Tan Engineering

Tan Engineering

Share

Tan Engineering/Sports construction company in Ethiopia. Quality is our difference.

27/05/2026

በሶማሌ ክልል ሰርተን በማጠናቀቅ ላይ የምንገኘው ስታዲየም!

15/04/2026

የሃላባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማደጋችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እንወዳለን።

ይህ ስኬት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን ለአመታት ተደክሞበት እንደሆነ መመስከር ይቻላል። በቀጣይም በውቡ ስታዲየማችሁ በደማቅ ደጋፊዎቻችሁ ፊት ስትመኙት የነበረውን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን ለማድረግ ያብቃችሁ።

ጠንካራ፣ ስራ ወዳድ እና በልማት ቁርጠኛ የሆነ ማህበረሰብ እና አመራር ከጀርባችሁ ስላለ በፕሪሚየር ሊጉም ስኬታማ እንደምትሆኑ እምነታችን ነው።

በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ!
Tan Engineering

Photos from አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau .'s post 04/02/2026
Photos from Tan Engineering 's post 04/02/2026

ምቹ የእግር ኳስ መጫዎቻዎችን ማስፋፋት አላማ አድርጎ እየሰራ ያለው ታን ኢንጂነሪንግ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የወረዳ 8 ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ግንባታ በይፋ አስጀመረ።

በማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ: "መንግስት ከለውጡ በኋላ አገር ተረካቢ ትውልድ ለማነፅ የሚያስችሉ የስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በመስራት ላይ ይገኛል።

አሁን በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገነባው ሜዳም ሳቢ፣ ማራኪና ጥራቱን የጠበቀ ሲሆን፤ ለሌሎች አካባቢዎችም እንደ ሞዴል የሚያገለግል መሆኑን አቶ በላይ ገልፀዋል።

ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው "የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ማስፋፋት ወጣቶችን ንቁ፣ ጤናማና ግብረ-ገብነትን የተላበሱ ለማድረግ ያስችላል። ንቁና ብቁ ትውልድ የማፍራት ኃላፊነት የሁላችንም ድርሻ በመሆኑ፣ ይህ ፕሮጀክት ለነገ አገር ተረካቢዎች ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።"

አቶ ክብረዓለም ደምሴ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ም/ቢሮ ሀላፊ: "በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በጥራትና በአጭር ጊዜ ገንብተን እያስመረቅን እንገኛለን። ይህንም ሜዳ በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቆ ለስፖርት ቤተሰቡ ክፍት እንደሚደረግ ተናግረዋል ።"

የፕሮጀክቱ ስራ ተቋራጭ አቶ ፋአድ ይብራሂም በበኩላቸው፣ የተሰጣቸውን እድል በመጠቀም ስፖርቱ የተሰጠውን ትኩረት በሚመጥን መልኩ ስራውን በጥራትና በጊዜው አጠናቀው እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ከታን ኢንጂነሪግ ጋር በመተባበር በወረዳ 08 ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚለማው ስፖርት ማዘውተርያ ስፍራ ግንባታው በ3 ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡

Photos from Tan Engineering 's post 11/01/2026

ጥራት፣ ፍጥነት እና ታመመኝነት የማንደራደርባቸው መርሆዎቻችን ናቸው። አደራችንን ለመወጣት እና ደንበኞቻችን በስራችን እንዲኮሩ ብሎም እንዲመሰክሩ ማድረግ የዘወትር ትጋታችን ነው።

Tan Engineering

11/01/2026

ውድ ሃላባዎች እንኳን ለዘመን መለወጫ 'ሴራ' በዓል አደረሳችሁ! እኛም በዚህ ቀን የሰጣችሁንን አደራ በከፍተኛ ጥራት ተወጥተን በማስረከባችን ድርብ ደስታ ተሰምቶናል።

Photos from Tan Engineering 's post 04/01/2026

የሃላባ ስታዲየም የትራክ ንጣፍ ስራ በስኬት ተጠናቋል!

27/10/2025

Credit: Dire tv

Website

Address


Semay Tower
Addis Ababa
ADDIS