Hawassa Polytechnic College
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa Polytechnic College, College & University, Hawassa, Awassa.
Hawassa polytechnic is public TVET College established in 1990 E.C to offer technical and vocational education and training for the local community through both formal and non-formal programs aimed to provide morally up right and competent work force for
With Hawassa Polytechnic College – I just made it onto their weekly engagement list by being one of their top engagers!
✨ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን! ✨
=====🌼🌼====🌼🌼=====🌼🌼====
አዲሱ 2019 ዓ.ም ዓመት ለሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ፣ ለሰልጣኞቻችን፣ ለአሰልጣኞችና ሠራተኞቻችን እና ለአጋር አካላት እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ፣ የአብሮነትና የስኬት ዓመት እንዲሆን ከልብ ይመኛል። 🌿
አዲሱ ዓመት ከአዲስ ተስፋ ጋር አዲስ ዕድሎችን ሰንቆ ፤ የእውቀት፣ የክህሎት፣ የፈጠራና የልማት ጉዟችንን በበለጠ ትጋት እንድንቀጥል ያበረታታን።
አንጋፋው እና በሀገራችን ቀዳም በመሆን ISO ሰርተፊኬት ባለቤት የሆነው ጥራት ያለውን አካታች ስልጠና በመስጠት ላይ የምገኘው ኮልጃችን በተግባራዊ እውቀትና በዘመኑ የሥራ ገበያ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ክህሎት ያላቸውን ብቁ ዜጎችን በማፍራት እና ለሀገራችን ዕድገት የሚያበረክቱ የሰው ኃይል ማፍራቱን በቁርጠኝነት ይቀጥላል። 💙🌟
2019 ዓ.ም የሰላም፣ የብልጽግና፣ የአንድነትና የተሳካ የሥራ ዓመት ይሁንልን!
🌼 መልካም አዲስ ዓመት! 🌼
እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሰን! 🎉🇪🇹
🌼🌼የሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማኔጅመንት 🌼🌼
05/09/2026
19/08/2026
**የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብ ስምምነት ተፈራረመ**
የግብ ስምምነት የተፈራረመው በ ሐዋሳ ከተማ መምሪያ ስር ከሚገኙ አራት የ ሥ/አሰ/ቴክኖሎጂ እና ኢን/ል/ፅ/ቤቶች መካከል ሲሆን በዕለቱም የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ ጥሪ ለተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ስብሰባውን ሲከፍቱ ባጠናቀቅነው አመት የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ እስከ ማስመዘን ውጤቱ የእቅድ ትግበራችን የተሻለ ቢሆንም ለ2019 ዓ ም በልዩ ትኩረት መተግበር እንዳለበት አሳስበዋል፦
በዋናነት ከተነሱት ግቦች
- የ ኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን አገልግሎት
- የ ቴክኖሎጂ ሽግግር
- ገበያ አጫጭር ስልጠና እና
- የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ይገኙበታል:: ባለ ድርሻ አካላት ለአዲሱ አመት ስራችንን በጥንካሬና ውጤት በሚያመጣ መልኩ ትኩረት አርገን መስራት አለብን በማለት ተነሳሽነታቸውን አሳውቀዋል
# # #12/12/2018 ዓ ም # # #
18/08/2026
-Search-and-Readiness Training for Graduate Trainees
Hawassa Polytechnic College is taking action to prepare our graduates for the job market—starting today! With the job fair approaching, we've kicked off comprehensive training for over 850 graduate trainees in 2018 E.C. from developing standout CVs to mastering professional communication, these sessions are equipping our future professionals with the skills they need to shine and succeed!
23/07/2026
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከቀን 23/10/2018 እስከ 16/11/2018 ድረስ ኮሌጃችን ከተለያዩ ትምህርት ቤት የተመደቡ 714 ተማሪዎችን ተመቀበሎ እያስተናገደ መቆየቱ የምታወስ ስሆን: አጠቃላይ ፈተናው ያለምንም ሙሉ በሙሉ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን በማስመልከት ከተለያየ ሀገራችን ክፍል ለዝህ ፈተና የተመደቡ ፌደራል ፖሊስ: የፈተና ጣቢያ ኃላፊ: ሱፐርቫይዘሮች እንድሁም ፈታኞችን በዚህ መልኩ ለፈተናው ስኬት ላበረከቱት አስተዋፅኦ በማመስገን የምስክር ወረቀት በማበርከት ፕሮግራሙ ተጠናቅቋል::
21/04/2026
የሚመረቱ ቴክኖሎጂዎች የአከባቢን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ለገበያዉ የማቅረብ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሚገኙ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ገለጹ።
ኮሌጁ የሰራዉን የፕላስቲክ ሪሳይክልና ፕሮሰስ ቴክኖሎጂን በሀዋሳ ከተማ ተደራጅቶ እየሰራ ለሚገኝ ዉበት ሀዋሳ ኢንተርፕራይዝ በ1.2 ሚሊየን ብር ግዢ በመፈጸም ርክክብ አድርጓል ።
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ በኮሌጃቸዉ የሚመረቱ ቴክኖሎጂዎች የአከባቢን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ችግር ፈቺ አዋጪ ቴክኖሎጂ በመስራት ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች የማሸጋገርና በተቋም በማምረት ለገበያዉ የማቅረብ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በኮሌጃቸዉ ተሰርቶ በዛሬዉ ዕለት ለርክክብ የበቃዉ ቴክኖሎጂ የፕላስቲክ ሪሳይክል ፕሮሰስ ቴክኖሎጂ መሆንና የፕላስቲክ ዉጤቶችን የሚፈጭ ፣ የሚያጥብና የሚያደርቅ ቴክኖሎጂ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ ዲን የሀዋሳ ከተማ ለተጀመረዉን ስማርት ሲቲ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ተናግረዋል።
በኮሌጁ የተመረተዉ ይህ ቴክኖሎጂ ከዉጪ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ሊተካ የሚችል ቴክኖሎጂ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ ዲን ለአከባቢ ጥበቃ አበርክቶ ሚናዉ ከፍተኛ መሆንን ተናግረዋል።
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢ/ኤ ዋና አስተባባሪ ወ/ሮ ከበብሽ ተሰማ ይህ የተመረተዉ ቴክኖሎጂን እሴት ሰንሰለት ትንተናን መነሻ በማድረግ የተሰራ ቴክኖሎጂ በማንፋክቸሪንግ ዲፖርትመነት የአከባቢን ብክለት ችግር መነሻ ተደርጎ የተሰራ መሆኑንና ቴክኖሎጂውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሁለት ዓመት ጊዜ መዉሰዱን ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂው ሲሰራ አካል ጉዳተኞችን እና ሴቶችን ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን እንዲሁም የሚሰሩ ማንኛዉም ስራዎች ከእጅ ንኪኪ ነጻ መሆኑን ከምክትል ዲኗ ገለጻ ለመረዳት ችለናል።
የዉበት ሀዋሳ ኢንተርፕራይዝ ማናጀር አቶ አልታየ የቦ በቀላሉ ሊበሰብስ የማይችል ሀይላንድዶችን የመፍጨት የማጠብ ስራዎችን የሚሰራ ቴክኖሎጂ በመሆኑ ይህንን ቴክኖሎጂ በአግባብ በመጠቀም የማህበራቸዉን የዉስጥ ገቢያቸዉን ለማሳደግ ትልቅ አበርክቶ እንዳለዉ ተናግረዋል።
11/04/2026
****** የኮሌጃችን ማህበረስብ በሙሉ*********
እንኳን ለጌታችንና ለመዲኃንታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! በዓሉን ስናከብር አቅም ያጡና አዛውንቶችን በማስታወስ፤ ጌታችን የእኛ በደል ይቅር ለማለት በመስቀል እርቃኑን ተሰቅሎ ፍቅርንና ይቅርታን እንዳስተማረን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር በመባባል በፍቅሩ ተዋደን አንድ ሆነን ማክበር ይኖርብናል።
በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና እንዲሆንልን እምኛለው።
*****ሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ********
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ(ገና) በዓል በሰላም
አደረሳችሁ/አደረሰን!!
🌲🌲🌲🌲ታህሳስ 28/2018 ዓ/ም🌲🌲🌲🌲
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ(ገና) በዓል በሰላም
አደረሳችሁ/አደረሰን: በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣የብልጽግና፣የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆን የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መልካሙ በራሳ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፏል!!!!
🌲🌲🌲🌲🌲ታህሳስ/2018 ዓ/ም🌲🌲🌲🌲
🌲🌲🌲🌲🌲ሀዋሳ ፓሊ ቴክንክ ኮሌጅ🌲🌲🌲
Category
Contact the university
Telephone
Website
Address
Hawassa
Awassa