Guulit.com

Guulit.com

Share

It is a virtual open market like "guulit gebeya"

10/09/2023
Photos from Ethio Sugar ኢትዮ ስኳር's post 27/10/2021
Home 23/07/2019

የኮሚሽን ስራ ዕድል ለ1000 ተመራቂዎች

Home Ethio Sugar Manufacturing Industry Share Company is a company emerging at the right time of the country's all-rounded transition. It is working to bring about technologies, finance, employment opportunity, public ownership and many more at the heart of Wonji_Shoa and of course, to the surrounding ar...

16/07/2019

ገንዘቤን ምን ላይ ባውል ጠቀም ያለ ገንዘብ አገኛለው ብለው አስበው ያውቃሉ?

በየዓመቱ ኢንቨስት ያደረጉትን 30 በመቶ በላይ ትርፍ ለመካፈል ይፈልጋሉ?

የግዙፍ ፋብሪካ ባለቤት ለመሆን ይሻሉ?

መልስዎ አዎ ከሆነ መፍትሄው
አሁኑኑ የኢትዮ ስኳር አባል ይሁኑ!!

እንዴት?
ለሚለው ከትንሹን የአክሲዮን ብዛት 10አክሲዮን ጀምሮ አክስዮን ይገዛሉ ከዚያ እንደዕርሶ ደግሞ ሌሎች ሲገዙ…. ኢትዮጵያውያን በጋራ በመሆን የግዙፉ ስኳር ፋብሪካ ባለቤት መሆን ይችላሉ፡፡ በተዋጣው ገንዘብ ፋብሪካው ይገዛልም ይሻሻልበታል፡፡ ስለዚህ ጊዜው ሳይረፍድ አክሲዮኑን ይግዙ፡፡ 1 አክሲዮን=1,000.00ብር ፡፡ ለበለጠ መረጃ ገፃችንን ውድድ (Like) (Share) በማድረግ ይከታተሉ፡፡ 0915666666/0952080808/0116160001/0116160002
አክስዮኑም በአዋሽ፣በንብና በኦሮምያ ህብረት ስራ ባንኮች በሁሉም ቅርንጫፎቻቸው ይገኛል፡፡

12/07/2019

…………..
- የአገሪቱን ሰፊ ህብረተሰብ የቢዝነስ ባለቤት ማድረግ ፣
- የኢንዱስትሪ ሰላምን ማረጋገጥ ፣
- የኢንዱስትሪ ባህልን በማስፋፋት የወንጂና መተሀራ ዙሪያ አካባቢ የኢንዱስትሪ መናኸሪያ (Industrial Hub) እንዲሆን ማድረግ እና
- በአጠቃላይ በአግሮ ኢንደስትሪው በተለይም በስኳር እና ተዛማጅ የስኳር ስራዎች በክፍለ አህጉሩ የልህቀት ማዕከል መሆን ነው፡፡.............

ስለኢትዮ ስኳር የተዘጋጀ አንኳር ማስታወሻ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

ራዕይ
,,,,,,,,,,,,
በ2030 በስኳር ቴክኖሎጂና ምርት በአፍሪካ ቀንድ ተጠቃሽ ሆኖ የወንጂ ሸዋ እና መተሃራ ስኳር ፋብሪካ አካባቢን የኢንዱስትሪ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ማየት ነው፡፡
ግብ
,,,,,,,
ቀዩን ዝሆን ከነዘመኑ የኢንዱስትሪ ባህል ክብሩ እንዲመለስ ማረጋገጥ ነው፡፡
ተልዕኮ
,,,,,,,,,,,
የአካባቢውን ህዝብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በቢዝነስና ማህበራዊ ሀላፊነት መፍታት ነው፡፡ የወንጂ ሸዋና መተሃራ ስኳር ፋብሪካን ሠራተኞች አርሶ አደሮችና የአካባቢውን ነጋዴዎች እና ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የአክስዮን ባለቤት ማድረግ ነው፡፡ ኤች ቪ ኤ የወንጂ እና መተሃራ እናት ኩባንያ ጋር የዕውቀት ፣ የቴክኖሎጂ እና የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የጋራ መግባቢ ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ታሪክ የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ልህቀት ማዕከል ማድረግና ወደ ቀድሞ ዝናው በመመለስ እንደዝሆን ጠንካራ የሀገር ኩራትነትን መፍጠር፡፡ በፓራ(ተጓዳኝ) ስኳር ስራዎችም የኢንዱስትሪው መሪ ሆኖ መገኘት ነው፡፡
አጠቃላይ ዳራ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
የኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ አክሲዮን ማህበር የስኳር ቴክኖሎጂ እውቀትና ከፍተኛ የዘርፉ አመራር ልምድም ባላቸው የኢንደስትሪው ተቆርቋሪዎች የተቋቋመ ሲሆን ራዕዩ የወንጂ ሸዋ እና መተሀራ ስኳር ፋብሪካና አካባቢው እ.አ.አ በ2030 በምስራቅ አፍሪካ በአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በስኳር ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል ሆኖ ማየት ነው፡፡
የላቀ የኢንዱስትሪ ባህል የዳበረበትን የቀዩን ዝሆን (Bringing the Red Elephant Back) ምርጥ ዘመን የበለጠ አሻሽሎ መልሶ ማምጣት ነው ተልዕኮው፡ ህዝብን ያቀፈ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት የሚያስችል ክንውን በማካሄድ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የህብረተሰብ ኑሮ እንዲሻሻል ማድረግ ነው፡፡
የኢትዮ ስኳር ወቅታዊ እድገት መግለጫ ዋነኛ ነጥብ
- ኢትዮ ስኳር በአሁኑ ወቅት የአክሲዮን ሽያጩን ለመቀላቀል መነሻውን አንዱ አክሲዮን 1000 ብር ሆኖ አንድ ሰው መግዛት ያለበት ዝቅተኛው ወለል መጠን 10 አክሲዮኖች ወይም 10 ሺህ ብር እና 8 በመቶ የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ 10ሺህ 800 ብር ይሆናል፡፡ ክፍያውም በ2ዙር የሚጠናቀቅ ሆኖ ከሰኔ 1 / 2011 አንስቶ የታለመው የአክሲዮን መጠን 60 በመቶ ተከፍሎ እስከ መጪው ህዳር 2012 ድረስ ደግሞ ቀሪው 40 በመቶ ተከፍሎ ሊጠናቀቅ ይገባል፡፡
- ከመስከረም 2012 መጀመሪያ አንስቶ ግን አንድ ሰው መግዛት የሚኖርበት ዝቅተኛው ወለል ከ10 ሺህ ብር ጀምሮ አክሲዮን መግዛት እንደሚችልና ክፍያውም መቶ በመቶ በአንዴ መጠናቀቅ እንደሚኖርበትና የአገልግሎት ክፍያውም ከ8 በመቶ ወደ15 በመቶ ከፍ እንደሚል ከወዲሁ ይገለጻል፡፡
- ኩባንያችን አሁን አበረታች ሁኔታ ላይ ሲደርስ የሚከተሉት ጉዳዮች አብረው ትኩረት እንዲያገኙ ማሳሰብ ይሻል፡-
1 - በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ወደግል ይዞታ ከሚያዞራቸው የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች መካከል የፍላጎት መግለጫ ንድፈ ሀሳብ ሰነድ ካስገቡት 10 ኩባንያዎች መካከል አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ሲሆኑ ኢትዮ ስኳር ወንጂና መተሀራ ስኳር ፋብሪካን ለመግዛት ፍላጎት ያሳየ ብቸኛው የሀገር ውስጥ ኩባንያ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከመንግስት በተገኘ ይፋ የመረጃ ምንጭ መሰረት ከብዙ በጥቂቱ ኬንያ ፣ ሞርሸስ ፣ ሞሮኮ ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ ውሱን የአረብ ሀገራትም ይገኙበታል፡፡
2 - የኢፌዲሪ መንግስት የመንግስት ይዞታዎች የሆኑ የስኳር ኢንዱስትሪና ፕሮጀክቶችን ወደግል በማዘዋወር ሂደት ለሀገር ውስጥ አቅም የኢኮኖሚ ማስቻያ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት አኳያ (consider to include as a policy direction input as part of due process for privatization to facilitate an opportunity for local community economic empowerment) ልዩ የማበረታቻ እድሎችን መስጠት እንደ ፖሊሲ አቅጣጫ እንዲታይ ኩባንያችን ያሳስባል፡፡ ኢትዮ ስኳር የህብረተሰብን የኢኮኖሚ አቅም የሚያበቃ የቢዝነስ ሞዴልን መከተሉ ይዞታዎቹ ለውጭ ኩባንያዎች ቢሸጡ የተገኘችው ትርፍ ሁሉ የውጭ ምንዛሪ ከሀገር ቤት ኮብልሎ እንዲወጣ (Foreign currency repatriation) የሚያደርግበትን ሁኔታ ሊያስቀር ይችላል፡፡
3 - በአሁኑ ወቅት ይህ ሂደት ከ6 ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደግል ይዞታ እንደሚሸጋገር ዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ዘንድ እየተገለጸ መሆኑን ተከትሎ ኩባንያችን በተለይም በስኳር ኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ልምድ ያዳበሩ ሙያተኞችን ለመመልመል እና አብረውም ለመስራት ፍላጎት ያላቸውን ሙያተኞች አቅም በተመለከተ ዳታቤዝ ለማደራጀት ስለተፈለገ እውቀቱና ዝግጅቱ ያላቸው በየቦታው የተበተኑ እውቀትን ከልምድ ያዳበሩ ሙያተኞች አብረው ለመስራት እንዲያመለክቱ ኩባንያችን ይጋብዛል፡፡
4 - ኢትዮ ስኳር አሁንም ቢሆን በአጋርነት አብሮ ለመስራት የአውሮፓውያኑን ጨምሮ በተለያ ደረጃ ከተለያዩ የውጪ ኩባንያዎች ጋር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ላይ እየደረሰ ነው፡፡
5 - ኢትዮ ስኳር እየተከተለው ባለው የቢዝነስ ሞዴል እና በፕራይቬታይዜሽን ሂደቱ የሀገር ውስጥ ኩባንያ እንዲበረታታ ስለሚደረግባቸው አማራጮች ከየሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት አካላት ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ ጉዳዩ ሊታይ እንደሚገባ አበረታች ምላሾችም ተገኝተዋል፡፡

መሰረታዊ የኩባንያው ዳራ
- ወደግል ከሚዛወሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች መካከል የታለመውን የወንጂና መተሀራ ስኳር ፋብሪካን በመግዛት የፋብሪካዎቹ ሰራተኞች ፣ የዙሪያ ገባው አርሶ አደሮች ፣ በምስራቅ ሸዋ እና አርሲ ዞኖች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ ማዕዘናት እና በውጭም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በዘርፉ መሳተፍ የሚፈልጉ ነጋዴና ባለሀብቶች በሙሉ በባለቤትነት የሚታቀፉበት ይሆናል፡፡
- በስኳር አመራረት ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከልነቱን ማረጋገጥ እና በስኳር ተዛማጅ ምርቶች ኢንዱስትሪም ቀዳሚ ሚና መጫወት ከትልሞቹ አንዱ ነው፡፡ የልህቀት ማዕከልነትን የሚያጠናክር የስኳር ቴክኖሎጂ ኮሌጅን በመመስረት ለአያሌ አመታት በምርምር ጭምር ተደግፎ የተከማቸውን የስኳር ቴክኖሎጂ እውቀትን እና ክህሎትን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ጭምር ማስፋፋትም ከተቋቋመባቸው ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳል፡፡
- በአለም ገበያ አመታዊ የስኳር ፍጆታ መጠን እስከ 59 ሚሊዮን ቶን ወይም 590 ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ ሲሆን - ዘርፉ በአመት እስከ 29 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚሸፍን ነው፡፡ በአለም ገበያ ተወዳድሮ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ደግሞ በዝቅተኛ ወጪ ማምረት ይጠበቃል - ለአለም ገበያ ዋና የስኳር ላኪዎች ብራዚል ፣ ህንድ እና ታይላንድ ናቸው፡፡ ስኳርን ወደሀገር ውስጥ በማስገባት ድርሻ ረገድ ኢሲያ 35.4 % ፣ አፍሪካ 18.8% ፣ መካከለኛ ምስራቅ 16% እና አውሮፓ ደግሞ 15 % ይደርሳል ወደሀገር ውስጥ የሚያስገቡት የድርሻ መጠን፡፡ የአለም የስኳር ገበያ መጠን በየአመቱ ጭማሪው 2.3 በመቶ ይደርሳል፡፡
የኢንዱስትሪው አጠቃላይ ሁኔታ
- በቅርቡ ከተለያዩ ጥናታዊ መረጃዎች ተሰባስቦ በተጠናቀረው መሰረት እ.አ.አ ከ2019 - 2025 ባሉት ቀጣይ 10 አመታት ውስጥ አመታዊ የሀገር ውስጥ የስኳር ፍጆታ ትንበያ መሰረት አሁን ካለው የ9 ሚሊዮን ኩንታል ወደ 17 ሚሊዮን እንደሚያድግ ይገመታል፡፡
- በኢትዮጵያ የኢታኖል ፍላጎትም ከ53 ሚሊዮን ሊትር ወደ 226 ሚሊዮን 534 ሺህ ሊትር ከፍ እንደሚል የተመሳከረው መረጃ ያመለክታል፡፡
- በተለይ የስኳሩ ምርት በፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለው ክፍተት የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር የመጥበብ መስፋት ካልሆነ በቀር እስከ መጪው 12 አመት እ.አ.አ. 2035 ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችል የተለያዩ ጥናቶችን በመዳሰስ የተደረገ የሰነድ ቅኝት ያመለክታል፡፡
- እ.አ.አ በ2019 ከ927 ሺህ ቶን በላይ የሆነው የስኳር ሀገራዊ አመታዊ ፍላጎት ከ108 ሚሊዮን በላይ ከሆነው ህዝብ ቁጥር አንጻር ሲታይ የአንድ ሰው አማካይ የነፍስ ወከፍ አመታዊ ፍጆታ 8.5 ኪሎ ግራም ሲሆን በተመሳሳ ሁኔታ የማሌዢያ የነፍስ ወከፍ አመታዊ ፍጆታ 56 ኪሎ ግራም እንዲሁም የእነ ኬንያ 21 ኪሎ ግራም ገደማ ነው፡፡ እ.አ.አ. በ2035 ላይ የህዝብ ቁጥሩ ከ144 ሚሊዮን በላይ ይደርስና አመታዊ ሀገራዊ ምርቱም ወደ 3 ሚሊዮን ቶን ከፍ ይልና የኢትዮጵያ አማካይ አመታዊ የነፍስ ወከፍ የስኳር ፍጆታ ከ21 ኪሎ ግራም እንደማይሻገር ጥናታዊ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
- ኢትዮ ስኳር ወደፊት ከ60 - 63 በመቶ የሚሆነውን የሸንኮራ ተክል ማሳን ማልማት እንደሚችል እና እስከ 160 ቶን ስኳር በሄክታር በማምረት በአመት እስከ 1.4 ሚሊዮን ቶን የሚደርስ የሚፈጭ ሸንኮራን በማዘጋጀት አመታዊ የስኳር ምርትን በእጥፍ እጥፍ አሳድጎ እስከ 172 ሺህ ቶን ስኳር በአመት ማምረት እንደሚችል ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡
- ኢትዮ ስኳር እንዳለመው መንግስት ፋብሪካዎቹን ወደግል ይዞታ የማዘዋወሩ ሂደት ቢጠናቀቅም ከዚህ የኢንደስትሪ ፕሮጀክት ስራ አፈጻጸም የተሻሻለ ሙሉ አቅም ላይ ለመድረስ ከ4 - 5 አመት እንደሚፈጅበት ያካሄደው ጥናት ይጠቅሳል፡፡
- ኢትዮ ስኳር ወደፊት በምርት እና አገልግሎት ሊሰማራባቸው ካቀዳቸው መካከል፡-
- የስኳር
- የሞላሰስ እና የኃይል ማመንጨት
- ጣፋጮች (ደስታ ከረሜላ)
- ከቤንዚን የሚቀላቀለው የኢታኖል ፣ የአልኮል ፣ የሽቶ
- የወረቀት እና ችፑድ ቦርድ
- ኖራ እና ከሰል
- የእርሻ ፣ የፍራፍሬ ፣ የአሳ ፣ የእርሾ ፣ የወተት ሀብትና ከብት እርባታ ፣ የእንስሳት መኖ
- እንዲሁም በስኳር ቴክኖሎጂ ማማከር እና የአግሮ ኢንዱስትሪ ቱሪዝምን ይጨምራል
ስለኢትዮ ስኳር ሽርክና እና አክሲዮን አሻሻጥ ሁኔታ
- ኢትዮ ስኳር ለሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመሸጥ ያወጣው አጠቃላይ የአክሲዮን መጠን 3 ሚሊዮን ሆኖ ኩባንያው ለመሰብሰብ ያሰበው አጠቃላይ መጠን በብር 3 ቢሊዮን ሆኖ ቀሪው በውጭ ሀገራት በአውሮፓ ከሚገኝ እውቅ የስኳር ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከኤች.ቪ.ኤ ሆላንድ እና መሰል አጋሮች ጋር ቴክኖሎጂን በማሸጋገርና ለፋብሪካው ግዢም የውጭ ምንዛሪን ለማምጣት ከጋራ መግባቢያ ላይ በመድረስ አብሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
- የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1000 ብር ሆኖ አንድ ሰው በጥቂቱ መግዛት ያለበት 10 ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ግዢ ጣራ ደግሞ 50 ሚሊዮን ነው፡፡
- ከሶስት ባንኮች ጋር በረዥም ጊዜ የሚከፈልበት ስርአት በማመቻቸት በምስራቅ ሸዋ እና በአርሲ ዞኖች የሚገኝ ከ40 ሺህ የማያንስ ህብረተሰብን የኩባንያ ባለቤት የሚያደርግ ፕሮጀክት ነው፡፡ ተጨማሪ 20ሺህ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አካቶ አጠቃላይ 60 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የግዙፉ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ባለቤቶች ይሆኑበታል፡፡
- ብዙዎችን የኩባንያ ባለቤት ከማድረግ አኳያ ቀደም ሲል የአክሲዮን አከፋፈል ሁኔታው በሶስት ዙር ሆኖ - በመጀመሪያ 25% ፣ በሁለተኛው ዙር 35% ሆኖ የመጨረሻው ሶስተኛው ክፍያ እስከ ህዳር 2012 ድረስ 40% ተጠናቆ እንዲከፈል ሁኔታዎች ተመቻችተው እጅግ በርካታ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለፉት 5 ወራት አክሲዮኑን ተቀላቅለዋል፡፡ አሁን ግን ክፍያው በ3 ዙር መሆኑ ቀርቶ በ2 ጊዜ ክፍያ ሆኖ የ25 በመቶው ክፍያ ጊዜ አብቅቶ ከላይ በተገለጸው የ60 በመቶና እና የ40 በመቶ ከነተጨማሪ የ8 በመቶ የአገልግሎት ክፍያው እንዲፈጸም ይጠበቃል፡፡
- ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ አክሲዮን ማህበር አርሶ አደር ፣ ሰርቶ አደሩን ፣ ነጋዴ እና ባለሀብቱን ጨምሮ መላ የህብረተሰቡን ክፍሎች አካቶ እስከ 60 ሺህ የሚደርስ የሀገር ቤትን ባለራዕዮች አቅፎ ፣ የአውሮፓ እውቅ የስኳር ቴክኖሎጂ ባለቤት ከሆነው ኤች.ቪ.ኤ ሆላንድ ጋር አብሮ ለመስራት ተስማምቶ ፣ እንደ አዋሽ - ንብ እና ኦሮሚያ ህብረት ስራ ካሉ ባንኮች ጋር የአጋርነት መግባቢያ በመፈራረሙ ፕሮጀክቱ የህብረተሰብ መሰረቱን ከውጭ ምንዛሪ ግኝት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጋር ሁሉን አጣጥሞ የያዘ ኢኮኖሚን ከማህበራዊ ጠቀሜታ ያዋደደ ለብዙሀን ተስፋ የሚሆን አቃፊ ሆኖ የቀጠለ ጥረት በመሆኑ ለሀገረ ኢትዮጵያም አብነት የሆነ ቢዝነስ ሞዴል መሆኑን ሳይጠቅስ አያልፍም፡፡
የኢትዮ - ስኳር ትኩረት ከኢትዮጵያ መንግስት አቅጣጫ
- የኢፌዴሪ መንግስት በክቡር ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የመጀመሪያ ንግግር ወቅት ከተጠቀሰበት ጊዜ አንስቶ በቅርቡም በፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፉ በኩል የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደግል ይዞታ ለማዞር ከተወሰነባቸው መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም በአንደኛው ወገን በሌላ በኩል ደግሞ የወንጂ ሸዋ እና መተሀራ ስኳር ፋብሪካዎችን ጨምሮ 13ቱ የስኳር ፕሮጀክቶች እንደሚገኙበት መጠቀሱ ይታወሳል፡፡
- በዚሁ መሰረት ኢትዮ ስኳር ማኑፋክቸሪንግ ኢንደስትሪ አክሲዮን ማህበር ከተቋቋመበት አንድ አመት ገደማ አንስቶ ትኩረቱን በወንጂና መተሀራ ስኳር ፋብሪካዎች ላይ በማድረግ ወደግል ከሚዞሩት ውስጥ የተጠቀሱትን ፋብሪካዎች ለመግዛት የ140 አመታት የስኳር ቴክኖሎጂ የካበተ ልምድ ካለውና በመንግስት ከመወረሱ በፊት ቀድሞም የእነኚሁ ፋብሪካዎች ባለቤት ከነበረው የአውሮፓው ኤች.ቪ.ኤ. ሆላንድ ጋር አብሮ ለመስራት የጋራ መግባቢያ ባለፈው ጥቅምት 2011 ተፈራርሞ ሂደቱን በትብብር የቀጠለበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡
- ኢትዮ - ስኳር በስትራቴጂክ ትኩረቱ የሚከተሉትን ያሳካል
- የሚገዛውን ፋብሪካ በተደረገው ጥናት መሰረት ከሸንኮራ ተክሉ እስከ መፍጫ ማሽኖች ቴክኒካዊ አቅማቸውን በማሻሻልና በማዘመን እጅግ ትርፋማ ማድረግ ፣
- የስኳር ምርትን እጅግ በጣም ከፍ በማድረግ ከውጭ የሚገባ የስኳር መጠንን በመቀነስ ሀገሪቱ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ ማዳን ፣
- የስኳር ኢንዱስትሪ የፋብሪካዎች እናት የመባሉን ያህል ከስኳር ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን በማስፋፋት ለወጣቶች እጅግ ሰፊ የስራ እድሎችን መፍጠር ፣
- የዙሪያውን ሰፊ ህብረተሰብ የቢዝነስ ባለቤት ማድረግ ፣
- የኢንዱስትሪ ሰላምን ማረጋገጥ ፣
- የኢንዱስትሪ ባህልን በማስፋፋት የወንጂና መተሀራ ዙሪያ አካባቢ የኢንዱስትሪ መናኸሪያ (Industrial Hub) እንዲሆን ማድረግ እና
- በአጠቃላይ በአግሮ ኢንደስትሪው በተለይም በስኳር እና ተዛማጅ የስኳር ስራዎች በክፍለ አህጉሩ የልህቀት ማዕከል መሆን ነው፡፡

12/07/2017

Dear All here is a Great opportunity to start online Business. So use this page to post your product. It is FREEEEE.

Photos from Guulit.com's post 08/04/2017

New products arrived for price inbox me

Category

Address


Hawassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guulit.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Hawassa.