Sky First
ይህ ገጽ ለታማኝ ዜናዎች እና ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ለመሆን የተዘጋጀ ነው።
https://t.me/SkyFirstMedia YouTube.com/@skyfirst-sf
09/14/2026
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ባቀረቡ ቅሬታ መሰረት በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ ተወሰነ።
ትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በክልሉ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር በሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩና በአሁኑ ወቅት በክልሉ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው ለቅሬታቸው መፍትሔ ለመጠየቅ በትምህርት ሚኒስቴር ግቢ ከተገኙ ተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት፣ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ደህንነታቸው ወደሚጠበቅባቸው ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ገልጸዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም፣ ወጣቶች በአሁኑ ወቅት ማተኮር ያለባቸው በትምህርታቸው ላይ በመሆኑና ወደፊት ሀገራቸውን የሚረከቡ ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል።
ሀገር ማጽናት የሚቻለው የዛሬው ትውልድ ለነገው ትውልድ ማሰብ ሲጀምር ነው ያሉት ሚኒስትሩ ጦርነትና ግጭትን በመሸሽ ከትግራይ ክልል የወጡ ተማሪዎች በሰላም የመኖርና የመማር መብት ያላቸው መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም እነዚህን የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች በተለያየ መንገድ ማስተናገድና ትምህርታቸውን ያለመስተጓጎል እንዲቀጥሉ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
በዚህም ተማሪዎች ለምዝገባ በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባቸው ከዛሬ ማታ ጀምሮ ይፋ በሚደረገው የበየነ መረብ (Online) መተግበሪያ በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።
በምዝገባው ወቅትም ተማሪዎች ከዚህ በፊት ይማሩበት የነበረውን ዩኒቨርስቲ፣ የትምህርት ዘመናቸውን እና የሚማሩበትን የትምህርት መርሐ ግብር (field of study) በመግለጽ ባሉበት ቦታ ሆነው የዝውውር ፎርሙን በአጭር ግዜ እንዲሞሉ አሳስበዋል።
ዛሬ በአካል በትምህርት ሚኒስቴር ግቢ የተገኙት በርካታ ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን ክቡር ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወትን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ለተጨማሪ መረጃ እና መመዝገቢያ ሊንክ ሲለቀቅ ለመከታተል የቴሌግራም https://t.me/SkyFirstMedia/605 ገፃችን ይከታተሉ
09/14/2026
የአዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት ነገ በይፋ ይጀምራል
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ነገ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በይፋ እንደሚጀምር የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ትምህርት ቤቶች የመማር–ማስተማር ሂደቱን በወጣው ካሌንደር መሠረት ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻቸውን ማጠናቀቃቸውን ሚኒስቴሩ ገልጿል። በዚህም መሠረት ወላጆችና አሳዳጊዎች ለልጆቻቸው አስፈላጊውን የትምህርት ግብዓት በማሟላት ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ መልዕክት ተ አስተላልፏል።
ትምህርት ሚኒስቴር ለአዲሱ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ በማለት ለመላው ተማሪዎች፣ መምህራን እና ወላጆች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ተመኝቷል።
Via ትምህርት ሚኒስቴር
"የ6 ሰከንድ ሪከርዱን ብሰብረው ደስ ይለኛል"- ቢኒያም ሽብሬ
09/14/2026
ሪያድ ከሁቲዎች ጋር ባለው ግጭት የጠበበ አማራጭ ውስጥ ገብታለች ተባለ
በኢራን የሚደገፉት የሁቲ አማፂያን በየመን ያሳዩት ፈጣን የጦር ግስጋሴ እና በሳዑዲ ዓረቢያ መሠረተ ልማቶች ላይ ያሰነዘሩት ጥቃት፣ የገልፍ አረብ ኤምሬትስ ግዛቷን ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍሉ ጠባብ የውሳኔ አማራጮች ውስጥ እንደከተታት ተገለጠ።
ሪያድ ከወታደራዊ ባለሙያዎች ዘንድ የከረረ ውጊያ ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌላት የሚጠቁሙ መልእክቶች ቢወጡም፣ የሁቲዎች እያደገ የመጣው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ግን ቀጠናውን ወደ ሰፊ ውጊያ ሊጎትተው እንደሚችል ይገመታል።
በየመን እና በዋሽንግተን ዲሲ የአደጋ ስጋት አማካሪ የሆኑት ሞሃመድ አል-ባሻ ለሲኤንኤን እንደገለጹት፣ አሁን ያሉ የፓለቲካ እና ወታደራዊ ሁነቶች ወደ ከፍተኛ የሳዑዲ የአየር ምላሽ ያመላክታሉ። አክለውም «በዚህ ደረጃ ሳዑዲዎች የተወሰነ አማራጭ ነው ያላቸው» ብለዋል።
በዚህ ሳምንት አማፂያኑ በቀይ ባሕር አፌፍ ላይ የምትገኘውን ስትራቴጂካዊዋን ፔሪም ደሴት እና የሞካን የወደብ ከተማ በመቆጣጠር የባቢ አል-መንደብን የኃይል ማጓጓዣ መስመር ስጋት ላይ ጥለዋል። ተከታታይ በሆነ ክስተትም የሳዑዲ ዓረቢያ ዋና የምስራቅ-ምዕራብ የነዳጅ ቧንቧ መስመር ከኢራቅ በተቃጡ ድሮኖች ጥቃት ደርሶበት ተዘጋጅቷል። ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወገን ባይኖርም፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ተኪ ኃይሎችን ተጠያቂ አድርገዋል።
የቀጠናው የወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት፣ በወረቀት ላይ ዘመናዊ ጦር ያላት ሀብታሟ ሳዑዲ ዓረቢያ እና በድሃዋ የመን የሚገኘው አማፂ ቡድን ግጭት የማይመጣጠን ቢመስልም፣ ሁቲዎች ግን በቀላሉ የማይበገሩ ሆነው ተገኝተዋል። የሁቲዎች ተወካይ ናስር አል-ዲን አሜር በበኩላቸው በሳዑዲ ላይ የሚደረገው ጫና ሀገሪቱ የጣለችውን የ12 ዓመታት እገዳ እስከምታነሳ ድረስ እንደሚቀጥል በመግለጽ የውጥረት ማባባስ ፍላጎታቸውን አረጋግጠዋል።
የምዕራብ ሀገራት ተመራማሪዋ ሲንዚያ ቢያንኮ እንደሚያስረዱት፣ ሳዑዲ ዓረቢያ «በሙሉ ኃይሏ» ወደ ጦርነት ብትገባ አጠቃላይ ቀጠናውን አደጋ ውስጥ የሚከት እና የሰብዓዊ ቀውስ የሚያባብስ ይሆናል። በተጨማሪም አሜሪካ በሀገር ውስጥ ፖለቲካ እና በሆርሙዝ ቀውስ ምክንያት ቀጥተኛ ወታደራዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆነች ተጠቅሷል።
የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጊዜው ሉአላዊነቴን የማስከበር መብቴ እንደተጠበቀ ሆኖ ዲፕሎማሲያዊ ትዕግሥትን መርጫለሁ ቢልም፣ የጂኦፖለቲካ ተንታኞች ግን የፖለቲካ መፍትሔዎች መሟጠጣቸውን እና በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሰዓታት የጦርነቱ አቅጣጫ ሊቀየር እንደሚችል ይጠቁማሉ።
09/14/2026
የ2019 የትምህርት ዘመን ሲጀመር የትምህርት ጥራትና የነገዋ ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ
የ2019 ዓ.ም አዲስ የትምህርት ዘመን በዛሬው ዕለት በመላው ሀገሪቱ በይፋ ተጀምሯል። አዲሱ ዓመት የተማሪዎችንና የወላጆችን ስሜት ከማነቃቃቱም በላይ፣ የሀገራችንን የትምህርት ጥራት እና የወደፊት የትውልድ እጣ ፈንታ በድጋሚ እንድንፈትሽ ትልቅ እድል ይፈጥራል።
በቅርብ ዓመታት የነበሩ የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤቶች እንደሚጠቁሙት፣ የተማሪዎች አቀባበልና የውጤት ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ይፈልጋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመሰረታዊ ንባብ፣ ጽሑፍና ሒሳብ ብቃትን ማጠናከር ቀዳሚው ተግባር ነው። በተጨማሪም የመምህራን የሙያ ማሻሻያና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣ የተሟሉ ቤተ-ሙከራዎችና ቤተ-መጻሕፍት፣ እንዲሁም የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅርቦት ለስኬቱ ወሳኝ ድርሻ አላቸው።
ከትምህርት ሚኒስቴር እስከ ትምህርት ቤት ባለው መዋቅር ውስጥ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር መዘርጋትም ሌላው አስፈላጊ ጉዳይ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ እና የሪሚዲያል ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ ለማየት የቴሌግራም ገፃችን https://t.me/SkyFirstMedia/604 ይጎብኙ
09/14/2026
የመቄዶንያ በጎ አድራጐት ማህበር ወጣቱ ባለሀብት ምህረትአብ ሙሉጌታ 8.5 ሚሊየን ብር ለማህበሩ መለገሱን አስታወቀ።
ባለሃብቱ የዘመን መለወጫን በማስመልከት ትናንት በመቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር ዋናው ማዕከል ተገኝቶ አዲስ አበባ እና 57 ቅርንጫፍ ለሚረዱ 9,000 አቅመ ደካማ ወገኖች የምሳ ማብላት መርሃ ግብር ማካሄዱን ማህበሩ ገልጿል።
ለዚህ የምሳ ማብላት መርሃ ግብር 4.5 ሚሊየን ብር የመደበው አቶ ምህረትአብ፣ በተጨማሪም 4 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ በአጠቃላይ 8.5 ሚሊየን ብር ለመቄዶንያ አበርክቷል ተብሏል።
አቶ ምህረትአብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን ተቋም ማገዝና መደገፍ እንደሚገባው ጠቁሟል።
የመቄዶንያ መስራች ዶ/ር ብንያም በለጠ በበኩላቸው ምህረትአብ ሙሉጌታ ሁሌም የማዕከሉ ደጋፊ መሆኑን ገልፀዋል።
09/14/2026
አዲስ መረጃ፡ የ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል መርሃ-ግብር የዩኒቨርሲቲ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
የትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብን በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም እና በሀገራዊ ፍትሃዊነት መርህ ላይ በመመስረት ይፋ አድርጓል።
⨳ መደበኛ የመቁረጫ ነጥብ
በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ወንድ ተማሪዎች ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%) እንዲሁም ሴት ተማሪዎች ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%) ያመጡ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።
⨳ በልዩ ድጋፍ የሚታዩ የተማሪዎች ምድብ
ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈተኑ ተማሪዎች እንዲሁም ከአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
በተጨማሪም በስነ-ልቦና እና አካል ጉዳት ምድብ በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውራን ተማሪዎች ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%) እንዲሁም መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) ካስመዘገቡ ብቁ ይሆናሉ።
ለተጨማሪ መረጃ እና ሙሉ ዝርዝሩን የቴሌግራም ገፃችን https://t.me/SkyFirstMedia/602 ላይ ታገኛላችሁ
09/14/2026
የሁቲዎች ወደ ባብ አል-መንደብ ግስጋሴ እና የዓለም አቀፉ ስጋት
የሁቲዎች ወደ ስትራቴጂካዊው የባብ አል-መንደብ ግስጋሴ ዓለም አቀፍ ስጋት ፈጠረ። በየመን የተቀሰቀሰው ግጭት አዲስ መልክ መያዙን ተከትሎ፣ አማፅያኑ ወደ አደገኛው የባህር ወሰን የሚያደርጉትን ፈጣን ግስጋሴ ማፋጠናቸው በቀጠናው እና በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ አዲስ የስጋት ደወል ደውሏል።
በሁቲዎች እና በየመን መንግሥት ኃይሎች መካከል የቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ-ሰላጤ ማገናኛ የሆነውን ወሳኝ የባህር መስመር ለመቆጣጠር በተደረገው ውጊያ በሁለቱም ወገኖች በኩል ከፍተኛ የከባድ መሣሪያዎች ድብደባ ተካሂዷል።
ዓለም አቀፍ የነዳጅ እና የንግድ መርከቦች ዋነኛ ማለፊያ በሆነው በዚህ ቀጠና የሁቲዎች አዲስ ግስጋሴ በባህር ንግድ ደህንነት ላይ ደቅነዋል የተባለውን አደጋ ተከትሎ፣ ሳውዲ ዓረቢያ በሁቲዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ትብብር ለማድረግ ጥያቄ ማቅረቧ ተሰምቷል።
የኢንዲያ ቱዴይ ዘገባ እንደሚያመላክተው የቀጠናው እና የዓለም አቀፍ ኃይሎች ሁኔታውን በከፍተኛ ትኩረት እየተከታተሉት የሚገኙ ሲሆን፣ ውጥረቱ ወደ የከፋ ቀውስ እንዳያመልጥም ማስጠንቀቂያ በመስጠት ላይ ናቸው።
09/13/2026
“በኢትዮጵያ የሕክምና ትምህርት ጥራትና የመንግሥት ሠራተኞች ምልመላ ጉልህ ክፍተት አለ” የዓለም ባንክ
የዓለም ባንክ "የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸምና ብልፅግና" በሚል ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ በሕክምና ትምህርት ጥራት፣ በመንግሥት ሠራተኞች ቅጥርና በተቋማት ቁጥጥር ዘርፍ ያሉ ጉልህ ክፍተቶችን ይፋ አድርጓል።
በሀገሪቱ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑ የሕክምና ተማሪዎች በሚያገኙት ሥልጠና እርካታ እንደሌላቸው የገለጹ ሲሆን፣ ለዚህም ዋነኛው ምክንያት መንግሥት የሕክምና ተማሪዎች ቅበላን ከሶስት እስከ አራት እጥፍ እንዲያሳድግ ማድረጉ ከተቋማቱ አቅም በላይ መሆኑ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ፣ የብሔራዊ የሙያ ብቃት ማረጋገጫና ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓቱ ከተግባር ልምድ ይልቅ ለንድፈ ሐሳብ ትኩረት የሚሰጥና የቴክኖሎጂ አቅም የሚያንሰው በመሆኑ፣ ተመራቂዎች ለሥራው በቂ ዝግጅት ሳይኖራቸው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ እያደረገ እንደሆነ ሪፖርቱ ያመላክታል።
በሌላ በኩል ሪፖርቱ የመንግሥት ሠራተኞች የሚቀጠሩበትን መንገድ የዳሰሰ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ወደ 30 በመቶ የሚጠጉ የመንግሥት ሠራተኞች ክፍት በሆነ የውድድር ሒደት ሳያልፉ መቀጠራቸውን አሳይቷል። ይህም ሀገሪቱን ከአርሜኒያና ኡራጓይ ጋር ተመሳሳይ ተመጣጣኝ ደረጃ ላይ ያመጣታል።
አያይዞም 29 በመቶ የሚሆኑ የተቋማት አስተዳደር ኃላፊዎች በጤናና በትምህርት ተቋማት ላይ የሚያደርጉት ቁጥጥርና ክትትል በዓመት ከሁለት ጊዜ እንደማያልፍ በመጠቆም፣ የምልመላ ሒደቶች በግልጽነትና በውድድር ላይ እንዲመሠረቱ እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓቱ እንዲጠናከር አሳስቧል።
09/13/2026
🔥 ለአካል ግንባታ (Gym) አፍቃሪዎች በልዩ ማስተዋወቂያ (Promotion) የተዘጋጀ የታላላቅ ብራንዶች ቅናሽ! 🔥
ሰውነትን በፍጥነት ለመገንባት፣ የጡንቻ መጠንን (Mass) ለመጨመር እና የኃይል አቅምን (Strength) በከፍተኛ ሁኔታ ለማሻሻል የሚረዱ ምርጥ ፕሪሚየም ፕሮቲኖች እና ክሬቲኖች በልዩ ዋጋ አቅርበናል! አሁኑኑ በመጠቀም ውጤትዎን ይቀይሩ።
1. Mass Gainers (ለክብደት እና ለጡንቻ እድገት)
USN Hyperbolic Mass
1 ኪ.ግ — 4,000 ብር
2 ኪ.ግ — 6,500 ብር
4 ኪ.ግ — 12,000 ብር
✨ ዋና ጥቅሞች: ከፍተኛ የካሎሪ፣ የፕሮቲን እና የሚኖ አሲድ ይዘት ያለው ሲሆን፣ ቀጭን አካል ያላቸው ሰዎች በፍጥነት ጤናማ ክብደት እንዲጨምሩ እና ጡንቻዎቻቸው እንዲፋፉ ያደርጋል። ከከባድ ስፖርት በኋላ ፈጣን ማገገም (Recovery) ይሰጣል።
Mutant Mass
2.3 ኪ.ግ — 10,000 ብር
ዋና ጥቅሞች: በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዙፍ የጡንቻ መጠንን ለመገንባት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኘ። በውስጡ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ካርቦሃይድሬቶችና ፕሮቲኖች በመያዝ የኃይልና የመጠን ዕድገት ያፋጥናል።
2. Creatine Monohydrate (ለጉልበት እና ለጥንካሬ)
Gold Creatine Monohydrate (300g) — 3,700 ብር
Applied Nutrition Creatine (250g) — 3,700 ብር
Creatine (400g) — 5,500 ብር
ዋና ጥቅሞች: በጡንቻዎ ውስጥ የኃይል ማመንጨት አቅም (ATP) እንዲጨምር በማድረግ በስፖርት ሰዓት ተጨማሪ ክብደት ማንሳት እንዲችሉ አቅም ይሰጣል። ጡንቻ ውኃ እንዲይዝ በማድረግ የተሟላና የጠነከረ ቅርጽ እንዲኖረው እንዲሁም ጡንቻን እድገት ከፈተኛ አሰተዋፀኦ ያደርጋል።
ይዘዙን ያሉበት እንልካለን።
📞 ለማዘዝ ብቻ በስልክ ቁጥር +251911277521 ይደዉሉ።
ወይም በTelgram
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Website
Address
US
Atlanta, GA
404