EthioTimes
EthioTimes is a source of credible news and entertaining TV and radio productions.
09/27/2026
ትግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን ድል ቀንቷታል
‼️
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የሴቶች ውድድርን በ2 ሰዓት 11 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በማጠናቀቅ የውድድሩን ድል አስመዝግባለች።
አትሌቷ ውድድሩ ወደ መጨረሻው ሲቃረብ የጡንቻ ህመም ቢያጋጥማትም በጽናት በመቀጠል የድል መስመሩን ተሻግራለች።
በዚህም የግል ምርጥ ሰዓቷን ያሻሻለች ሲሆን፣ የበርሊን ማራቶን የውድድር ስፍራ ሪኮርድንም አሻሽላለች። የሰዓቷ ውጤትም በሴቶች ማራቶን ታሪክ ከተመዘገቡ ፈጣን ሰዓቶች መካከል ሆኗል።
ትግስት ከውድድሩ በኋላ በህክምና ድንኳን እርዳታ ያገኘች ሲሆን፣ በውድድሩ ያሳየችው ጽናት በርካታ የስፖርት አሰራጮችንና ተመልካቾችን አስደንቋል።
09/27/2026
የዕለቱ ምስል💚💛❤
👉 ታዳጊዋ ማዕዶት በዛሬው የመስቀል በዓል🙏
09/27/2026
ጠያቂ (አርቲስት መዉደድ ክብሩ)፦ እሺ ጃሉድ፣ ለአንድ ወር ስልጣን ቢሰጥህ ምን በመስራት ታሳልፈዋለህ❓
ጃሉድ፦ በዓለም ያለውን ሀብት ሰብስቤ ለአዲስ አበባ ሕዝብ አከፋፍለዋለሁ።
የተመረጠ አስተያየት፦ “የአዲስ አበባ ልጅ ብቻውን ስለማይበላ፣ ለሌሎች ወገኖቹም ያካፍላል።” ❤️
👉 አስተያየታችሁን በጨዋነት ያስቀምጡ፤ ለመዲናችንም ያላችሁን ፍቅር አሳዩ።
09/27/2026
የ14 ዓመታት የፍቅር ጉዞ‼️ ❤️🎶
ጋብቻ በፍቅር መጀመሩ ብቻ አይበቃም፤ ለዓመታት አብሮ ለመዝለቅ መተማመን፣ መቻቻልና እርስ በርስ መደጋገፍ ያስፈልጋል።
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና አምለሰት ሙጬ የ14 ዓመት የትዳር ጉዟቸውን አስቆጥረዋል። በዚህ ዓመታት የግል ሕይወታቸውን ከሥነ ጥበብ ሥራቸው ጋር በማጣጣም አብረው ቆይተዋል።
ቴዲ በሙዚቃው ለሚሊዮኖች መልዕክት ሲያደርስ፣ አምለሰት ከጎኑ በመቆም የሕይወት አጋሩ ሆናለች። ሁለቱም በየሙያቸው የሚታወቁ ቢሆኑም ፣ ከመድረክ ውጭ የሚጋሩት ቤተሰባዊ ሕይወት የግንኙነታቸው ሌላው ገጽታ ነው።
14 ዓመት ማለት ብዙ የሕይወት ደረጃዎችን በአንድነት ማለፍ ማለት ነው። ደስታንም ሆነ ፈተናን አብሮ መጋፈጥ፣ በእርስ በርስ መተማመንና ፍቅርን ማስቀጠል ነው።
ለቴዲ እና አምለሰት፤ እንኳን ለ14ኛ የጋብቻ ዓመታችሁ አደረሳችሁ! ❤️🎉
ፍቅራችሁ ይበልጥ ይፅና፣ ቤተሰባችሁም በሰላምና በደስታ ይቀጥል። 🙏❤️
— ከሚሊዮን ተኮላ (ቴዲ አፍሮ አድናቂ)
09/27/2026
ሞዴል ፣ አርቲስት እና የሚዲያ ባለሙያ ሉላ ገዙ💚💛❤
👉 መስቀል በጉራጌ
መልካም በዓል🙏
09/27/2026
በዛሬዉ የመስቀል በዓል የጉራጌ አባት የመረቁት ለየት ያለ ምርቃት 👉 "ከቤት ኪራይ ትረፉ‼️"
📷 Yoadan Ephrem
እናንተስ በበዓል ምን የሚል ምርቃት ተቸራችሁ❓
አስተያየታችሁን አስቀምጡ።
09/27/2026
የአቶ ጌታቸው ረዳ አባት አረፉ‼️
የቀድሞው የትግራይ ክልሰ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ምኒስትር የአቶ ጌታቸው ረዳ አባት አቶ ረዳ ካህሳይ ማረፋቸውን ዋሱ ሙሀመድ ዘግቧል።
ነፍስ ይማር🙏
09/27/2026
የመስቀል ደመራ በዓል በጎንደር💚💛❤
09/27/2026
የዕለቱ ምስል💚💛❤
የመስቀል ደመራ በዓል ድባብን በአነስተኛ ስልካቸዉ በፎቶ ለማስቀረት የሞከሩ እናት🙏
👉 ጎንደር 💚💛❤
09/27/2026
በመስቀል ቀን ለመስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን‼️
🚨 ታላቅ የበረከት ጥሪ‼️
በምስሉ የሚታየዉ ቤተክርስቲያን በሰሜን ጎንደር፣ ጃናሞራ ገጠር የሚገኝ ጥንታዊው የመስቀለ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ነዉ።
የቤተክርስቲያኑ ግንባታ ከተጀመረ 8 ዓመታት ቢያልፉም፣ በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ግንባታው ተቋርጦ ይገኛል።
🙏 በመሆኑም የቻልነውን ድጋፍ በማድረግ የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን።
💰 የቤተክርስቲያኑ አካውንት
ንግድ ባንክ – 1000091602311
📞 ለበለጠ መረጃ፦
0918055897 | 0957827972
🙏 ለብዙዎች እንዲደርስ እባክዎ ሼር ያድርጉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Opening Hours
| Monday | 9am - 5pm |
| Tuesday | 9am - 5pm |
| Wednesday | 9am - 5pm |
| Thursday | 9am - 5pm |
| Friday | 9am - 5pm |
| Saturday | 9am - 5pm |
| Sunday | 9am - 5pm |