Thomando

Thomando

Share

Striving To Build Positivity All Over The World!

17/08/2026

ዘዳግም 8:17-18
17 ምናልባትም፣ “ይህን ሀብት ያፈራሁት በጕልበቴና በእጄ ብርታት ነው” ብለህ በልብህ ታስብ ይሆናል።
18 ነገር ግን ሀብት እንድታፈራ ችሎታ የሰጠህ፣ ለአባቶችህም በመሐላ የገባውን ኪዳን ያጸናልህ እርሱ ስለሆነ፣ አምላክህን እግዚአብሔርን ዐስበው።

09/08/2026

Value those who add value to your life.

12/04/2026

-አመክንዮ (Logic & Mindset)
👉በቀን ስንት ሰዓት ስልካችን ላይ መረጃዎችን በማንበብ እናሳልፋለን? ለጤና፣ ለገንዘብ አያያዝ፣ ለቴክኖሎጂና ለስኬት የሚረዱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጽሁፎችን እናነባለን።
ግን ጥያቄው እዚህ ጋር ነው፤ ባነበብነው ልክ ህይወታችን ላይ ለምን ለውጥ አይታይም?"
👉ምናልባት
#የመረጃ መጥለቅለቅ (Information Overload)፦ አእምሯችን መረጃን ከማከማቸት ባለፈ የማውጠንጠኛና የመተግበሪያ ጊዜ እያጣ ይሆን?
#የማወቅ ስሜት እንጂ #ዕውቀት አለመኖሩ፦ አንድን ነገር ስላነበብነው ብቻ ያወቅነው ይመስለናል፤ እውነተኛ ዕውቀት ግን ከተግባር ነው የሚመነጨው።
#የማሳወቂያዎች (Notifications) ረብሻ፦ አንዱን ጠቃሚ ነገር አንብበን ሳንጨርስ ሌላ መረጃ ይደርሰናል፤ ይህም ትኩረታችን እንዲበታተን ያደርጋል።
#ከጥልቅ ንባብ ወደ አጉራሽ ንባብ፦ መጽሐፍትን በጥልቀት ከማንበብ ይልቅ አጫጭር ጽሁፎችንና ቪዲዮዎችን ብቻ መመልከት ጥልቀት የሌለው ትውልድ እየፈጠረ ይሆን?

14/01/2026

👉​በአንድ ወቅት፣ ሁለት እንቁራሪቶች ምግብ ፍለጋ ሲዘሉ ሳያውቁት በአንድ ግዙፍ የወተት ገንዳ ውስጥ ዘለው ገቡ። ገንዳው ጥልቅ፣ ግድግዳው ደግሞ በጣም የሚያንሸራትት ነበር።
​ሁለቱም እንቁራሪቶች ለመውጣት ደጋግመው ዘለሉ፤ ነገር ግን ግድግዳው ስለሚያንሸራትት ተመልሰው ወተቱ ውስጥ ይወድቃሉ። ለሰዓታት ሲታገሉ ቆዩ።
👉​የመጀመሪያው እንቁራሪት በጣም ደከመው። በአሉታዊ አመለካከት ተሞልቶ እንዲህ አለ፦ "ይህ ከንቱ ድካም ነው። መውጫ የለም፣ ግድግዳው ይንሸራትታል፣ ማንም ሊረዳን አይመጣም። ደክሞ መሞት ምን ያደርጋል?" አለና መዋኘቱን አቆመ። ወዲያውም በወተቱ ውስጥ ሰጥሞ ቀረ።
👉​ሁለተኛው እንቁራሪት ግን አመለካከቱ የተለየ ነበር። "አሁን ባላውቀውም አንድ መውጫ መንገድ መኖሩ አይቀርም፤ እስከ መጨረሻው እስትንፋሴ ድረስ ግን እግሮቼን አላቆምም" በማለት በሙሉ ኃይሉ መዋኘቱንና መታገሉን ቀጠለ።
👉​ለብዙ ሰዓታት እግሮቹን ሲያወዛውዝና ሲመታ ቆየ። በሚገርም ሁኔታ፣ የእንቁራሪቱ እግሮች ወተቱን ደጋግመው ሲመቱት፣ ወተቱ ተመታና ወደ "ቅቤነት" ተለወጠ። ወተቱ ወፍሮ ቅቤ ሲሆን፣ እንቁራሪቱ በቅቤው ላይ ተረግጦ መቆም ቻለ። ከዚያም በቅቤው ላይ ቆሞ በመዝለል ከገንዳው ወጥቶ ሕይወቱን አተረፈ።
​"ድካምህ ቅቤ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፤ ብቻ መዋኘቱን አታቁም!"

13/01/2026

Listen to the inner light; It will guide you.
Listen to the inner Peace; It will feed you.
Listen to the inner Love;It will transform you.

02/01/2026

#ድንቅ ልማድ

አንድ ልማድ ስትጀምረው እንደማይታይ ክር ነው፤ ያ ክር እርስበርሱ ሲደጋገም ሲጠላለፍ ትንሽ ቆይቶ በቀላሉ የማይበጠስ ሀያል ገመድ ይሆናል።

አየህ አሪፍ ልማድን ስትጀምረው እንደ ክሩ ስስ ነው፤ ለመበጠስ ቅርብ ነው፤ ስትደጋግመው ግን አንተ ውስጥ ጠንካራ ማንነት ይፈጥራል።

ሌላ ምሳሌ የትኛውም ሱስ ከትንሹ ነው የሚጀምረው ለምሳሌ የሲጋራ ሱስ ያለባቸው ሰዎች አይተህ ከሆነ ማጨስ ሲጀምሩ 1 ወይም 2 ፓኮ በማጨስ አይደለም የጀመሩት ከባኮ ውስጥ አንዷን በማውጣት ዛሬ አንዷን ነገም ይደግማል እያለ የሆነ ጊዜ ላይ በአነዴ ፓኮ ሲጨርስ ታገኘዋለህ።

ግድ የለህም ወዳጄ በጠዋት መነሳቱን፣ ማንበቡን፣ ስፖርት መስራቱን፣ ቋንቋ መለማመዱን በቃ የጀመርከውን አሪፍ ልማድ ሳትሰለች ትንሽ ደጋግመው፤ ከዛ ምን አይነት ሰው እንሚያደርግህ ታየዋለህ!

የተባረከ ቀን ተመኘን🙏

31/12/2025

"Before you judge someone about their anger. Ask them about their pain".

27/12/2025

👇
☞ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ስትሆን ኩራት (PRIDE) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ኩራት አንተ የደረስክበት የስኬት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ሰዎችን በንቀት እንድትመለከት ያደርግሃል፡፡

☞ ታችኛው ክፍል ላይ ስትሆን ፣ ምሬት (BITTERNESS) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ምሬት ቅናት እንዲሰማህ እና አንተ ያልተሳካልህ በሌሎች ሰዎች ምክንያት እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል፡፡

☞ ወደ ላይኛው መንገድ ስትጓዝ ስግብግብነት (GREED) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ስግብግብነት ትዕግሥት ያሳጣሃል እናም እንድትሰርቅ ወይም አቋራጮችን እንድትፈልግ ያደርግሃል።

☞ ወደ ታች በምትወርድበት ጊዜ ፣ ተስፋ መቁረጥ (DESPAIR) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ፣ ሁሉም ነገር ተጠናቋል ብለህ እንድታስብ ሊያደርግህ ይችላል።
❤መልካም ቀን❤

26/12/2025

!

🚶‍♀️ስትራመድ— ደስ ይበልህ!

☀️ጸሐዩአን ስታይ— ደስ ይበልህ!

🎧መዝሙር ስትሰማ— ደስ ይበልህ!

🤸‍♀️ስትንጠራራ— ደስ ይበልህ!

🙊ከሚወዱህ ጋር ስታወራ— ደስ ይበልህ!

🧎ስትጸልይ— ደስ ይበልህ!

ይህን ማድረግ ያልቻሉ ብዙ አሉና። ተመስገን በል!

Category

Website

Address


Addis Ababa