልገሉ!
Addis MESOB
The New Horizon of Service!
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን
04/08/2026
03/08/2026
የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አመራሮችና ሰራተኞች በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ::
Addis MESOB: ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም.
"ተስፋን እንትከል" በሚል ታላቅ መሪ ቃል በተካሄደው ስምንተኛው ሀገራዊ "የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ" መርሃ-ግብር መሠረት የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አመራሮችና መላው ሰራተኞች በዛሬው ዕለት በየካ ክፍለ ከተማ በመገኘት የታሪካዊው ጥሪ ንቁ ተሳታፊ ሆነዋል::
በዚሁ ህዝባዊና ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ የተገኙት የማዕከሉ አመራርና ሰራተኞች የተለያዩ ጥቅም ያላቸውን በርካታ ችግኞች የተከሉ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ -ግብር የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባሻገር ለነገዋ ኢትዮጵያ ለምለምና ዘላቂ ተፈጥሮን የማስረከብ ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል::
አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ቀልጣፋና ዘመናዊ የህዝብ አገልግሎት ከማስረከብ ባልተናነሰ ማህበራዊና ሀገራዊ ጥሪዎችን በግንባር ቀደምትነት የመወጣት ባህሉን አጠናክሮ ይቀጥላል::
ዛሬ የተተከሉት ችግኞችን ተንከባክቦ የማጽደቅና ለፍሬ የማብቃት ስራ የማዕከሉ የሁልጊዜ ትኩረት እንደሚሆን ተመላክቷል::
የዕለቱ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተክሎ ከመሄድ ባለፈ የተተከሉት ችግኞች እንዲጸድቁ የችግኝ መሸፈኛ ላስቲኮችን በስነ-ስርዓት በማጽዳትና በማንሳት በስኬት ተጠናቋል::
Addis MESOB
The New Horizon of Service !
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!
01/08/2026
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የኩነት ምዝገባ ኦን ላይን መሆኑ አገልግሎት ለማግኘት የነበረውን እንግልት የቀነሰ መሆኑ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ገለጹ።
Addis MESOB: ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም.
በጉለሌ ክፍለ ከተማ በዲጂታል የሚሰጡ አገልግሎት ዙሪያ ግንዛቤ ሲያገኙ ካነጋገርናቸው የወረዳ 4 ነዋሪ መጋቢ ስርዓት ባየልኝ የማነ ቀደም ሲል ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ መስሪያ ቤቶች የመመላለስና ረጅም ጊዜ የመጠበቅ እንግልት ይደርስባቸው እንደነበር አስታውሰው አሁን ግን በተጀመረው በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምክንያት ጉዳያቸውን በአጭር ጊዜና ያለምንም እንግልት ማጠናቀቅ እንደሚችሉ ባገኙት ግንዛቤ ገልጸዋል።
የወረዳ 9 ነዋሪ ሀጂ መሐመድ አሚን የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የወሳኝ ኩነት ኦን ላይን ምዝገባ ስርዓት የገንዘብ ብክነት ከማስወገድ ባለፈ የወረቀት ምልልስ በማስቀረት የተቀላጠፈ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል በመሆኑ በአገልግሎቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ግርማቸው አብቴ በዛሬው በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በተፈጠረው ግንዛቤ አሰራሩ የህብረተሰቡን የጊዜና ወጪ ብክነት በማስቀረት ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለውና ከሙስና የጸዳ አሰራር መዘርጋት የሚያስችል ተቋም መሆኑንም አብራርተዋል።
ከዚህ ቀደም የተበታተኑ የመንግስት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕቀፍ እና በዲጂታል አማራጮች በማጣመር የተቋቋመ ተቋም መሆኑንም ለአገልግሎቱ ቀልጣፋ መሆኑን ተናግረዋል።
Addis MESOB
The New Horizon of Service !
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን
01/08/2026
በአዲስ መሶብ ንፋስልክ ማዕከል የሚሰጡ ፈጣንና ጥራት ያላቸው አገልግሎቶች ከተገልጋዮች አዎንታዊ ምላሽ እያገኙ ነው
Addis MESOB: ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም.
የአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል መንግሥት አገልግሎት ንፋስልክ ማዕከል ለኅብረተሰቡ የሚያቀርባቸው ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያላቸው አገልግሎቶች ከተገልጋዮች አዎንታዊ ምላሽ እያገኙ መሆናቸው ተገለጸ።
ማዕከሉ የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ስፍራ በማቅረብ ዜጎች ከተቋም ወደ ተቋም በመዘዋወር የሚያጠፉትን ጊዜና ወጪ በመቀነስ ተገልጋዮች አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ እያስቻለ ይገኛል። በዲጂታል ሥርዓት የተደገፈው አሠራርም የአገልግሎት ፍጥነትን፣ ግልጽነትን እና ተደራሽነትን በማሻሻል ለተገልጋዮች ምቹ የአገልግሎት ሁኔታ ፈጥሯል።
በማዕከሉ አገልግሎት የተጠቀሙ ተገልጋዮች በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም ለማግኘት ብዙ ጊዜ እና ጉልበት ይጠይቁ የነበሩ አገልግሎቶችን አሁን በአጭር ጊዜ እና በአንድ ማዕከል ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም በማዕከሉ የሚደረግላቸው አክብሮት የተሞላበት አስተናጋጅነት፣ ፈጣን ምላሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት እርካታቸውን እንዳሳደገ ጠቁመዋል።
የአዲስ መሶብ ንፋስ ስልክ ማዕከል ዜጎችን ያማከለ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የዲጂታል መንግሥት አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ እየሰራ ሲሆን፣ ወደፊትም የአገልግሎት ጥራትን እና ተደራሽነትን የበለጠ ለማጠናከር ጥረቱን እንደሚቀጥል ተገልጿል።
Addis MESOB
The New Horizon of Service !
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 21:00 |
| Tuesday | 08:00 - 21:00 |
| Wednesday | 08:00 - 21:00 |
| Thursday | 08:00 - 21:00 |
| Friday | 08:00 - 21:00 |
| Saturday | 08:00 - 21:00 |
| Sunday | 08:00 - 21:00 |