Blue Board

Blue Board

Share

Blue Board is an Ai service platform, where every workflow is automated. We transform complex, manual processes in to streamlined, self-running systems.

08/13/2026

የባንክ CEO የተሾመው 35 ሚሊዮን ብር፥ ጉቦ ከፍሎ ነው" የሚል አሉባልታ ክስ እየተዘዋወረ ነውና፥ ማጣሪያ እንዳደርግላችሁ፥ አንባቢያን በውስጥ ጠይቃችሁኛል።

ጉዳዩ ለብሉ ቦርድ የማይመጥን ቢሆንም፥ ከአንባቢያን ለቀረበ ጥያቄ፥ መመለስ ተገቢ ስለሆነ፥ትክክለኛ ያልነውን መረጃና ሃሳብ እናጋራችሁ።

1) ሲጀመር አንድ የተጣራ የወር ደመወዝ 300,000 ብር የሚከፈለው የባንክ ስራ አስፈፃሚ፥ የወደፊቱን የአስር አመት ደመወዙን( እስከ 2029 ዓም ሊቀበለው የሚችለውን 35 ሚሊዮን ብር) አስቀድሞ ጉቦ ከፍሎ... መሾም የሚፈልግበት ምክንያት...፥ በየትኛውም የሂሳብ ቀመር፥ ተገቢ ውሳኔ ሊሆን አይችም፤ አንጎሉ ምንም ያክል የማሰላሰል ውስንነት ያለበት፥ ከሳሽ ያቅርበው....፥ የውንጀላው እሳቤ በራሱ....በዕውነትም ሆነ፥ በሃሰት አለም የሌለ ምዕናባዊ ቅዠት ስለሚመስል፥ ችሎቱ አያስተናግደውም።

2) የአሉባልታ ክሱን ያቀረቡት "አክቲቪስቶች"፥ የፋይናንስ ጉዳይ ይቅርና፥ የሳንቲሞችን አይነትና መጠን፥ መለዬት የሚችል ግንዛቤ እንዳላቸው አናምንም። ከዘርፉ ጋር አይተዋወቁም።

3) "አክቲቪስቶቹ" በከፍተኛ የፋይናንስ ባለሙያ፥ በጥብቅ ዳሬክቲቭ እና የንግድ ህግ/ፖሊሲ የሚመራውን ብሄራዊ ባንክ ጨምረው ለመወንጀል ሲደክሙ ማየቱ በራሱ፥ አንጀት የሚበላ አሳዛኝ አመል የሚመስል፥ ግን ብርቱ የስነ-ልቦና በሽታ የተጠናወታቸው ሊሆኑ ይችላሉ እንጅ፥ ህግ እንደተጣሰ የሚያሳይ፥... የህግ አንቀፅ/ዳሬክቲቭ ተጠቅሶ፥ የቀረበ ማስረጃ የለም።

4) የCEO ምርጫ ሂደቱን በተመለከተ፥
...በቦርዱ በፀደቁ የኮርፖሬት ገቨርናንስ መመሪያዎች፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተፈጻሚ በሆኑ መመሪያዎችና መስፈርቶች መሠረት ብሎም በተቋሙ የውስጥ አሠራር ስርዓቶች መሠረት ደረጃ በደረጃ እንደተከናወነ፥ አማራ ባንክ በመግለጫ ማሳወቁን እናስታውሳለን። ሂደቱ በብቃት፣ በሙያዊ ብስለት፣ በተገቢ ምዘና እና የአመራር ብቃትን መሰረት ባደረጉ መስፈርቶች ላይ የተመሰረተ እንደነበር፣ በየደረጃው የተሰጡ ውሳኔዎችም በህጋዊና ተቋማዊ ሂደት እንዳስመረጣቸው፥ በዝርዝር አቅርቧል።

5) ይህ አሉባለተኛ ቡድን፥ በርካታ ሙሁራንን ተገቢ ባልሆነ መልኩ፥ ስም በማጥፋት የሚታወቅ እንደሆነ፥ በርካቶች ይናገራሉ። ለአብነት ያክል፥ ዶር ዩኋንስ አያሌው CEO ሆነው ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት፥ ባቀረቡባቸው ተመሳሳይ ክስ፥ በምሬት ለቀው ወደ ፀደይ ባንክ እንደተዛወሩ እናስታውሳለን።
ዶር ዩኋንስ በብሄራዊ ባንክ፥ ንግድ ባንክ እና ልማት ባንክን በከፍተኛ ሃላፊነት ሲመሩ የቆዩ ፋይናንስ ኤክስፐርት ናቸው።

6) አማራ ባንክ፥ ስራ ከጀመረ አምስት አመት ውስጥ፥ ከአራት በላይ ዋና ስራ አስፈፃሚ (CEO) ቀያይሯል፤
ለዚህም የ CEO ፍልሰት እንደ ዋና ምክንያት ሆኖ ሲጠቀስ የቆየው፥ በአካባቢ/ጎጥ እና ጥቅም የተሳሰሩ፥ በሙስና የተጨማለቁ ፥ አቅመ ቢስ የውስጥ ክፍል ሃላፊዎች እና ጥቂት የቦርድ አባላት.. ከውጭ አክቲቪስቶች ጋር በመቀናጀት፥ በርካታ ጫናዎችን ሲፈጥሩ በመቆየታቸው ነው። በቦርድና በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ የሚገኙ አክቲንግ መኮንኖች፥ ከጅምሩም በዕቅድ፥ ለሴራ ተልዕኮ የተቀመጡ ስለሆነ፥ ዝርዝሩን በማህበራዊ ሚዲያ ከመበተን፥ ጉዳዩን በጥንቃቄ ይዘን መቆየትን መርጠናል። አስፈላጊ በሆነ ጊዜ፥ መፍትሄ ላይ ያተኮረ መረጃ እናቀርባለን።

"35 ሚሊዮን እጅ መንሻ ተከፍሏል"፥ የተባለው ተራ የስም ማጥፋት፥ ሃሰት አሉባልታ ነው!

ለአዲሱ ስራ አስፈፃሚ፥ የስኬት አመት እንዲሆን ምኞታችን ነው።

08/11/2026

በመጨረሻም ሹመታቸው ፀድቆ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾመዋል።

አማራ ባንክ አቶ ይህንዓለም አቅናውን በዋና ስራ አስፈፃሚነት ሹመት በዛሬው እለት በይፋ አፅድቋል።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዝርዝር መስፈርቶችን በጥልቀት በማጤን፣ በትምህርት ዝግጅታቻው፣ በባንክ ኢንዱስትሪው ያላቸውን ልምድ፣ የአመራር ብቃት፥የብሄራዊ ባንክ እና የንግድ ህጉ በሚፈቅደው መስፈርት መሠረት፥ አቶ ይህንአለም አቅናው ብቁ ሆነው በመገኘታቸው፥ የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ መርጧል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክም ሹመታቸውን በዛሬው ዕለት አጽድቋል። ሹመቱን አማራ ባንክ በኦፊሺያል ገፁ አሳውቋል።

ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ያለው የዋና ስራ አስፈፃሚ ሹመት ተፈፃሚ መሆን፤ ከነባሮቹ የአማራ ባንክ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ባንኩን ወደ ቀጣዩ ዕድገት ለማሻገር ከፍተኛ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ይታመናል።

በቅርቡ፥ አማራ ባንክ የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ፣ ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ሰራተኞች በማሳደግ እና ክፍተት የነበረባቸውን የስራ መደቦች በመሙላት፥ መልካም እንቅስቃሴ ማድረጉ፥ አወንታዊ መነቃቃት የፈጠረ መሆኑን ሰምተናል።

የብሉ ቦርድ አባላት፥ በአማራ ባንክ ባለአክሲዮኖች ስም ለአቶ ይህንዓለም አቅናው፥ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛሉ።

07/26/2026

የአማራ ባንክ ሰራተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ! !

የአማራ ባንክ ሰራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ከሃምሌ 2026 ጀምሮ ጭማሪ አድርጓል። የባንኩ አስተዳደር በሰራተኛ ጉዳይ ጥልቅ ጥናት አድርጎ፥ ተገቢው የዕርከን ጭማሪና ጉርሻ(Bonus) ጥቅማ ጥቅም ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑን መረጃዎች ደርሰውናል።

የባንኩ አስተዳደር ይህን ውሳኔ ማስተላለፉ፣ የሰራተኞችን፥ ማህበራዊ ግንኙነት፥ የስነልቦና እና የኢኮኖሚ ጫና በሚገባ እንደተረዳ፤ የሰራተኛ መነቃቃት የሚያመጣውን የአገልግሎት ጥራትና ምርታማነት፤ ባለ ድርሻ አካላት ለባንኩ የሚኖራቸውን በጎ አመለካከትና የሚፈጥረውን መልካም ገፅታ ... ቀድሞ የተረዳ መሆኑን ያሳያል። ይህ ዕርምጃ ከአንድ ጠንካራ ስራ አስፈፃሚ አካል የሚጠበቅ ነው። Bravo!

በአንድ ድርጅት ውስጥ፥ ንቁ እና ትኩስ የስራ ፍላጎት ያለው ደስተኛ ሰራተኛ እንደማየት የሚያስደስት ነገር የለም።

የአማራ ባንክ፥ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የወሰዳችሁት የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ጭማሪ፥ትክክለኛ ውሳኔ በትክክለኛ ጊዜ ነው። ይህ ታሪካዊ ውሳኔ፥ በትንሹ፥ የሚከተሉትን አዎንታዊ ውጤቶች እንደሚያስመዘግብ እምነት አለን።

1) በገበያ ላይ የሚታዬውን የዋጋ ንረት ተከትሎ በሰራተኛው ላይ የደረሰውን የኑሮ ውድነት ጫና ዕፎይታ ይሰጣል፤

2) በተገቢው ጊዜ የሚፈፀሙ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅሞች፥ በሰራተኛው ላይ የስራ መነቃቃት ይፈጥራል፤ ጤናማ የስራ ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል...፤ የተነቃቃ ሰራተኛ፥ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት፥ ችግሮችን ለመፍታትና ደንበኞችን ለማስደሰት የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው። ለዚህም ነው ዘመናዊው የባንክ አገልግሎት መርህ፦
"A highly motivated banker does not just process transactions; they actively build client relationships, speed up problem-solving, and eliminate operational friction." የሚለው።


3) ሰራተኛ motivated ከሆነና መልካም ግንኙነት ከተፈጠረ፥ አስተዳደራዊ ስራ ላይ የሚያደርሰውን ተጨማሪ ጫና ይቀንሳል። የስራ ሃላፊዎች፥ ዳሬክተሮችና ስራ አስፈፃሚው አካል፥ ስትራቴጅክ ዕቅዶችን ማስፈፀም ተግባራቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ዕድል ይሰጣቸዋል።
Motivated staff reduce operational errors, freeing CEOs and directors from daily firefighting.

4) አስተዳደሩ ስልታዊ መርሃ-ግብሮችን በብቃት ለማስፈፀም ነፃነት ካገኘ፥ አማራ ባንክ ከምታስቡት በላይ ያድጋል።

በወርሃ ሃምሌ፥ በርካታ የኑሮ ውድነት ያስጨነቃቸውን የባንካችን ሰራተኞች፥ ቤተሰቦቻቸውን እና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አስደስታችኋልና ምስጋና ይገባችኋል።

ተባረኩ! መልካም ሰንበት።

Follow us and share it.
Thank you.

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Dallas?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Dallas, TX

Opening Hours

Monday 8am - 6pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 8am - 6pm
Thursday 8am - 6pm
Friday 8am - 6pm
Saturday 8am - 6pm
Sunday 9am - 1pm