Ethio Computer Store
ምን አይነት ላፕቶፕ ለመግዛት አስበዋል?ለትምህርት, ለቪዲዮ ኤዲቲንግ, ለኦንላይን ስራ, ለሪሰርች መስሪያ, ለቢሮ ስራ, ጌሚንግ - እኛን ሳያማክሩ አይወስኑ
ይደውሉልን 0973424250 Office Number: M05, DH Geda Tower
20/09/2026
ፊልም ወዳጅ ነኝ። ረጃጅምና ብዙ ክፍል ያላቸው ለማየት ትዕግሥቱ ስለሌለኝ አላይም። ቢበዛ በ2:30 ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ አለበት። በተለይ በቂ ትምህርት ሰጥቶ የሚያልፈው ለረዥም ጊዜ አልረሳውም። ምሥሉ ላይ የሚታየው እውነተኛ ታሪክን መሠረት አድርጎ የተሠራው ''Coach Carter'' አንዱ ነው።
ሚ/ር ካርተር የራሱ መካከለኛ ቢዝነስ ያለው እንዲሁም የቅርጫት ኳስ አሰልጣኝ ነው። ማሸነፍ እንጂ ሌላ የማያውቅ የ highschool ቅርጫት ኳስ ቡድኑን እንዳይጫወት በማገድ የልምምድ ሜዳውን (basketball court)ም በመዝጋቱ በጣም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ይህን ያደረገው ደግሞ ተጫዋቾቹ ሙሉ ትኩረታቸውን ቅርጫት ኳስ ላይ አድርገው በትምህርታቸው ዝቅተኛ ውጤት በማስመዝገባቸው ተበሳጭቶ ነው።
ሚ/ር ካርተር አሁንም በሕይወት ያለ እውነተኛ 'ሰው' መሆኑ ልብ ይባል። ልበ-ወለድ ካራክተር አይደለም።
ምን ዓይነት ኃላፊነት የሚሰማው ሰው ነው!? ተጫዋቾቹ ትምህርታቸው ላይ ካልበረቱ በቅርጫት ኳስ ብቻ የትም እንደማይደርሱ ያውቃል። በቁጥር በጣም ጥቂት የሆኑት እንዳጋጣሚ ሊሳካላቸው ይችላል። የስኬት በርን ሰፋ ለማድረግ ደግሞ አማራጮችን ማስፋት ምርጫ የሌለው ነው።
ኋላ ላይ ተጫዋቾቹ ተስማምተው ሰዓታቸውን አከፋፍለው ትምህርታቸው ላይ በረቱ፤ ቅርጫት ኳሳቸውም ላይ እይበገሬነታቸውን አሳዩ። ከሌሎች ትምህርት ቤቶች በተለየ አብዛኞቹ ተጫዋቾች በትምህርታቸው በጣም ጥሩ ውጤት በማምጣታቸው እንዲሁም በቅርጫት ኳስ ተጫዋችነታቸው ስኮላርሺፖችን አሸንፈው ኮሌጅ/ዩኒቨርሲቲ ገቡ። ለየት ባለ ዲሲፕሊን በመያዛቸው ስኬትን ተጎናጸፉ።
ትምህርት ባሕሪው ይቀያየር እንጂ ድሮም አሁንም ወደፊትም የዕድገት መሠረት ነው። የስልጣኔ መሠረት ነው። የሕልውና መሠረት ነው። ከትምህርት በመፆም በአቋራጭ የሚገኘው ቁልቁለት ገደል ነው።
ስለ ትምህርት ሳነሳ በዲግሪ ስለመመረቅ የማወራ የሚመስለው ብዙ የዋህ አለ። እንደዚያ አይደለም። የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ (ኢኮኖሚ፣ ባሕል፣ ተፈጥሮ፣ አኗኗር፣ ፖለቲካል ሲስተም ወዘተ.) ባገናዘበ መልኩ የትምህርት ስርዓታችን ቢቃኝ እወዳለሁ። እንደ ወረደ የምዕራባውያንን ካሪኩለም መውሰዳችን ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም። ለአገራችን እድገት እና ሥልጣኔ የሚመጥን እንዲሁም በአጭርም በረዥምም ጊዜ ውጤት የምናይበት ሥርዓተ-ትምህርት ቢኖረን ብዬ እመኛለሁ።
ከዚያ ውጪ የትምህርትን አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ በማስገባት ''ሳይማሩ የተሳካላቸው''ን ምናልባት የዓለምን ሕዝብ ከ0.5% በታች ቁጥር የማይዙ ባለሃብቶችን እየጠቀሱ ቁጭ ብሎ በመማለልና ''ድንቁርና''ን በማስፋፋት የሚመጣ አንዳች ጠብብ የሚል ነገር የለም።
-Hawlet
20/09/2026
ትልቁ ውድቀት የሚጀምረው ጠላትን አሳንሶ ከማየት ነው፤over confidant ነበርክ ካንተ የማይጠበቅ ስህተት ሰራህ ተሸነፍክ።
እንደምትችል ግን አምነናል።
🚀Free AddisCoder 2027 Coding Program for Ethiopian High School Students🚀
✨Are you an Ethiopian high school student in Grades 9–11 who loves mathematics and wants to explore programming, algorithms, and advanced problem-solving? AddisCoder 2027 offers a free summer learning experience for talented students from across Ethiopia.
What You’ll Gain:
🔹Learn programming and algorithmic problem-solving
🔹Develop advanced computational and mathematical skills
🔹Work on challenging problems and learn with other talented students
🔹Experience an intensive academic learning environment
🔹Free dormitory accommodation and meals
Who Can Apply?
🔸Ethiopian high school students currently in Grades 9–11
🔸Students with strong academic performance, especially in mathematics and related subjects
Students from anywhere in Ethiopia
🔸No previous programming experience required
📍Location: Addis Ababa, Ethiopia
📆Exact dates: To be announced
⏳Duration: 4 weeks
💰Fee: Free
🔗Apply: https://addiscoder.com/
📝Deadline: December 31, 2026
"If this isn't for you, please share it with others who might be interested."🙏
19/09/2026
🚨 ከቁጥጥር ውጪ የሆነው AI ፡ ጉግል ጀሚኒ 3 ኩባንያዎችን ጠለፈ!
በአንድ የደህንነት ሙከራ ስህተት ምክንያት የጉግል Gemini AI ሦስት እውነተኛ ኩባንያዎችን ራሱ ሰብሮ መግባቱ (Hack ማድረጉ) ተረጋገጠ!
🔥 እንዴት እና ምን ተፈጠረ?
🤖 በራሱ ፈቃድ፡ በሙከራው ወቅት ኢንተርኔት በስህተት ክፍት ሆኖ በማግኘቱ ራሱ ፈልጎ ተቋማቱን አጠቃ።
🔑 ፓስዎርድ ገመተ፡ የይለፍ ቃላትን (Passwords) በራሱ ጥረት በመገመት ነው ወደ ሲስተማቸው ሾልኮ የገባው።
🛑 በራሱ ቆመ፡ ድርጅቶቹ የሙከራ ሳይሆኑ እውነተኛ መሆናቸውን ሲገነዘብ ወዲያውኑ ጥቃቱን አቋርጦ ወጣ (ምንም ጉዳት አላደረሰም)።
⚠️ የተጠለፉት ኩባንያዎች ስም ሚስጥር ቢሆንም፣ ይህ ክስተት "የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ከቁጥጥር ውጭ ቢሆን ምን ሊፈጠር ይችላል?" ለሚለው ትልቅ ማሳያ ሆኗል!
Ethio Computer Store
0973424250
16/09/2026
🤖 AI እና የ"17" ቁጥር ፍቅር! 😂
AIን (ChatGPT, Claude ወይም Gemini)
"ከ 1 እስከ 25 random ቁጥር ምረጥ" ብትሉት…
አብዛኛውን ጊዜ መልሱ ያው 17 ነው!😳
ከ 1 እስከ 100 ሲሆን ደግሞ ወይ 37 አሊያም 42 ላይ ይጣበቃል! 😂
እስኪ አሁኑኑ ጠይቃችሁት የመጣላችሁን ቁጥር ኮመንት ላይ አሳውቁን ! 👇 ይመቻችሁ 💪
ግን ለምን? 🙅🤔
Ethio Computer Store
15/09/2026
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስጋት፦
እውነት ነው ወይስ የንግድ ማስታወቂያ?
🤖💡በቴክኖሎጂው ዓለም፣ የትልልቅ ኩባንያ መሪዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ እርስ በርስ መወጋገዝ ጀምረዋል፦
😈 የችግር ፈጣሪዎቹ ሴራ?
የዓለማችን ግዙፉ የቺፕ አምራች (Nvidia) አለቃ እንዳሉት፣ "AI አደገኛ ነው፣ ዓለምን ሊያጠፋ ይችላል" የሚለው ጩኸት ኩባንያዎች የራሳቸውን የመከላከያ ሶፍትዌር ለመሸጥ የፈጠሩት የገበያ ማስታወቂያ (Marketing) ሊሆን ይችላል። "ፍላጎት ለመፍጠር ችግር ከመፍጠር የተሻለ ምን መንገድ አለ?" ሲሉም አሽሟጠዋል።
😨 የሌሎች ፍርሃት
በተቃራኒው እንደ OpenAI እና ኢሎን መስክ ያሉ የዘርፉ መሪዎች "ቴክኖሎጂው ከቁጥጥር ውጪ እንዳይወጣ ፍጥነቱ ይገደብ፤ በገለልተኛ አካልም ይመረመር" በማለት አስጠንቅቀዋል።
📉 የአክሲዮን ገበያው መደናገጥ
ይህን ውዝግብ ተከትሎ የቺፕ ፍላጎት ይቀንሳል በሚል ስጋት የኩባንያዎች አክሲዮን ወድቋል፦ Nvidia ከ3% በላይ፣ AMD በ4.6%፣ እንዲሁም Intel ወደ 5% የሚጠጋ የዋጋ ቅናሽ አሳይተዋል።
🇪🇹 ለኢትዮጵያስ ምን ትርጉም አለው?
የሀገራችን ባንኮች፣ ቴሌኮም እና የመንግሥት አገልግሎቶች በከፍተኛ ፍጥነት ዲጂታላይዝ እየሆኑ ባሉበት ወቅት፣ የሚወሩት የ AI ጥቃት ስጋቶችም ሆኑ ውድ መፍትሔዎቻቸው እውነተኛ ናቸው ወይስ ሌላ የገበያ ሸቀጥ? የሚለው ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው።
እርስዎ ምን ይመስልዎታል?
በ Reaction ያሳዉቁን ፦
❤️ — እውነት ነው! AI ከቁጥጥር ውጪ እንዳይወጣ ፍጥነቱ መገታት አለበት።
🔥 — ኧረ ተውት! አዲስ ነገር ለመሸጥ የተፈጠረ የቢዝነስ ማስታወቂያ ነው።
👉 የእርስዎስ እይታ ምንድን ነው? አስተያየትዎን ኮመንት (Comment) ላይ ያጋሩን! 👇
Ethio Computer Store
09/09/2026
⚡ አዲስ ዘመን በአፕል፡ አይፎን 18 ፕሮ እና 18 ፕሮ ማክስ ይፋ ሆኑ!
የአፕል አዲሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ (CEO) ጆን ተርነስ ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ በመውጣት እጅግ ዘመናዊ የሆኑትን iPhone 18 Pro እና 18 Pro Max ስልኮችን በይፋ አስተዋውቀዋል።
🔹 የዓመቱ ምርጥ ከለር: በርገንዲ (Burgundy/ጥቁር ቀይ) የዘንድሮው ልዩ እና ተመራጭ ከለር ሆኗል፤ ከዚህም በተጨማሪ በጥቁር፣ ሲልቨር እና ቀላል ሰማያዊ (Light Blue) አማራጮች ቀርቧል።
🔹 ጉልበቱ: ስልኩን የሚመራው እጅግ ፈጣኑ A20 Pro ቺፕ ሲሆን፣ ውስብስብ የሆኑ የ-AI ሞዴሎችን (LLMs) እና ከፍተኛ ግራፊክስን በስልኩ ላይ ብቻ ያለምንም መቆራረጥ የማስኬድ ሙሉ አቅም አለው።
አፕል በዚህኛው ዝግጅቱ ሙሉ ትኩረቱን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በከፍተኛ ፍጥነት ላይ አድርጓል።
💬 ከቀለሞቹ የትኛው ይበልጥ ማረካችሁ—አዲሱ በርገንዲ ወይስ ክላሲኩ ጥቁር? አስተያየታችሁን ኮመንት ላይ አጋሩን! 👇
07/09/2026
ቪዲዮ እያያችሁ ማስታወሻ መጻፍ ሰልችቷችኋል? ይሄን ድካም የሚያስቀር አዲስ ሚስጥር ልንገራችሁ! 🤯
ዩቲዩብ ላይ tutorial ስትከታተሉ ረጅም code ወይም ኖት በእጅ እየጻፋችሁ ጊዜያችሁን አታባክኑ። ይህ ትንሽ extension በሰከንድ ውስጥ ከየትኛውም ቪዲዮ ላይ ጽሁፍ ኮፒ (copy) ያደርግላችኋል!
Selectext ምን ያደርግላችኋል?
* Coding Tutorials ላይ የሚታዩ ረዣዥም ኮዶችን በሰከንድ ውስጥ ኮፒ ያደርጋል
* Online Lectures ስትማሩ ማስታወሻዎችን ያለድካም ይገለብጣል
* Slide Presentations ላይ ያሉ ጽሁፎችን በቀጥታ ይወስዳል
* በ YouTube ብቻ ሳይሆን በማንኛውም የብራውዘር ቪዲዮ ላይ ይሰራል!
እንዴት ይሰራል?
* ቪዲዮውን Pause አድርጉ
* የ Extension-ኑን icon ክሊክ አድርጉ
* የፈለጋችሁትን ጽሁፍ Highlight አድርጋችሁ Copy ማድረግ ብቻ!
አሁኑኑ ሞክሩት፣ ጊዜያችሁን ቆጥቡ 👇
🔗 https://chromewebstore.google.com/detail/selectext-copy-text-from/gkkdmjjodidppndkbkhhknakbeflbomf
ይህ መረጃ ለጓደኛችሁ ይጠቅማል? Share ማድረግ እንዳትረሱ! 💡
ተጨማሪ የቴክኖሎጂ ሚስጥሮችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ
03/09/2026
🎙️ Jabra Speak2 75 — Professional meetings, anywhere.
Experience clearer calls with 360° voice pickup, AI noise cancellation, Bluetooth & USB-C connectivity, and up to 32 hours of battery life.
🔥 BEST PRICE — Contact us today!
📞 +251-973-424-250
📍 Friendship Super Market Building, Bole, Addis Ababa
29/08/2026
የኮምፒውተርዎ ሙሉ መረጃ (Specifications) ማወቅ ይፈልጋሉ?
ምንም መገመት አያስፈልግም! እነዚህን 3 ነፃ ሶፍትዌሮች ይጠቀሙ፡-
🖐1. HWiNFO (ለሙሉ እና ዝርዝር መረጃ)
* ጥቅሙ፡ የኮምፒውተርዎን አጠቃላይ ክፍሎች ዝርዝር መረጃ ለማወቅ።
* ምን ይመረምራል፡ የሙቀት መጠን (Temperature)፣ የፋን ፍጥነት፣ የቮልቴጅ መጠን እና የቺፕ ዝርዝሮችን በቅጽበት ያሳያል።
* ዋጋ፡ 100% ነፃ።
🖐2. Speccy (ለቀላል እይታ)
* ጥቅሙ፡ ለማንበብ በጣም ቀላል የሆነ ዳሽቦርድ አለው።
* ምን ይመረምራል፡ የRAM፣ CPU፣ GPU፣ Storage እና የሙቀት መጠን መረጃዎችን በአንድ ቦታ ያሳያል።
* ዋጋ፡ ነፃው ስሪት ሙሉ መረጃ ይሰጣል።
🖐3. CPU-Z / GPU-Z (ለፈጣን ቴክኒካል መረጃ)
* ጥቅሙ፡ ስለ ፕሮሰሰር (CPU) ወይም ግራፊክስ ካርድ (GPU) ፈጣን መረጃ ለማግኘት።
* ምን ይመረምራል፡ የክሎክ ስፒድ፣ የRAM ታይሚንግ እና የቪዲዮ ሜሞሪ (VRAM) ዝርዝር።
* ዋጋ፡ 100% ነፃ።
🫡(የMac ተጠቃሚዎች፡ Option key ⌥ ተጭነው የApple ምልክቱን በመንካት 'System የሚለውን በመምረጥ ያለ ምንም ሶፍትዌር ማየት ትችላላችሁ!)
💬 እነዚህን ሶፍትዌሮች በነፃ ማውረድ ይፈልጋሉ?
የትኛውን ሶፍትዌር መጫን እንደፈለጉ ኮሜንት ላይ ጻፉልን፤ የነፃ ማውረጃ ሊንኩን ወዲያውኑ እንልክልዎታለን! 👇
0973424250
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Bole
Addis Ababa
0000
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 20:00 |
| Tuesday | 08:00 - 20:00 |
| Wednesday | 08:00 - 20:00 |
| Thursday | 08:00 - 20:00 |
| Friday | 08:00 - 20:00 |
| Saturday | 09:00 - 20:00 |
| Sunday | 08:00 - 20:00 |