PICE

PICE

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from PICE, Education & Learning, https://goo. gl/maps/pRCrxGcKvqhzPxVB 6, Addis Ababa.

01/10/2026

PICE & ROTECH

Photos from PICE's post 24/09/2026

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት የበጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅና የስልጠና መርሃ-ግብር አካሄደ

መስከረም 14/2019 ዓ.ም

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት የ2019 በጀት ዓመት የተቋማዊ ዕቅድ ትውውቅ እና «የጥቅም ግጭትን መከላከልና ማስተዳደር» በሚል ርዕስ ለማዕከሉ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ።

በመድረኩ ጅማሮ ላይ የማዕከሉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር ወ/ሮ እህትናት ደሳለው የ2019 በጀት ዓመት የስራ ክፍሉን አቅጣጫዎች፣ ዋና ዋና ግቦችንና የታቀዱ ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል።

ዳይሬክተሯ አክለውም በተቋሙ ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማጎልበት የሁሉም ሰራተኛ ንቁ ተሳትፎና የጋራ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመቀጠልም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስልጠና ባለሙያ አቶ ደረጀ በጥቅም ግጭት መከላከልና ማስተዳደር ዙሪያ አጠቃላይ ስልጠና ሰጥተዋል።

አቶ ደረጀ በስልጠናው ወቅት እንደተናገሩት፡
"የጥቅም ግጭት ማለት አንድ የመንግስት ወይም የተቋም ሰራተኛ የተጣለበትን ህዝባዊና ተቋማዊ ሀላፊነት በገለልተኝነትና በትክክል እንዳይወጣ የግል፣ የቤተሰብ ወይም የቅርብ ወዳጅ ጥቅም ተፅዕኖ ሲፈጥርበት የሚከሰት ሁኔታ ነው ያሉ ሲሆን የዚህ ችግር ዋና መንስኤዎች ደግሞ የግንዛቤ እጥረት፣ የግል ፍላጎትን ከተቋም ዓላማ ማስቀደም፣ እንዲሁም ግልጽ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችና ቁጥጥሮች መላላት ናቸው ብለዋሎ።

ጥቅምንና ሀላፊነትን ለይቶ ማወቅና የጥቅም ግጭትን አስቀድሞ መከላከል ለተቋማችን ህልውና ወሳኝ ነው ያሉት አሰልጣኙ የጥቅም ግጭትን በአግባቡ ማስተዳደር የተቋሙን ሀብት ከብክነት ከማዳኑ ባሻገር፣ በስራ አካባቢው ፍትሃዊ አሰራር እንዲሰፍን፣ የተቋሙ መልካም ስም እንዲጠበቅና በህዝብ ዘንድ ያለው አመኔታ ከፍ እንዲል ያደርጋል ብለዋል።

ስለዚህ እያንዳንዱ ሰራተኛ ሊከሰቱ የሚችሉ የጥቅም ግጭቶችን አስቀድሞ የማወቅ፣ የመጠቆምና በቅንነት የመመራት ሙያዊና ስነ-ምግባራዊ ግዴታ አለበት።

ይህ የስልጠናና የዕቅድ ትውውቅ መርሃ-ግብር በሰራተኞች ዘንድ የስነ-ምግባር ግንዛቤን በማሳደግ፣ ግልጽና ከሙስና የጸዳ አሰራር እንዲሰፍን በማድረግ በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

(https://t.me/pice1962)

(https://www.youtube.com/)

(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

(https://www.tiktok.com/)

Photos from FastMereja.com's post 22/09/2026
Photos from NBC Ethiopia's post 22/09/2026
Photos from PICE's post 22/09/2026

PICE እና Rotech Information Technology በቴክኖሎጂና ሙያ ስልጠና ዘርፍ የትብብር ስምምነት ጀመሩ

መስከረም 12/2019 ዓ.ም

ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል (PICE) ከ Rotech Information Technology ጋር በስምንት የቴክኖሎጂና ሙያ ስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ስምምነት በመፈራረም የመክፈቻ መርሐ ግብር አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የPICE አቅም ግንባታ ምክትል ዲን አቶ መክብብ አሰፋ የማዕከሉን ተልዕኮና አገልግሎቶች ለእንግዶች ያብራሩ ሲሆን፣ የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ትብብሩ የ2030 Digital Ethiopia ራዕይን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ መርሐ ግብሩን በይፋ አስጀምረው፣ አጋርነቱ በICT፣ Software/Hardware Development እና Electronics ጥገና ዘርፎች ብቁ አሰልጣኞችን በማፍራት የከተማዋን የSmart City ግንባታ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

በበኩላቸው የRotech Information Technology ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሮቤራ ተሾመ ስልጠናዎቹ በICT፣ Electronics ጥገና እና Digitalization ላይ እንደሚያተኩሩ ጠቅሰው፣ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን፣ የICT ባለሙያዎችን እና የተቋማት ሰራተኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደታቀደ አስረድተዋል።

በመጨረሻም ተሳታፊዎች የPICE የስልጠና ወርክሾፖችን፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እና የኢንኩቤሽን ሴንተሩን በመጎብኘት ፕሮግራሙን አጠናቀዋል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላትፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Website:
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/
Telegram Channel: PICE
https://t.me/pice1962
YouTube Channel: PICE1962
https://www.youtube.com/
Facebook Channel: PICE
https://m.facebook.com/edu.pice.et/
TikTok Chann
https://www.tiktok.com/

Photos from PICE's post 15/09/2026

የልህቀት ማዕከሉ ከሠራተኞቹ ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫና ውይይት አካሄደ

መስከረም 5/2019 ዓ.ም.

ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል (PICE) የመስቀል፣ የኢሬቻ እና ሌሎች የዘመን መለወጫ በዓላትን አስመልክቶ ከሠራተኞቹ ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫና ውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ኢትዮጵያ የበለፀገ ታሪክ፣ ባህል እና የመቻቻል እሴቶች ያሏት ሀገር መሆኗን በመግለጽ፣ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የሰላም፣ የምስጋና፣ የፍቅር እና የአንድነት እሴቶችን የሚያጎሉ ሀገራዊ ቅርሶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በተካሄደው ውይይት ተሳታፊዎች የሕዝቦች አንድነት፣ የጋራ እሴቶችን ማክበር እና አብሮነትን ማጠናከር ለሀገራዊ አንድነትና ልማት ያለውን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በዓላቱ በሰላምና በደማቅ ሁኔታ እንዲከበሩ እንዲሁም ለኢኮኖሚና ለቱሪዝም ዕድገት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በአንድነት እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Websit .... https://pice.sims.aatvetb.edu.et/
Telegram Channel …….PICE https://t.me/pice1962
YOUTUBE Channel ……. PICE1962 https://www.youtube.com/
Facebook Channel ………….PICE https://m.facebook.com/edu.pice.et/
TikTok Channel ………Pice_1962 https://www.tiktok.com/

Photos from PICE's post 14/09/2026

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የ2019 አዲስ ዓመትን በ«ወርቃማው የአብሮነት መድረክ» አበሰረ

አዲስ አበባ (መስከረም 4/2019 ዓ.ም)

የምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል «Small Action, Big Impact - ትንሽ ተግባር፣ ትልቅ ተፅዕኖ» በሚል ርዕስ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያውን «ወርቃማ ሰኞ መድረክ» አካሄደ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ለአመራሩና ለሰራተኞች የአዲሱን ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዋና ዲኑ በመልዕክታቸው «አዲሱን ዓመት በዕውቀት፣ በፈጠራ፣ በትብብርና በምርት ማዕከላችንን ወደ ላቀ የልህቀት ደረጃ ለማሸጋገር ሁላችንም በተሰማራንበት የሥራ ዘርፍ በቁርጠኝነትና በጠንካራ አሰራር ልንረባረብ ይገባል» ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የእለቱ የወርቃማ ሰኞ ዝግጅት ዋና አቅራቢ የነበሩት የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ ክፍል ተጠሪው አቶ አያና ቡልቻ «Small Action, Big Impact - ትንሽ ተግባር፣ ትልቅ ተፅዕኖ» በሚለው ርዕስ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አቶ አያና ርዕሱን ከማዕከሉ ግቦች ጋር በማያያዝ ባስተላለፉት መልዕክት፡-
በየቀኑ የምንፈጽማቸው ጥቃቅን የሚመስሉ በጎ አሰራሮች፣ የሥራ ዲሲፕሊኖችና የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች የቡድን ስራዎች ተደምረው በማዕከላችን አጠቃላይ ምርታማነት ላይ ትልቅና አዎንታዊ ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም አላቸው። ሲሉ አስገንዝበዋል::

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/)

10/09/2026

2019 ዓ.ም

Photos from PICE's post 10/09/2026

በቴክኖሎጂ የበለጸገች የነገዋ ኢትዮጵያ፡ ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል እና የ5 Million Ethiopian Coders ጥረት

የዘመናዊነት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ባለቤት የሆነው ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል፣ ከተመሠረተ ከ56 ዓመታት በላይ የተሻገረ ባለጸጋ ታሪኩን መሠረት በማድረግ በአሁኑ ወቅት በርካታ የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ሥራዎችን በማምረትና ወደ ኢንዱስትሪው በማሸጋገር ላይ ይገኛል።

ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን "የነገ ቀን" በሚል በሚከበረው አገራዊ ቀን፣ ማዕከሉ በዲጂታል ዘመን ኢትዮጵያን ወደተሻለ የዕድገት ማማ ለማሸጋገር የሚደረጉ ጥረቶችን ከኢትዮ ኮደርስ (5 Million Ethiopian Coders) ሰልጣኞች ስኬት ጋር በማቀናጀት የነገዋን አገር ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጧል።

የማዕከሉ አሰልጣኞች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የተለያየ ይዘት ያላቸውን ተግባራዊ ቴክኖሎጂዎች በመንደፍና በማምረት ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።

Virtual Reality (VR) Technology (ቨርቹዋል ሪአሊቲ ቴክኖሎጂ)፦ በዲጂታል ምናባዊ (3D) በወርክ ሾፕ አካባቢ ላይ የተመሠረተና ለላቀ ስልጠና፣ ለትምህርት እንዲሁም ለልምምድ ተግባራት የሚያገለግል የዘመኑ ቴክኖሎጂ።

እነዚህ በማዕከሉ የተሰሩ ቁሳዊና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች፣ በኢትዮ ኮደርስ መርሃ-ግብር ከሚሰለጥኑት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች የኮዲንግ እና የሶፍትዌር ክህሎት ጋር ሲቀናጁ ለሀገራችን የነገ ተስፋ ትልቅ መሠረት ይጥላሉ።

በዛሬው "የነገ ቀን" የምስራች፣ ምርታማነት ማሻሻያ የልህቀት ማዕከል የነበሩትን ተሞክሮዎች ከዘመኑ ዲጂታል ዕውቀት ጋር በማጣመር የነገዋን የበለጸገችና በቴክኖሎጂ የበቃች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ በግንባር ቀደምትነት መምራቱን ይቀጥላል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/)

Address


Https://goo. Gl/maps/pRCrxGcKvqhzPxVB 6
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:00 - 17:00
Tuesday 02:00 - 17:00
Wednesday 02:00 - 17:00
Thursday 02:00 - 17:00
Friday 02:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when PICE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.