Debre Tabor Communication

Debre Tabor  Communication

Share

this page is create to address honest information for society

Photos from Amhara Communications's post 04/09/2026
04/09/2026

ጳጉሜን እንደ መስፈንጠሪያ!!

አገራችን ኢትዮጵያ ባለብዙ ሰውሰራሽና ተፈጥሮዊ ሀብቶች ባለቤት ስትሆን በሌሎች አገሮች የማይገኙ ለየት ያሉ መገለጫዎች ያሏትም ናት፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉት የዓለም አገራት አንዱን ዓመት በ12 ወራቶች ከፋፍለው የሚቆጥሩና የሚጠቀሙ ናቸው፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ግን ጳጉሜን 13ኛ ወር አድርጋ የምትቆጥር ሲሆን ይህም ከሌሎች አገራት ለየት የሚያደርጋት በመሆኑ የ13 ወር ፀጋ ያላት አገር እየተባለችም ትጠራለች፡፡ በመሆኑም የጳጉሜ ወር የነባሩ አመት መገባደጃ እና የአዲሱ አመት መጀመሪያ ድልድይ ሁና ታገለግላለች፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በባለፉት አመታት የጳጉሜ ወርን እንደ መስፈንጠሪያ ለመጠቀም የጳጉሜ ቀናትን በተለያዩ መሪ ሀሳቦች እና በተለያዩ ዝግጅቶች እንዲከበሩ በማድረግ ለተሻለ ለውጥና ውጤት ህዝቡ ላይ መነሳሳትን እና ንቅናቄን ለመፍጠር ጥረት አድርጓል፡፡

በተመሳሳይም የ2018 ዓ/ም የጳጉሜ ወር “የኢትዮጵያ መንሰራራት” በሚል መሪ መልእክት የሚከበር ሲሆን የየእለቱ ቀናት ደግሞ የራሳቸው መሪ ሀሳብ ይዘው የአገሪቱን ህዝብ አንድነት ከፍ በሚያደርጉ እና ወደ ጥሩ ለውጥና መነሳሳት በሚወስዱ ክንዋኔዎች ይከበራሉ፡፡

በመሆኑም ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን፣ ጳጉሜ 2 የመንሰራራት ቀን፣ ጳጉሜ 3 የጽናት ቀን፣ ጳጉሜ 4 የኅብር ቀን፣ ጳጉሜ 5 የነገ ቀን በሚሉ መሪ ሀሳቦች ከቀናቶቹ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የሚከበሩ ይሆናል፡፡

በደብረታቦር ከተማ አስተዳደርም የጳጉሜ ወር ቀናቶች በሚመለከታቸው ተቋማት አዘጋጅነት በተለያዩ ሁነቶች ይከበራሉ፡፡

ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ነሀሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

Photos from Debre Tabor  Communication's post 03/09/2026

በማህበረሰቡ ተሣትፎና ባለቤትነት የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ይረጋገጣል ሲሉ የአብክመ ጤና ቢሮ ሃላፊ አብዱልከሪም መንግስቱ ተናገሩ!
‎
‎የአብክመ ጤና ቢሮ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሀድ፣ የጤና አጠባበቅ ትምህርትና ጤና ማበልፀግ፣ እንዲሁም የሀይጅንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ኬዚቲሞችና የጤና መሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ‎በጋራ በመሆን በባህርዳር ከተማ ለ2 ቀናት ሲያካሂዱ የነበረው የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2019 በጀት አመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ ።
‎
‎ቢሮው በዛሬ ውሎው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የዳይሬክቶሬቶቹን ወረዳን መሠረት ያደረገ የ2019 በጀት አመት አንኳር ዕቅድ ገምግሞ አጽድቋል።
‎
‎ የአብክመ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ዛሬ ገምግመን ያፀደቅነው ዕቅድ የህብረተሰቡን ጤና ለማሰጠበቅ መሰረታዊ የሆነ ተግባር የሚከናወንበት ነው ብለው ይሄንን በአግባቡና በትኩረት መምራት ካልተቻለ ውጤታማ መሆን እንደማይታሰብ ጠቁመዋል።
‎
‎በተጨማሪም ፕሮግራሙ የወደፊት የትውልድ ዕጣ ፈንታ የሚወሰንበት ነው ያሉት ሀላፊው በግልም ሆነ በማህበረሰብ ደረጃ የአካባቢውንና የግሉን ንጽህና ጠብቆ የሚኖር ዜጋን መፍጠር የእኛ ድርሻ ነው ብለዋል።

‎ ቀጣይ ተጠናክረው መቀጠል ባለባቸው ተግባራት ላይም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
‎
‎በህዝብ ንቅናቄ መስራት ፣ የጤና ተቋማትን በመስፈርቱ መሠረት ጽዱ ማድረግ ፣ ዲጅታላይዜሽንን ማጠናከር ፣ የተጀመረውን ጤናን መሰረት ያደረገ አገልግሎት ጥራት እውን ማድረግ ፣ የጤና ተቋማትን ማስተሳስር ፣ አሰራርን በማዘመን ከይስሙላ አሰራር ወጥተን እስከ ቀበሌ መስራት፣ የህክምና ቁሳቁስ አሟልቶ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት ይገባል በማለት ከብዙ በጥቅቱ ገልፀዋል።
‎
ሀላፊው ‎አክለውም የአገልግሎት እርካታ የሚያመጣ ቅሬታ የማይፈጥር ውጤት ተኮር ስራ ሰርተን የህዝብ ግንኙነትና በአከባቢያችን ያሉ ሚዲያዎችን በአግባቡ በመጠቀም ለቀጣይ በአዲስ ሀሳብ ፣ ዕቅድ ፣ ትግበራ እና ስኬት መገናኘት እንደሚገባ አሳስበዋል።
‎
‎ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፍ አስተባባሪ አቶ ገስጥ ጥላሁን በተጠናቀቀው በጀት አመት በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ያሉ ሲሆን ሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች አንድ ላይ መገምገማቸው መሬት ላይ ያለውን ነገር በአግባቡ ለማየት ጠቅሞናል ብለዋል።
‎
‎አክለውም በእስታንዳርዱ መሠረት ማህበረሰቡን ያሳተፈ ተቋም ግንባታ ፣ ትምህርት ቤቶችን ማዘመን ፣ በጀትን ለታለመለት አላማ ማዋል ፣ የጤና ትምህርት ተግባቦት ላይ መስራት ፣ የግልና የአከባቢ ንጽህና ላይ ቤት ተኮር የሆነ ቆጠራ በማካሄድ የተሰራባቸውን መለየት ፣ መሠረተ ልማት ላይ የተጀመሩትን 222 (ሁለት መቶ ሀያ ሁለት) የጤና ተቋማት አጠናቀን ሌላ መጠየቅ ይገባናል በማለት ስለ ዘርፍ ዘርዘር ያለ ሀሳብ ሰጠዋል።
‎
‎በቢሮው የማህበረሰብ ተሳትፎና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሜነህ ልየው በበኩላቸው በችግር ውስጥም ሁኖ ውጤታማ የሆነ አመራርና ባለሙያ መኖሩን አድንቀው ቀጣይ ባለው ተነፃፃሪ ሰላም ከዚህ የተሻለ ውጤት ማምጣት ይቻላል ብለዋል።
‎
‎በተጨማሪም በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩ በተጠናቀቀው በጀት አመት በዘርፉ የተሻለ ለፈጸሙ ዞን ጤና መምሪያዎችና ከተማ አስተዳሮች የእውቅና ዋንጫ ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ገስጥ እጅ ተበርክቶላቸዋል።
‎
‎በመሆኑም ዞን ጤና መምሪያ
‎1ኛ- ሰሜን ጎጃም ዞን
‎2ኛ - ምስራቅ ጎጃም ዞን
‎3ኛ - ደቡብ ወሎ‎

ከተማ አስተዳደሮች
‎1ኛ- ደሴ ከተማ
‎2ኛ - ደብረታቦር ከተማ
‎3ኛ - ደብረ ብርሀን ከተማ የዕውቅናው ባለቤት ሆነዋል።
‎
መረጃው የአብክመ ጤና ቢሮ ነው።
‎
‎

Photos from Debre Tabor  Communication's post 03/09/2026

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 100 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹን፣ የአስተዳደር ሰራተኛውንና መምህራንን በማስተባበር እና ከተቋሙ በጀት በድምሩ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የትምህርት ቁሳቁስ እና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ ከአስተዳደር ሰራተኞችና ከመምህራንን በተገኘ 49 ሽህ 700 ብር እንዲሁም ከተቋሙ በጀት 1 ሚሊየን 092 ሽህ 580 ብር በጥቅሉ 1 ሚሊየን 142 ሽህ 280 ብር ወጭ የተደረገበት የተሟላ ትምህርት ቁሳቁስ እና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ለተማሪዎቹ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በድጋፉ ላይ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶክተር ሀብቱ ወርቁ እንደተናገሩት ዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር፣ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አንስተው ከ2004 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዩ በጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ እየተሳተፈ መሆኑን እና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በዚህ ክረምት ወቅትም የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የተሳተፈባቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቅሰው በዛሬው እለትም ለበርካታ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ እና ለሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ መደረጉን ጠቁመው ድጋፉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ሀሳብ ሳይኖርባቸው ትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ መሆኑን ተናግረው ተማሪዎችም ትምህርታቸውን በአግባቡ በመማር ራሳቸውን እና ማህበረሰባቸውን ሊጠቅሙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ እና የከንቲባው ተወካይ ኮማንደር አብራራው አበጀ እንዳሉት የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰቡን በተለያየ መንገድ እያገዘ መሆኑን ተናግረው አሁን ደግሞ ለነገ አገር ተረካቢ ተማሪዎች ያደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችም ትምህርታቸው ላይ ጀግና በመሆን አገር ተረካቢ ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበው ዩኒቨርሲቲው እያበረከተ ላለው ትልቅ አስተዋጽኦ እና ለተማሪዎች ላደረገው የተሟላ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ እየበሩ አእምሮ በበኩላቸው የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ አግባብ እገዛ እያደረገ መሆኑን አንስተው በትምህርት ዘርፉ ላይ ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ እና በአገራዊ ፈተናው ላይ ጥሩ ውጤት እንዲመጣ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀዋል፡፡

አሁን ደግሞ ለተማሪዎች ያደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን ተናግረው ዩኒቨርሲቲው እያበረከተ ላለው ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ እና ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ተማሪዎች ጠንክረው እንዲማሩ እና ስነ-ምግባር ያላቸው እንዲሆኑም መክረዋል፡፡

የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችም በሰጡት ሀሳብ ወላጆቻቸው የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት የአቅም ውስንነት እንዳለባቸው ተናግረው ዩኒቨርሲቲው ያደረገላቸው ድጋፍ ካለ ምንም ችግር ትምህርታቸውን ለመማር እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል፡፡

ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ነሀሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም

Photos from Debre Tabor  Communication's post 03/09/2026

"የስፖርት ዘርፉን በባህላዊ አሠራር ብቻ መምራት አይቻልም" አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)

የስፖርት ዘርፉን ከዚህ በፊት በነበረው ባህላዊ አስተሳሰብና አሠራር ብቻ መምራት የሚቻልበት ወቅት አለመሆኑን የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር አብዱ ሁሴን ገለጹ።

ዶ/ር አብዱ ሁሴን ይህን የገለጹት 27ኛው የአማራ ክልል ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ ሲካሄድ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ስፖርት ከጤናና ከዜጎች መሠረታዊ መብት ባሻገር ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መፍትሔ የሚያበረክት ዘርፍ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይም ወጣቶችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በየደረጃው ዘመናዊ አሠራር መዘርጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የክልሉን ስፖርተኞችና አሠልጣኞች ከስፖርቱ የሚገኘውን ዘመናዊ ጥቅም እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር፣ የክልሉን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለኢትዮጵያ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ማሳደግ ከስፖርት አመራሩ የሚጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም መንግሥት ለስፖርቱ ዘርፍ ልዩ ትኩረት እየሰጠ መሆኑን ጠቁመው፣ የስፖርት ልማትና አስተዳደር አዋጅ መጽደቅ፣ የስፖርት ፖሊሲ በአዲስ መልክ መዘጋጀትና የስፖርት መሠረተ ልማቶች መገንባት ለዘርፉ እድገት የሚያበረክቱ ተግባራት መሆናቸውን አንስተዋል።

በጉባኤው የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም፣ የ2019 ዓ.ም ዕቅድና የማስፈጸሚያ በጀት እንዲሁም የ2018 ዓ.ም የኦዲት ሪፖርት በጥልቀት እንደሚገመገም ተገልጿል።

Website

Address


Debre Tabor

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Tabor Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Debre Tabor.