SHEGER FM 102.1 RADIO
SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!
Hear us live on www.ShegerFM.com, dedicated phone numbers, and mobile Apps. ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡
ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡
ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡ የሸገር ዓላማ ከወገናዊነት የነፃ ትክክለኛ የሕዝብ ድምፅ መሆን፣ ሥነ ምግባርን የጠበቀ የጋዜጠኝነት መርህን መከተልና የተሣካለት የኢንፎቴይመንት (Information & Entertainment) ሬዲዮ ጣቢያ መሆን ነው፡፡
ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡
ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
በእስራኤል እና በቱርክ መካከል ጦርነት ሊጫር በቋፍ ላይ ነው! ምን መጣ ?
https://youtu.be/GCHDM272N4A
#ታሪክን የኋሊት
“የሴቶች ለእኩልነት አድማ”
26/08/2026
የነሐሴ 20 2018
ፍየሎችንና በጎችን የሚጨርሰው በሽታ አሁንም ስጋት መሆኑን እንደቀጠለ ነው፡፡
ደስታ መሰል በሚል ስያሜ የሚታወቀው በሽታ በአምስት ቀናት ውስጥ የሚገድል በመሆኑ በተለይ የአርብቶ አደሮችን መተዳደሪያ እያሳሳው ነው፡፡
ስጋቱን ለመቀነስ ምን እየተደረገ ነው?
ዶ/ር ሲሳይ ጌታቸው በግብርና ሚንስቴር የእንስሳት ጤና እና ቨተርነሪ ፐብሊክ ሔልዝ ሥራ አስፈፃሚ ናቸው።
ኃላፊው ይህንን በሽታ ለመከላከል በሚሊየን ለሚቆጠሩ በጎችና ፍየሎች ክትባት እየተሰጠ ነው ብለዋል።
በሽታው በብዛት በሚገኝበት የአርብቶ አደሮች አካባቢ ፣ አርብቶ አደሮች ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ሥፍራ እንስሳቶቻቸውን ይዘው የመዘዋወር ልምድ ስላላቸው ለበሽታው መዛመት ዕድል መፍጠሩንም ዶ/ር ሲሳይ ይናገራሉ።
በዚህም ምክንያት በሽታው የለም ያልንባቸው ሥፍራዎች ሳይቀሩ በሽታው ተከስቷል የሚል ሪፖርት ይደርሰናል ይላሉ።
ኢትዮጵያ እስከ 2030 በሽታውን የማጥፋት ዕቅድ እንዳላት የሚያነሱት ዶ/ር ሲሳይ ጉዳዩ ድንበር ተሻጋሪ እንደመሆኑ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ስምምነት ተደርጓል ብለዋል።
ይሁን እንጂ በዘርፉ ያለው የፋይናንስ እጥረት በሽታውን ለመከላከል ፈተና መሆኑንም አንስተዋል።
አርብቶ አደሮች ስለ ደስታ መሰል በሽታ ያላቸው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑ ለበሽታው በቀላሉ መስፋፋት ምክንያትም መሆኑንም ኃላፊው ያስረዳሉ።
ግጭት ባለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚፈለገው ልክ ክትባት መስጠትና አስፈላጊውን የእንሰሳት የጤና ክትትል ማድረግ አለመቻሉ፣ በሽታውን የማጥፋቱን ሥራ ፈትኖታል ብለዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚውን ድርሻ በያዘችበት የእንስሳት ሃብት ላይ ሥጋት የደቀነ በሽታ በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ዶ/ር ሲሳይ ጌታቸው ጠይቀዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ...
https://tinyurl.com/avdubsbp
ንጋት መኮንን
ነሐሴ 20 2018
በኢትዮጵያ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ዓመት ውስጥ ካሉ ሴቶች መካከል 11.1 በመቶ የሚሆኑት የጾታዊ ጥቃት፣ 24.9 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የአካላዊ ጥቃት ሰለባ እንደሚሆኑ የኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ እና ጤና ጥናት መረጃ አሳይቷል።
የወንጀሎች መስፋፋት እና የጥቃት አፈጻጸም ጭካኔ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም፣ የህግ ማሻሻያ አለመደረጉ እና የህግ ማስከበር አፈጻጸም ክፍተቶች ተጠቂዎች ተገቢውን ፍትህ እንዳያገኙ ማነቆ መሆናቸው ይጠቃሳል፡፡
በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ሴቶች እና ህፃናት የቅርቤ ባሏቸው ሰዎች አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጥቃቶች እንደሚደርስባቸው የሚነገር ሲሆን ጥቃቱም ዓይነቱን እየቀያየረ መምጣቱን የዘር ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
የህፃናትን የወደፊት ተስፋ የማጨለም፣ ልጆችን ካለ እናት የማስቀረት፣ ሴቶች ላይ እንዲህ ያሉ በደሎችን የመፈፀም ጭካኔው እንደማህበረሰብ ከየት የመጣ ነው?
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ.....
https://tinyurl.com/2bsw84an
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7
26/08/2026
#ማንንምንእንጠይቅልዎ
እናቴን ለማስታመም 10 ቀን ባስፈቅድም ከስራ ተባረርኩኝ የቦርዱ ሰብሳቢ ምላሸ
ማንን ምን እንጠይቅልዎ | እናቴን ለማስታመም 10 ቀን ባስፈቅድም ከስራ ተባረርኩኝ SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station...
26/08/2026
#ማስታወቂያ
ሐምሌ 8ቀን 2018ዓ.ም በይፋ የተጀመረው ታላቁ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በአሁኑ ወቅት ወደ ወሳኝ ምዕራፍ የተሸጋገረ ሲሆን በጉባኤው 8 አጀንዳዎች የቀረቡና ተወካዮች የተወያዩባቸው ናቸው።
ሂደቱን የበለጠ ግልፅ ለማድረግ የአለማቀፍ ልማት አጋሮች እና የለጋሽ ሀገራት ልዑካን በቦታው ተገኝተው የክትትል ምልከታ ማድረጋቸውን የተናገረው ኮሚሽኑ አስካሁንም ከ50በላይ ከሚሆኑ የመገናኛ ብዙኀን ተቋማት ጋር በመተባበር ወቅታዊ መረጃዎችን ለሕብረተሰቡ አያሳወቀ መሆኑን ገልጿል።
የነሐሴ 20 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች
#አሜሪካ
አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን አዲስ ማዕቀብ የተናጠል እርምጃ ነው ስትል ካታር ነቀፈችው፡፡
አሜሪካ ለወቅታዊው ቀውስ መፍትሄ ከማዕቀብ ይልቅ ለድርድር ቅድሚያ ልትሰጥ ይገባል ብላለች የባህረ ሰላጤዋ አገር ካታር፡፡
ካታር ሁሉም የባህረ ሰላጤው አገሮች የድርድር አማራጭን እንዲደግፉ በውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይዋ አማካይነት ጥሪ አቅርባለች፡፡
ከፓኪስታን በተጓዳኝ ካታርም አሜሪካ እና ኢራን ለመሸምገል እየጣረች ነው፡፡
ያም ሆኖ የሰላም ጥረታቸው ፍሬ እንዳላፈራ የካታር ሹሞች ተናግረዋል፡፡
የችግሩ መቀጠል ለቀጠናውም ሆነ ለመላው አለም ጠንቅ ይሆናል ብላለች ካታር፡፡
ከአሜሪካ አዲስ ማዕቀብ አስቀድማ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከኢራን ጋር የነበረኝን ሁሉንም የንግድ እና ምጣኔ ሐብታዊ ግንኙነት አቋርጫለሁ ማለቷን መረጃው አስታውሷል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝን የባህር መተላፊያ ወሽመጥ ከተቀባሪ ፈንጂዎች አፅድተነዋል አሉ፡፡
ትራምፕ በወሽመጡ ኢራን ከተጨማሪ ፈንጂ ቀበራዎች እንድትታቀብ ማስጠንቀቃቸውን አልጀዚራ ፅፏል።
ለፈንጂ ቀበራ የሚሰማሩ የኢራን የጦር መርከቦችን እና ጀልባዎችን አናስተርፋቸውም ፤ በሙሉ እናወድማቸዋል ሲሉ መዛታቸው ተሰምቷል፡፡
አሜሪካ እና ኢራን ስራ ላይ መዋል ያልቻለውን የጦርነት ማስቆሚያ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ በሆርሙዝ ጉዳይ እልህ እየተጋቡ ነው፡፡
የኢራን ሹሞች ሰሞኑን በሆርሙዝ የሚተላለፉ መርከቦች የኢራንን ህግ ካላከበሩ እርምጃ እንወስድባቸዋለን ሲሉ ዝተዋል፡፡
ጦርነቱን ተከትሎ የኢራን ፖለቲከኞች በሆርሙዝ ሙሉ ሉአላዊ ባለመብቶቹ እኛ ነን እያሉ ነው፡፡
ትራምፕ በፊናቸው ሆርሙዝን የአሜሪካ ግዛት አደርገዋለሁ ያሉት ሰሞኑን እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኦንታሪዮ ሐይቅን የአሜሪካ ሐይቅ ለማለት ተሰናድቻለሁ አሉ፡፡
ኦንታሪዮ ሐይቅ በካናዳዋ ኦንታሪዮ ግዛት እና በአሜሪካዋ ኒው ዮርክ አዋሳኝ የሚገኝ ሐይቅ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡
ትራምፕ የኦንታሪዮን ሐይቅ የአሜሪካ ሐይቅ ብዬ እጠራዋለሁ ሲሉ እወቁልኝ ያሉት በትሩዝ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ነው ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል የሜክሲኮ ባህረ ሰላጤን የአሜሪካ ባህረ ሰላጤ ሲሉ የፅሁፍ ትዕዛዝ ማውጣታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡
ትራምፕ ወደዚህ የሀይቅ መጠሪያ ንትርክ ያመሩት ካናዳ እና አሜሪካ ወደ ታላቅ የንግድ ጦርነት በገቡበት አጋጣሚ ነው፡፡
ካናዳ በአሜሪካ ለተቆለለባት የ50 በመቶ አዲስ የቀረጥ ታሪፍ ምላሽ ከአሜሪካ ወደ ካናዳ በሚገቡ እና የ20 ቢሊዮን ዶላር የዋጋ ግምት ባላቸው ሸቀጦች እና ምርቶች ላይ የ50 በመቶ የቀረጥ ታሪፍ ስራ ላይ እንደምታውል እወቁልኝ ማለቷ ተሰምቷል፡፡
#ታንዛኒያ
የታንዛኒያው ምክትል ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ንቺምቢ ሀላፊነቴን በገዛ ፈቃዴ ለቅቄያለሁ አሉ፡፡
ንቺምቢ ስልጣን የለቀቁት ቀደም ሲል ለፕሬዘዳንቷ በገባሁት ቃል መሰረት ነው ማለታቸው በሀላፊነት መልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ መጥቀሳቸውን የን ድረ ገፅ ጥፏል፡፡
ኢማኑኤል ንቺምቢ ሀላፊነቴን በገዛ ፈቃዴ ለቅቄያለሁ ያሉት የአገሪቱ ፕሬዘዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሌላ ምክትል ፕሬዘዳንት ለመሾም እንደሚፈልጉ ስለተረዳሁ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
የታንዛኒያ መገናኛ ብዙሃን በፕሬዘዳንቷ እና በምክትላቸው መካከል መቃቃር ስለመፈጠሩ ሲያወሩ መሰንበታቸው በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
አገሪቱ ነፃነቷን ካገኘች አንስቶ ላለፉት 62 አመታት ስልጣን በቃኝ ብሎ ከሀላፊነት በመሰናበት ምክትል ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ንቺምቢ የመጀመሪያው ናቸው ተብሏል፡፡
ንቺምቢ ስልጣን የለቀቁት ሀላፊነቱን በተረከቡ ከ10 ወራት በኋላ እንደሆነ መረጃው አስታውሷል፡፡የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ከሳውዲ አረቢያ ጋር የደረሰችውን ኒኩሊየር ነክ የትብብር ስምምነት እንዲያፀድቅላቸው ወደ ኮንግረሱ ላኩት ተባለ፡፡
ስምምነቱ ሳውዲ አረቢያ የአሜሪካን የኒኩሊየር ቴክኖሎጂዎችን ለሰላማዊ አገልግሎቶች እንድታውል የሚያስችላት እንደሆነ ሬውተርስ ፅፏል፡፡
ትራምፕ ስምምነቱ ስራ ላይ እንዲውል ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ይፋዊ ግንኙነት እንደትመሰርት በቅድመ ሁኔታነት አቅርበዋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ለመመስረት በቅድሚያ የፍልስጤማውያን ነፃ መንግስት ህልውና ማግኘቱን ማረጋገጥ አለብኝ ስትል ቆይታለች፡፡
በዋሽንግተን የሳውዲ ኤምባሲ የትራምፕን አስተያየት በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ እንዲህም ነው ፤ እንዲያም ነው አለማለቱ ተጠቅሷል፡፡
የኔነህ ከበደ
ነሐሴ 20 2018
የዋጋ ግሽበት በወር እስከ ሁለት ነጥብ 6 በመቶ እየጨመረ ቀጥሏል፡፡
ያለፈው ሐምሌ ወር አጠቃላይ የግሽበት ምጣኔም 15 ነጥብ 3 መድረሱን ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
በ2018 ዓ.ም በየወሩ 2 ነጥብ 6 እየጨመረ የቀጠለው የዋጋ ግሽበት የኑሮ ውድነቱን እያባባሰው መሆኑ ይነገራል፡፡
በሐምሌ ወር የምግብ ዋጋ በ15 ነጥብ 7 በመቶ ጨምሯል፡፡
በሐምሌ ወር ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶችም ዋጋቸው ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
የቤት ፣ ኤሌክትሪክ ክፍያና የነዳጅ ዋጋ በ13 ነጥብ 3 በመቶ መጨመሩን መረጃው ያሳያ፡፡
የቤት ውስጥ መጠቀሚያ ቁሶች ዋጋቸው በ15 ነጥብ 2 በመቶ ጨምሯል፡፡
የስልክ እና መሰል የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎቶች ዋጋ ደግሞ በ8 በመቶ መጨመሩ ተሰምቷል፡፡
የትምህረት 25 ነጥብ 3 በመቶ የጤና 12 ነጥብ 8 በመቶ እና የሬስቶራንትና ሆቴሎች አገልግሎትም ደግሞ 15 ነጥብ 3 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ሰምተናል፡፡
የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ በደፈናው በ15 ነጥብ 7 በመቶ ጨምሯል ቢባልም በተናጠል ሲታዩ እስከ 39 ነጥብ 4 በመቶ ዋጋቸው የናረ የምግብ ዓይነቶች መኖራቸውን ከወርሃዊ የግሽበት መረጃው ተመልክተናል።
የምግብ ዘይትና ቅቤ 20 ነጥብ 3 በመቶ ፣ እንቁላል ፣ ወተትና ዐይብ 18 ነጥብ 9 በመቶ ስጋ በ21 ነጥብ 6 በመቶ ዋጋቸው ከፍ ብሏል፡፡
ትዕግሥት ዘሪሁን
26/08/2026
ትንታኔ | በእስራኤል እና በቱርክ መካከል ጦርነት ሊጫር በቋፍ ላይ ነው! ምን መጣ ?
ትንታኔ | በእስራኤል እና በቱርክ መካከል ጦርነት ሊጫር በቋፍ ላይ ነው! ምን መጣ? #isreal #turkey SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station...
26/08/2026
ነሐሴ 20 /2018 የሸገር የቀትር ወሬዎችን በቀጥታ ይከታተሉ……
የሸገር የቀትር ወሬዎች ነሐሴ 20/2018 #shegerfm #ShegerWerewoch የሸገር የቀትር ወሬዎች ነሐሴ 20/2018
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa Bahirdar Road
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 00:00 |
| Tuesday | 08:00 - 00:00 |
| Wednesday | 08:00 - 00:00 |
| Thursday | 08:00 - 00:00 |
| Friday | 08:00 - 00:00 |
| Saturday | 08:00 - 01:00 |
| Sunday | 08:00 - 00:00 |