Awi Communication

Awi Communication

Share

Official

Photos from Awi Communication's post 02/09/2026

“ከድህነት የተላቀቀና በኢኮኖሚ የጠነከረ ማኅበረሰብ መፍጠር የግብርናው ዘርፍ ተቀዳሚ ተልዕኮ ነው” - አቶ ደረጀ ማንደፍሮ

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮና ተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 የምርት ዘመን ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጀ ማንደፍሮ እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት በግብርናው ዘርፍ በርካታ አበረታች ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት ነው ብለዋል።

የክልሉን የ25 ዓመት አሻጋሪ የዕድገትና ዘላቂ ልማት ፍኖተ ካርታ በግብርናው ዘርፍ የተቀመጡ ግቦች ለማሳካትም በተቀናጀ መልኩ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን እና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ከተመዘገበው 7.9 በመቶ ጠቅላላ የኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ የግብርናው ዘርፍ ከ5.5 በመቶ በላይ ድርሻ ማበርከቱን የገለፁት አቶ ደረጀ ይህም ውጤት ከክልል ጀምሮ እስከ ታችኛው የአፈጻጸም ደረጃ ድረስ ያለው የግብርና መዋቅር በተቀናጀ መልኩ ባደረገው ጥረት የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።

ከድህነት የተላቀቀና በኢኮኖሚ የጠነከረ ማኅበረሰብ መፍጠር የግብርናው ዘርፍ ተቀዳሚ ተልዕኮ ነው ነው ያሉት አቶ ደረጀ፣ የዘርፉ ተዋናዮች በቀጣይ ጊዜ የተሻለ ቅንጅትና ትጋት በማሳየት ተግባራቱን ከግብ ማድረስ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

በተለይም በአረንጓዴ አሻራ ልማት መርሃ ግብር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውንና የገበያ ተፈላጊነት ያላቸውን የፍራፍሬ ልማቶች በመስኖ ማስፋፋት፣ ሰፋፊ የቡና እና የፍራፍሬ ክላስተሮችን ማልማትና የግብርና መካናይዜሽንን ማስፋፋት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አቶ ደረጀ አክለውም ከሀገራዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራት አንዱ የሆነውን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የመሸጋገር ግብ እውን ለማድረግ ሁሉም የዘርፉ ተዋናዮች ተግባራቸውን በተቀናጀና በተጠያቂነት መንፈስ መፈጸም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በቀጣይ በጀት ዓመት ምርትና ምርታማነትን በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የኤክስቴንሽን አገልግሎትን ማጠናከር፣ የክላስተር አሰራርን ማስፋፋት፣ የግብርና ቴክኖሎጂ አቅርቦትና አጠቃቀም ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውንም ቢሮ ኃላፊው አስረድተዋል።

01/09/2026

21ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ በሚያጎላ መልኩ ይከበራል-አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦21ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የሕዝቦችን ትስስርና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ በሚያጎላ መልኩ እንደሚከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።

የ21ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ በበዓሉ መሪ ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ እያካሔደ ይገኛል።

https://www.ena.et/web/amh/w/amh_9482348

23/08/2026

የሕዝብ አደራ የሰነቀ አመራር በዘመቻም ሆነ በመከፋፈል ሴራ አይንበረከክም!
******
​ለአማራ ክልል ሕዝብ ሕልውና፣ ክብር እና የፍትህ ጥያቄዎች ጽኑ ምሽግ ሆኖ የቆመው አመራራችን፤ በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ውስጥ የሕዝባችንን ድምፅ ላለማስነጠቅ በሚያደርገው ርብርብ ላይ ዛሬም የተቀናጁ ዘመቻዎች እየተከፈቱበት ይገኛሉ። ይሁን እንጂ የሕዝብን ትክክለኛ የትግል አቅጣጫ ይዞ የሚጓዝ አመራር በየትኛውም ሴራ ሊመታ አይችልም።

​የአማራ ክልል አመራር ከሕዝቡ ተለይቶ የሚኖር ሳይሆን፣ የሕዝቡ ደም፣ ዕንባ እና የሰላም ጥያቄዎች አቆላምጦ ሳይሆን በግልጽ እና በድፍረት በማንጸባረቅ እውነተኛ የሕዝብ ወኪል መሆኑን በተግባር አሳይቷል። ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ ጫናዎችን እና የዘመቻ ውንጀላዎችን በመቋቋም የሕዝብን መብት ማስቀደም የጀግንነት እና የቁርጠኝነት ማሳያ ነው። በሀገራዊ መድረኮች የሕዝብን መብት የሚጻረሩ አሰራሮችን በመቃወም እና የተረጋገጠውን ሕጋዊ መዋቅራዊ ሂደት በመጠበቅ ረገድ የሕዝብን ጥቅም ያስቀደመ አቋም ይዟል።

​በተለይም አመራሩን ከሕዝቡ ለመነጠል፣ እርስ በእርሱ ለመከፋፈል የትግሉን አቅጣጫ ለማሳት የሚደረጉ ውንጀላዎች እና መረባረቦች ፍጹም ከንቱ ሙከራዎች ናቸው። አመራሩ በአንድነት የቆመው ለሕዝባዊ አደራ ብቻ ነውና

​ሕዝብን ይዞ መቆም ጽናትን ይጠይቃል፤ የአማራ ሕዝብም በታሪኩ አርዓያ የሆኑ ጀግኖችን እንዳፈራ ሁሉ፣ ዛሬም መብቱን የሚከለክለውንና ክፍፍልን የሚሰብከውን ሴራ የሚመክት ጽኑ አመራር አለው። የሚደረጉት ዘመቻዎችም ሆኑ የመከፋፈል ሙከራዎች የጊዜያዊ ጩኸት እንጂ የሕዝብን አንድነትና ድምፅ ሊያጠፉት ፈጽሞ አይችሉም!

Photos from Amhara Prosperity Party /APP/'s post 21/06/2026
Photos from Awi Communication's post 21/06/2026

የአጣዬ ከተማ የኮሪደር ስራ የእግረኛ መንገድ የቴራዞ ማንጠፍ ተጀመረ፤

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ ባለው የመጀመሪያ ዙር የኮሪደር ልማት ግንባታ ፕሮጀክት የእግረኛ መንገድ የቴራዞን ማንጠፍ ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

በቴራዞ ማንጠፍ ስራው ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ፣ የሰንበቴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኑረዲን አህመድ፣ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር እንድሪስ እንዲሁም ሌሎች የከተማው አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የአጣዬ ከተማ መሰረተ ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር አበቡ ማሞ እንደገለፁት፦ የከተማው ኮሪደር ልማት ግንባታ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ ሲሆን እና የቴራዞን ማንጠፍ ስራ መጀመሩ የፕሮጀክቱ አንዱ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የአጣዬ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጅነር እንድሪስ የሱፍ እንደተናገሩት፣ በመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ግንባታ አብዛኛው ስራ ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት የቴራዞ ማንጠፍ ስራ መጀመሩ የፕሮጀክቱን እድገት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም በቀጣይ የአረንጓዴ ቦታዎች ልማትና የፖል መብራት ተከላ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸው፣ ቀሪ ስራዎችም በቅርቡ ተጠናቀው ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ አስታውቀዋል።

በመጨረሻም የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ የከተማውን ውበት፣ የእግረኞች ምቹነት እና የትራፊክ ደህንነት በማሻሻል ለነዋሪዎች እና ለእንግዶች የተሻለ የከተማ አካባቢ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገልጿል።

Photos from Amhara Communications's post 21/06/2026
Photos from Awi Communication's post 11/05/2026

በደጀን ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በጠደን ቀበሌ የምረጫ ምዕልክት፣የምረጫ ማንፌስቶና የዕጩ ትውውቅ መድረክ ተካሄደ ።
‎
#​ምልክታችን _የስንዴ ነዶ ነው!
ሃገር!
!

08/05/2026

Telephone

Address

Spantov