Ethio plus
በኢትዮ-plus ገፃችን ሀገራዊ፣ ማህበረሰቧዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም አያሌ ሀሳቦችን እያነሳን እንነጋገራለን !!
30/09/2026
#አርቲስት ተሻለ ወርቁ (ተሼ) ማን ነዉ? 🌟
#አርቲስት ተሻለ ወርቁ (ተሼ) በኢትዮጵያ የፊልምና በቴአትር እና በሬዲዮ ተከታታይ ድራማ ለረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ በሙያው ጠንካራ ስራውን ወዳጅ ተወዳጅ ተዋናይ፣ ደራሲና ዳይሬክተር ነው።
በአዲስ አበባ ፒያሳ በተለምዶ ሰራተኛ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ተወልዶ ያደገውና የመጀመሪያ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአፍሪካ አንድነትና በሚኒሊክ ትምህርት ቤቶች የተከታተለው ይህ ድንቅ አርቲስት ከፍተኛ ትምህርቱን በሶሽሎጂ እና በትያትሪካል አርት ዘርፍ ካጠናቀቀ በኋላ የመጀመሪያ የጥበብ ጅማሮውን በፋቡላ ክበብ አድርጎ በ1991 ዓ.ም በአንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በቋሚነት ተቀጠረ።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት መድረክ ላይ በርካታ ስራዎችን በድርሰት፣ በዝግጅት (በዳይሬክተርነት) እና በትወና ጨምሮ በከፍተኛ የሙያ ዲሲፕሊን እያበረከተ ይገኛል። በዚሁ ታሪካዊ መድረክ ላይ ያቀረበው የመጀመሪያው ድንቅ ቴአትሩ «ጥምዝ» የተሰኘው ሥራው የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላም ትልቅ እውቅና እና የተመልካች ፍቅር ያገኘበትን «ትዳር ሲታጠን» ጨምሮ በርካታ የመድረክ ቴአትሮችን በመጻፍ፣ በማዘጋጀትና በመተወን በመድረክ ጥበብ ላይ የዳበረና የማይናወጥ የሙያ መሠረት ጥሏል።በመድረክ ጥበብ ይህንን ያህል ሰፊ ልምድ ካካበተ በኋላ ሁለገብ ብቃቱን ይዞ ወደ ሲኒማው ኢንዱስትሪ በመቀላቀል በፊልሞች ላይ ውስብስብና ጠንከር ያሉ የክፋትና የሴራ ገጸ-ባህሪያትን በሚያስገርም ተፈጥሯዊ ብቃትና አሳማኝ በሆነ መልኩ በመጫወት በአድናቂዎቹ ዘንድ የራሱ የሆነ ትልቅ የትወና መታወቂያና ሰፊ ተወዳጅነትን ለማግኘት በቅቷል።
ከካሜራ ጀርባ ባለው ሕይወቱ ለሥራው የማይደራደር፣ ጠንካራ የሥራ ዲሲፕሊን ያለውና በጥራት ላይ የሚያተኩር ባለሙያ መሆኑን የሥራ አጋሮቹ ይመሰክሩለታል። ከዚህም ባሻገር ከአዳዲስ ወጣቶች ጀምሮ እስከ አንጋፋ አርቲስቶች ድረስ ካሉ የሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመከባበርና በመደጋገፍ የሚሠራ እጅግ ቀና፣ ትሁትና ተጫዋች ስብዕና ያለው የጥበብ ሰው ነው።የግል ሕይወቱን ከአላስፈላጊ የሚዲያ ጫጫታዎች አርቆ በፕሮፌሽናል መንገድ መምራት የሚመርጠው ተሻለ ባለትዳርና የልጆች አባት ነው።ሁለገቡ አርቲስት በትውና ፣ እና በዝግጅት ከታሳተፈባቸው ፊልምዎች መካከል በጥቂቱ «ቤቴ ሚስቴ»၊ «ባለቀ ሰዓት» «የመንግሥት ሥራ»၊ «ሰርግ ከአሜሪካ» "አለም በቃኝ" እና በቅርቡ ከአርቲስት ሳምሶን ታደሰ (ቤቢ) ጋር በጋራ በመተወን ትልቅ አድናቆትና የተመልካች ፍቅር ያተረፈበት «ሁለት ፊት» እንዲሁም «ዲያስፖራው» የተሰኙ በርካታ ስኬታማ የሲኒማ ፊልሞችንና የመድረክ ሆነ ቴአትሮችን ለሕዝብ አቅርቧል የጥበብ ፈርጥ መሆኑን አስመስክሯል።በአጠቃላይ አርቲስት ተሻለ ወርቁ ሁልጊዜም ራሱን እያደሰና ለሙያው ታማኝ ሆኖ በመቀጠል በኢትዮጵያ የፊልም ጥበብ ውስጥ ደማቅ አሻራውን እያሳረፈ የሚገኝ ድንቅ ባለሙያ ነው።
28/09/2026
ትንቢት የሚመስል ንግግር እና የእግዚአብሔር ተአምር❤ ዓለምን ጉድ ያስባለ የእምነት ጥንካሬ
ከስቃይ ወደ ተስፋ! | የዚህች ህፃን ህይወት ታሪክ/A strength of faith that astonished the world.#ethioplus Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/c...
27/09/2026
#የአቶ ረዳ ካሕሳይ ህልፈት ተሰማ፤ አቶ ጌታቸው ረዳም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ — የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር እና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ፓርቲ (ስምረት) ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ አባት — አቶ ረዳ ካሕሳይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታወቀ።
የፖለቲካ አመራሩ አባት ህልፈትን አስመልክቶ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ፓርቲ ለአዲስ ማለዳ በላከው ይፋዊ መግለጫ፣ በህይወት መለየታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። መግለጫው ከሐዘን መግለጫው ባሻገር ስለ ስርዓተ ቀበራቸውና ተያያዥ ጉዳዮች ያካተተው ዝርዝር መረጃ የለም።
በሌላ በኩል አቶ ጌታቸው ረዳ ከአባታቸው ህልፈት በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባስተላለፉት ልብ የሚነካ መልዕክት፣ ፈረንሳዊውን ተዋናይና ደራሲ ዢን አኑይ (Jean Anouilh) በመጥቀስ፦ «“ከመጮኽ ውጪ ምንም ማድረግ የማይቻልበት ጊዜ አለ!” ያለው ይመስለኛል፤ ይህ ጊዜም ያ ይመስለኛል» ሲሉ የተሰማቸውን ጥልቅ የሐዘን ስሜት የገለጹ ሲሆን፣ ከጎናቸው ለቆሙና መጽናናትን ላመኙላቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ለአቶ ጌታቸው ረዳ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።
27/09/2026
#ትግስት አሰፋ - በበርሊን ማራቶን - ጉዳት ቢገጥማትም - አስደናቂ ድል በመቀዳጀት - የራሷን የውድድር ስፍራ ታሪክ አሻሻለች
በበርሊን ማራቶን የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትግስት አሰፋ በውድድሩ ማጠናቀቂያ አካባቢ የጉዳት ህመም ቢገጥማትም በጽናት በመታገል ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ04 ሰከንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች።
ትግስት ለ40 ኪሎ ሜትር ያህል የዓለምን ማራቶን ሪኮርድ በሰበረ ፍጥነት ውስጥ የነበረች ሲሆን፣ ውድድሩ ሊጠናቀቅ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ሲቀሩት በገጠማት የጡንቻ ወይም የጅማት ህመም ምክንያት እያነከሰችና በከፍተኛ ጽናት መስመሩን ለማለፍ ተገዳለች። ይህም ሆኖ ያስመዘገበችው ሰዓት የራሷን የግል ምርጥ ሰዓት (PB) ያሻሻለበት፣ የበርሊን ማራቶን የውድድር ስፍራ አዲስ ሪኮርድ (Course Record) ያስመዘገበችበት እንዲሁም በታሪክ ሶስተኛው ፈጣኑ የሴቶች ማራቶን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል።
አትሌቷ ከውድድሩ በኋላ በህክምና ድንኳን ውስጥ እርዳታ የተደረገላት ሲሆን፣ በፅናቷና ባሳየችው ድንቅ የውድድር መንፈስ ከአለም አቀፍ የቪዲዮ እና የጨዋታ አሰራጮች ከፍተኛ ሙገሳን አትርፋለች።
27/09/2026
#እናቴን ሲሳደብ ግን ቅስሜ ተሰበረ 😭
የቴኳንዶ ማስተር እና የኤምኤምኤ (MMA) ተወዳዳሪው ሀገረ ሰላም በEBS "ቅዳሜን ከሰዓት" (የሻይ ሰዓት) ፕሮግራም ላይ የተናገራቸውን ንግግሮች በሙሉ እንደወረደ በክፍል ተለይተው ከዚህ በታች ቀርበዋል።
•ስለ ኤምኤምኤ (MMA) ውድድር እና የውድድር #ስሜት
"ኤምኤምኤውን ያው ብዙ ሰው ወዶታል። ሳቢ ነው በቃ፤ ደስ ይላል ደስ ይላል። እኔም እራሴ ስወዳደር/ስትደባደብ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፣ የምወደው።እኔ ሪንግ ውስጥ ስገባ እራሴን እራሱ አላውቀውም፤ በቃ ሃይፐር ነኝ በጣም ማለት ነው። ቦታውም ይፈልጋል። አዎ የኤምኤምኤን ውድድር ሰው በጣም ወዶታል፣ በጣም ኢንጆይ እያደረገበት ነው። ምናልባት ከጥቂት ጊዜያቶች በኋላ እንደነ ቴኳንዶ፣ እንደነ አትሌቲክስ አገር የሚያስጠራ ስፖርት ይሆናል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ አልሸነፍ ባይነት አለው። ተፈጥሮአችንም ጥሩ ነው ብዬ ነው የማስበው እና በደንብ ብዙ ልጆችን ማውጣት ይቻላል በዚህ ስፖርት። በጣም አቅም ያላቸው ልጆች አሉ፤ በደንብ ከተሰራበት እንደ አትሌቲክስ፣ እንደ ቴኳንዶ፣ እንደ ቦክስ ምናምን ውጤት ማምጣት ይቻላል።"
"ለምሳሌ አሁን እኔ የምሰራበት ታይኮዋንዶ ስፖርት ከአትሌቲክስ ቀጥሎ ውጤታማ... በኦል አፍሪካ ጌም ስንሄድ ውጤት ይዘን የምንመጣበት ትልቅ ውድድር ነው። መንግስትም ትኩረት የሚሰጠው ውድድር ነው። ኦል አፍሪካ ጌም ስንሄድ 'ይሄን ያህል ወርቅ፣ ይሄን ያህል ብር፣ ይሄን ያህል ነሐስ ከናንተ እንጠብቃለን' ተብለን ነው የምንሄደው። በጣም በቃ ውጤታማ ነን፣ ስኬታማ ነን በዛ ውድድር ላይ። ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ ቴኳንዶን ስፖርት ሁሉም ሰው ሪስፔክት ማድረግ አለበት፤ በጣም ዲሲፕሊን ያስተምራል።"
•ስለ ቴኳንዶ #ዲሲፕሊን እና የፌስ-ኦፍ (Face-off) ስነምግባር
"ቢኒያምም የ'አይቲኤፍ' ቴኳንዶ ተማሪ ነው፣ ተወዳዳሪም ነበር ከዚህ በፊት። አውቀዋለሁ በደንብ። እኔ ደግሞ የ'ወርልድ ቴኳንዶ' ተወዳዳሪ ነኝ ረጅም አመት። ስለዚህ ወርልድ ቴኳንዶ ላይም አይቲኤፍ ላይም ስትሄድ መጀመሪያ ገና ስትገባ ኢቲክስ ነው የምትማረው፤ በቃ ዲሲፕሊን! ዲሲፕሊን ከሌለ ጭራሽ አስተማሪው ሊያባርርህ ይችላል፤ ምንም ጎበዝ ብትሆን አይመለከተውም፣ ያስወጣሃል።"
•ስለ ቤተሰቡ እና ስለ #ሚስቱ ጭንቀት
"ከባድ ነው፤ ለእናት ከባድ ነው፣ ለአባት ከባድ ነው። ባለቤቴም በጣም ተጨንቃ ነበር። እኔ እንደውም 'በቃ ምጧ መጣ... ነፍሰጡር ነች' ብዬ አደራ ያልኩት ሰው አለ። ከዛ ያው ጭንቀት አለው፤ በቲቪ ሲያዩ ምናምን... አዎ ትንሽ እኔንም ደግሞ ብዙ አላወቁኝም። ቤተሰቦቼም፣ ባለቤቴ ታውቀኛለች—እሷም ስፖርተኛ ነች፣ ብሄራዊ ቡድን ነበረች ከቴኳንዶ ማለት ነው። ታውቀኛለች ግን እንደዚህ አልጠበቀችኝም። ይሄኛው ሌላ ስፖርት ላይ ስሄድ የመጀመሪያዬ እንደመሆኑ ትንሽ ፈራች።"
"ቤተሰቦቼ ደግሞ ከወንድሜ ውጪ የኔን ውድድር ማንም አይቶ አያውቅም። ከዚህ በፊት ባሉ ውድድሮች ማንም አያይም፣ በቃ ማየት አይፈልጉም። እናቴና አባቴ ብቻ ናቸው ቤት የነበሩት፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዳለ መጥተው ነበር። እናቴ ተንበርክካ ነበር፤ እየጸለየች ስታይ ነበረች። ከባድ ነው... እነሱ ሴንሴቲቭ ናቸው።"
•ከውድድር በኋላ ስላጋጠሙት #ስድቦች እና ስሜቶች
"ሚስማር ሲመታ ይጠከራል አይደል? ስለዚህ ነገሮች በሙሉ ያጠነክሩኛል። ነገር ግን አንድ ሰው የፈለገውን መደገፍ መብት አለው፤ ማንም ሰው ማለት ነው። በሰዓቱ ቁጭ ብዬ ነበር፣ አንገቴን ደፍቼ ነበር... እኔ በቢንያም መሸነፌ አይደለም፤ እዛ ጋር ልክ ያልሆኑ ቃላት ሲጠቀሙ ሰማሁኝ። እናቴን ነው የሰደቡት! እናቴ ደግሞ ቤቴ ልጄን መድሃኒአለም ጥበቅልኝ እያለች ተንበርክካ እየለመነች፣ እየተማጸነች ነው ያለችው። እናቴ... እኔ እኮ አንገቴን ስያዝ አባቴ ነው የነገረኝ፣ ወደኋላ እሷ እራሷ ወድቃ ውሃ ምናምን አድርገውላት ነው የተነሳችው።"
"እናቶችን መስደብ... የኢትዮጵያ እናቶች እኮ ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው። እንጨት ተሸክመው፣ ጉሊት ሽጠው ዋጋ ከፍለው ያሳደጉንን እናት በልበ ሙሉነት ትልልቅ እንግዶች በተቀመጡበት፣ እነሱ መሃል ሆኖ ያንን ቃላት መሰንዘር የእውነት ቅስሜን ነው የሰበረው። ውስጤ ሞራሌ ነው የተነካው፣ አጠገባችን ናቸው... በጣም ነው ያዘንኩት፣ እባክህ አልቅሼ ነው የመጣሁት! ግን ምንም እዛ ጋር አላንጸባረቅኩም፤ ምንም ስለማልፈልግ። አሁንም እግዚአብሔር አምላክ እሱም ከእናት ነው የተወለደው እና እናትን መስደብ ምን ያህል ፔንፉል እንደሆነ፣ እናቶች በምን አይነት መልኩ እንዳሳደጉ ስለምታውቁ መናገር ማስረዳት አይጠበቅብኝም። የኔ እናት ሳትሆን የሁሉንም እናት ነው የሰደደቡት። በዛ ልክ እናትን መሳደብ ውስጤ ሊወጣልኝ አልቻለም፤ ግን እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጠው ነው የምለው። ሌላው መደገፍ መብቱ ነው፤ የፈለገውን መደገፍ ይችላል።"
25/09/2026
#ካሉበት ሞያ በተጨማሪ- በሌላ ስራ የተዋጣላቸው አርቲስቶች🤔
ካሉበት ሞያ በተጨማሪ በሌላ ስራ የተዋጣላቸው አርቲስቶች ። More talente Join this channel to get access to perks:https://www.youtube.com/c...
25/09/2026
#በመቐለና በሌሎች የትግራይ አካባቢዎች #የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ መቋረጥን ተከትሎ #የሳፋሪኮም ሲም ካርድ ሽያጭ ማዕከሎች ተጨናነቁ
በመቐለ ከተማና በመላው ትግራይ ክልል የኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክና የኮሙኒኬሽን አገልግሎት በድንገት መቋረጡን ተከትሎ፣ በዛሬው ዕለት በማለዳ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርድ ሽያጭ ማዕከሎች በደንበኞች ተጨናንቀው አርፍደዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መቋረጥ ህዝቡ ከወዳጅ ዘመዶቹና ከመረጃ አውታሮች ጋር የሚገናኝበትን መስመር በመዝጋቱ፣ አማራጭ የኔትወርክ መስመር ለማግኘት በርካታ ነዋሪዎች ወደ ሳፋሪኮም የሽያጭ ጣቢያዎችና ወኪሎች በመምጣት አዳዲስ ሲም ካርዶችን ለመግዛት ረጅም ሰልፍ ይዘው ታይተዋል።
የሳፋሪኮም አውታረ መረብ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም በከፊል እየሰራ የሚገኝ በመሆኑ፣ ህዝቡ የመረጃ ግንኙነቱን ለማስቀጠል ወደዚህ አገልግሎት ለማዘንበል መገደዱ ተገልጿል።
25/09/2026
#ከዛሬ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌትን በአዲስ አበባ ማሽከርከር እንደተከለከለ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታወቀ።
ፖሊስ እንደገለጸው፣ አንዳንድ ወንጀል ፈጻሚዎች ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም የቅሚያና የስርቆት ወንጀሎችን ሲፈጽሙ ተይዘው በምርመራ ላይ ይገኛሉ። ወንጀል ፈጻሚዎችም ከቦታ ቦታ ለመዘዋወርና የተሰረቁ እቃዎችን ለማጓጓዝ ሞተር ብስክሌትን በብዛት እንደሚጠቀሙ ገልጿል።
በተጨማሪም ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ደንቦችን እንደማያከብሩ ፖሊስ ጠቁሟል። ከተጠቀሱት ጥሰቶች መካከል ቀይ መብራት ማለፍ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን ገጭቶ ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳይጠቀሙ ማሽከርከር እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ ወይም የተበላሹ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም ይገኙበታል።
በመሆኑም ወንጀልን ለመከላከልና በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን ለመቆጣጠር፣ ከኮድ 4 ተሽከርካሪዎችና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌቶች በስተቀር ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌትን በአዲስ አበባ ማሽከርከር ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ተከልክሏል።
የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች መመሪያውን እንዲያከብሩ ፖሊስ አሳስቧል። እገዳውን በመተላለፍ ማሽከርከር በሚቀጥሉ ላይም ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ ገልጿል።
25/09/2026
#ታንዛኒያዊቷ ድምፃዊት ናንዲ ተገቢ
ያልሆነ ልብስ በመልበሷ ተቀጣች
ታዋቂዋ የታንዛኒያ ድምፃዊት ናንዲ በዳሬሰላም በተካሄደው የ«ሚስ ዩኒቨርስ ታንዛኒያ» ውድድር ላይ ያደረገችው አለባበስ «የተመልካቾችን ክብር የሚጥስና ነውረኛ ነው» በመባሉ 3 ሚሊዮን የታንዛኒያ ሺሊንግ (ወደ 1,100 ዶላር ገደማ) እንድትከፍል ተወስኖባታል።
የሀገሪቱ የኪነ-ጥበብ ምክር ቤት እንዳስታወቀው፣ ናንዲ ጥፋቷን አምና የተቀጣችውን ገንዘብ የከፈለች ሲሆን፣ የትርኢቱን ቪዲዮ ከማህበራዊ ሚዲያ ገጾቿ ላይ አንስታለች። ይሄን ተከትሎም ሥራዋን እንድትቀጥል የተፈቀደላት ቢሆንም፣ በምክር ቤቱ ክትትል ሥር ትቆያለች። የውድድሩ አዘጋጅ አካልም በዚሁ ምክንያት ተመሳሳይ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።
24/09/2026
#በገዛ ልጃቸው ላይ የተፈጸሙት አሰቃቂ እና አስነዋሪ ድርጊት 💔
ሀዋሳ ዙሪያ (ኢሞሼ ሁሞ) — በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ልዩ ስሙ «ኢሞሼ ሁሞ» ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አእምሮን የሚፈታተን፣ ሰብአዊነት የጎደለው እና እጅግ አስነዋሪ የሆነ ድርጊት በወላጆች አማካኝነት በገዛ ልጃቸው ላይ ተፈጽሟል።
እንደ ተገኘው መረጃ ከሆነ፣ ድርጊቱ የተቀሰቀሰው ወላጆች በሌሉበት ወቅት ልጅቷ የቤተሰቧን ቡና ከእርሻ መሬታቸው በመልቀም ገበያ አውጥታ ሸጣለች በሚል ምክንያት ነው። ወላጆች ወደ ቤት በተመለሱበት ወቅት “ያለ እኛ ፈቃድ ለምን ቡናውን ለቀምሽ? ለምንስ ሸጥሽ?” በሚል እጅግ አነስተኛ በሆነ የገንዘብ እና የቡና ጥቅም ምክንያት ከባድ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ልጅቷ ላይ ድብደባ እና እንግልት ፈጽመውባታል።
ወላጆቹ በቁጣ ተነሳስተው ቢላዋ በእሳት በማሞቅ የገዛ ልጃቸውን አንገት ጨምሮ አካላቷን በማቃጠል እጅግ አሰቃቂ የቃጠሎ ቁስል አድርሰውባታል።
ይሁን እንጂ ድርጊቱ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እና የልጅቷ ሕይወት ሳያልፍ የአካባቢው የቀበሌ አመራሮች፣ የሕግ አካላት እና ህብረተሰቡ በፍጥነት በቦታው በመድረሳቸው ልጅቷን በሕይወት ማትርፍ ተችሏል። በአሁኑ ወቅት የሕግ አካላት ድርጊቱን የፈጸሙትን ወላጆች በቁጥጥር ስር ለማዋል እና አስፈላጊውን የሕግ እርምጃ ለመውሰድ እየሰራ ይገኛል።
ይህ ድርጊት በህብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ ቁጣን እና ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፣ በምንም ዓይነት መለኪያ፣ ምክንያት እና ባህል የማይደገፍ፣ ሰብአዊነትን የሚጻረር አሰቃቂ ድርጊት ነው። ልጆች የቤተሰብ እና የህብረተሰብ ሀብት በመሆናቸው በምንም ዓይነት ጥፋት ውስጥ ቢገቡ እንዲህ ዓይነቱ አረመኔያዊ ቅጣት ሊፈጸምባቸው እንደማይገባ እና ህብረተሰቡም ይህን መሰል ድርጊቶችን በፅኑ ሊያወግዝ እንደሚገባ መልእክት ተ አስተላልፏል።
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
4 Kilo
Addis Ababa
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Ethio plus posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.