Horn Insight
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Horn Insight, News & Media Website, Hawassa.
12/09/2026
ጠበቃ ሙሉጌታ በላይ እና ጠበቃ ሰብለ አሰፋ በቅን ልቦች የሽልማት መርሃ ግብር በአላማ መር ማህበራዊ ሚዲያ ይዘት አቅራቢዎች ዘርፍ እጩ ሆነው ቀረቡ።
ባለሙያዎቹ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ውስብስብ የህግ ጉዳዮችን ለህዝብ ቀለል ባለ መንገድ በማስረዳት፣ ህብረተሰቡ መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ በማድረግ እና ፍትህ ተከባሪ እንድትሆን በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ይህ የሽልማት ዘርፍ ሀገራዊ እሴትን ጠብቀው ማህበረሰብን የሚጠቅሙ ይዘቶችን ለሚያቀርቡ አካላት የሚሰጥ ሲሆን፣ ለከፍተኛ አሸናፊዎች እንደየደረጃቸው በአጠቃላይ የ100 ግራም ወርቅ ሽልማት ተዘጋጅቷል። በዚህም መሠረት ለ1ኛ ደረጃ 50 ግራም፣ ለ2ኛ ደረጃ 30 ግራም፣ እንዲሁም ለ3ኛ ደረጃ 20 ግራም ወርቅ ይበረከታል።
የህግ እውቀትን በማስፋፋት አዲስ ትውልድ በመቅረጽ ላይ የሚገኙትን እነዚህን ባለሙያዎች ለማበረታታት ህዝቡ በተዘጋጀው የድምፅ መስጫ ሊንክ በኩል ድምፅ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።
12/09/2026
በፍኖተ ሰላም በ80 ሺህ ብር በተገዛ በሬ ውስጥ 13.7 ግራም ወርቅ ተገኘ!
በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ 03 ቀበሌ ለአዲስ ዓመት በዓል ማጠቃለያ በተደረገ የከብት እርድ ወቅት፡ በበሬው ሆድ ውስጥ የወርቅ ቁራጭ መገኘቱ ተገለጸ።
አቶ አንዱአምላክ , አቶ ውለታው እና አቶ በፍትህ ከተባሉ አባላት ጋር በመሆን ለበዓል በ80,000 ብር የተገዛው በሬ ታርዶ በውስጡ የተገኘው ወርቅ በመጀመሪያው የወርቅ ሚዛን የመዘኑት ሰዎች 14 ግራም መሆኑን የገለጹ ሲሆን፡ ለሁለተኛ ጊዜ በሌላ ወርቅ ቤት ሲመዘን ደግሞ 13.7 ግራም ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ ያልተጠበቀ ክስተት በከተማው ነዋሪዎችና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ እና ትኩረት ሳቢ አጋጣሚ ሆኗል።
ሲዳማ ቡና ለአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለጸ
በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ኢትዮጵያን ወክሎ እየተሳተፈ የሚገኘው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ፣ ከቻዱ ተጋጣሚው ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ የመልስ ጨዋታ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ያደረገውን ዝግጅት በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ።
ክለቡ በሜዳው ውጭ በነበረው የመጀመሪያ ጨዋታ ከቻዱ ተጋጣሚው ጋር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ከተለያየ በኋላ፣ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ በድሬዳዋ ስታዲየም ጠንካራ የልምምድ ጊዜያትን አሳልፏል። የቡድኑ ተጫዋቾችና አመራሮች እንደገለጹት፣ ቡድኑ ለአሁኑ የመልስ ጨዋታ በቂና በጥሩ የአካል እንዲሁም የስነ-ልቦና ዝግጁነት ላይ ይገኛል።
የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች ይህ ጨዋታ የክለብ ውድድር ብቻ ሳይሆን መላዋን ሀገር የመወከል ትልቅ አደራ እንዳለበት በመግለጽ፣ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍና የሀገራቸውን ስም የሚያስጠራ ውጤት ለማስመዝገብ በሙሉ ቁርጠኝነት እንደሚጫወቱ አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም፣ እሁድ በሚካሄደው በዚህ ወሳኝ ጨዋታ የድሬዳዋና የአካባቢው እግር ኳስ አፍቃሪዎች በስታዲየም በአካል ተገኝተው ለቡድኑ አስፈላጊውን የሞራል ድጋፍ እንዲሰጡ ክለቡ ጥሪውን አስተላልፏል።
12/09/2026
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ በሲዳሙ አፎ ስርጭት በአስቸኳይ እንዲጀምር ጥሪ ቀረበ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 97.7 የሚገኝበትን የአካባቢውን ህዝብ ቋንቋ የሆነውን ሲዳሙ አፎ በስርጭት ፕሮግራሞቹ ውስጥ አካቶ አለመጠቀሙ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩን ጋዜጠኛ ተፈራ ቀንፋቶ አስታወቀ።
ጋዜጠኛው ባወጣው የሂስ ጽሁፍ እንደገለጸው፣ ጣቢያው በሲዳማ ክልል እምብርት ሀዋሳ ከተማ ውስጥ እየሰራ የአካባቢውን ቋንቋ ዘንግቶ መቆየቱ ትልቅ የሙያ እና የማህበረሰብ ተደራሽነት ክፍተት ያለበት መሆኑን አመልክቷል። የማህበረሰብ ሬዲዮ ከተቋቋመበት ዋነኛ አላማ አንዱ የአካባቢውን ህዝብ ባህል፣ ታሪክ እና ቋንቋ መሰረት በማድረግ መረጃ መስጠት ቢሆንም፣ ኤፍ ኤም 97.7 ይህንን መሰረታዊ የመገናኛ ብዙሃን መርህ መጣሱንም አክሎ ገልዟል።
ይህ አሰራር ማህበረሰቡ በሬዲዮ ጣቢያው ላይ ያለው የባለቤትነት ስሜት እንዲቀንስ እና መረጃ የማግኘት መብቱ እንዲገደብ ማድረጉ ተጠቅሷል።
በመሆኑም፡
💫የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና የጣቢያው አስተዳዳሪዎች፡ አሰራራቸውን በአስቸኳይ በመገምገም በሲዳሙ አፎ የሚሰጡ ስርጭቶችን እንዲጀምሩ፤
💫የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የኮሙኒኬሽን አካላት፡ ህዝቡ በቋንቋው የመጠቀም መብቱ እንዲከበር አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲያስደርጉ፤
ጋዜጠኛ ተፈራ ቀንፋቶ ጥሪውን አስተላልፏል።
በተጨማሪም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቋሙን የሚመሩ አንዳንድ አካላት በአካባቢው ማህበረሰብ ምሁራን፣ አመራሮች እና ኤክስፐርቶች ላይ ያነጣጠረ መድልዎ እና ጥቃት እያደረሱ ነው ተብሎ ቅሬታዎች እየተነሱ መቆየታቸው ይታወሳል።
12/09/2026
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ቀይ መስመሮች ማስመራቸውን ገለጹ
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደል አቲ አገራቸው በኢትዮጵያ አቋም ላይ ሦስት ዋና ዋና ቀይ መስመሮች ማስመሯን መናገራቸውን ዘ አረብ ዊክሊ ዘገበ።
ሚኒስትሩ አገራቸው የኢትዮጵያን የመልማት መብት የምታከብር ቢሆንም፣ የግብፅ የውሃ ደህንነት ግን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ሊከበር እንደሚገባ እና በወንዙ ላይ የሚደረጉ የተናጠል እርምጃዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ ካስቀመጧቸው ቀይ መስመሮች መካከል የመጀመሪያው የአባይ ወንዝ ቁጥጥርን የሚመለከት ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በወንዙ ላይ አዳዲስ ግድቦችን በመገንባት የበላይነት ለመያዝ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ግብፅ የማትቀበለው መሆኑን አስረድተዋል። ሁለተኛው ደግሞ ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ባሻገር የግድቦች ኔትወርክ ለመዘርጋት የምታደርገው ጥረት በረጅም ጊዜ ውስጥ የወንዙን ፍሰት ሊቀንሰው ወይም ሊያዛባው ስለሚችል፣ በአባይ ወንዝ አስተዳደር ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች በግልጽ እና አስገዳጅ ህግ ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው ብለዋል።
በሦስተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቀይ መስመር የኢትዮጵያን የባህር በር የመፈለግ እንቅስቃሴ የሚመለከት ነው። እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፣ ግብፅ ኢትዮጵያ ለንግድ አገልግሎት ወደቦችን በመጠቀሟ ላይ ተቃውሞ የሌላት ቢሆንም፣ በቀይ ባህር አካባቢ የባህር ሃይል ለማስፈር የምታደርገው ጥረት ከኢኮኖሚ ባለፈ ወታደራዊ አላማ ያለው ነው የሚል ስጋት አላት። የቀይ ባህር እና የሱዌዝ ካናል ደህንነት ለግብፅ ብሄራዊ ደህንነት ወሳኝ በመሆናቸው፣ በቀጣናው ላይ ሌላ ወታደራዊ ሃይል እንዲሰፍር አገራቸው የማትፈልግ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
የአባይ ወንዝ ዋና ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ በወንዙ ላይ የመልማት መብቷ ለዘመናት በቆዩ የኮሎኒያል ዘመን አድሏዊ ስምምነቶች ታስሮ ከቆየ በኋላ፣ አሁን ላይ የተፈጥሮ ሀብቷን በፍትሃዊ እና ሚዛናዊ መንገድ ለመጠቀም እና ለማልማት በተግባር መተግበር የጀመረች ሲሆን፣ ለግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስተያየትና ለቀረቡት ቀይ መስመሮች የምትሰጠው ይፋዊ ምላሽ ይጠበቃል።
11/09/2026
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ160 የልማት ተነሽ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ዕጣ አወጣ
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በቱላ ክፍለ ከተማ ልዩ መንደር ጨፌ ቀበሌ ለኮሪደር ልማት ሥራ ተነሽ ለሆኑ 160 ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት የመኖሪያ ቤት ዕጣ ማውጣት መርሃ ግብር አካሂዷል።
በአስተዳደሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ እንደገለጹት፤ ከተማ አስተዳደሩ ለዘጠኝ ወራት የቤት ኪራይ ድጎማ ሲያደርግላቸው ለቆዩት የመጀመሪያ ዙር የልማት ተነሽዎች ውሃና መብራት የተሟላላቸው ዘመናዊ ቤቶች ተገንብተው የዕጣ ርክክብ ተደርጎላቸዋል። ቤቶቹ በመንግሥት መመሪያ መሠረት በተመጣጣኝ ኪራይ የሚተዳደሩ ሲሆን፣ በቀጣይ አንድ ሳምንት ውስጥ ሙሉ በሙሉ አልቀው እንደሚረከቡ አስታውቀዋል።
ዕጣ ያወጡ ነዋሪዎች በበኩላቸው አሰራሩ ፍትሐዊ መሆኑን ጠቅሰው ባገኙት ዕድል መደሰታቸውን ገልጸዋል።
11/09/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በነገው ዕለት በሕንድ ይወያያሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በነገው ዕለት በሕንድ ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመካከሩ ታውቋል።
የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ስብሰባ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ዘመናት የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
11/09/2026
ሰበር ባብ ኤል-መንደብ ከባድ ስጋት ላይ ወደቀ
የየመን ሐውቲዎች አስደናቂ በሆነ ፍጥነት የተለያዩ የሀገሪቱን ስትራቴጂካዊ ቦታዎች በቁጥጥራቸው ስር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ሃይሎቹ ዓለም አቀፍ የባህር ንግድ መስመር የሆነውን የባብ ኤል-መንደብ (Bab-el-Mandeb) ወሰን ለመዝጋት በጥቂት ርቀት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተለይም ዛሬ አዳሩን በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥንካሬ ወደ ፊት በመግፋት ላይ መሆናቸው የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ሐውቲዎች ይፋ እያደረጉት ባለው ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) መሠረት፤ በርካታ የየመን የመንግስት ሰራዊት አባላት እጃቸውን እየሰጡ መሆናቸው ታይቷል።
ይህ በከፍተኛ ፍጥነት እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት እና ስጋት በእጅጉን ስቧል።
10/09/2026
የድሮን ትርኢት በአዲስአበባ
የባሕር በር ቁርጥ ነው!
10/09/2026
ሀዋሳ ድሮና ዘንድሮ
“ድሮ በበዓላት ወቅት አቅመ-ደካማ የከተማው ነዋሪ የሚያገኘው ድጋፍ ከጎመን አልፎ አይታሰብም ነበር፤ ዘንድሮ ግን ታሪክ ተቀይሯል! የሀዋሳ ነዋሪዎች በበግ ሙከት፣ በምግብ ዘይትና በትላልቅ ቁሳቁሶች ድጋፍ የሚደረግላቸው ሆነዋል።
ለዚህ ትልቅ ለውጥና መልካም አስተዳደር ለሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እና ለብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ ምስጋና ይግባልን።
የሀዋሳ ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፤ እንኳን ሕዝቡን የሚመጥንና የሚበጅ እውነተኛ መሪ አገኛችሁ!”
የዘወትር ተከታያችን፦ ህሩት ፀጋዬ
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hawassa